Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

እንቁላል የሚያስገርሙ በጣም በርከት ያሉ የጤና በረከቶች አሉት፡፡

አስገራሚ 7 የእንቁላል የጤና ጥቅሞች



እነዚህ አስገራሚ የጤናማ እንቁላል እውነታዎች ናቸው፦

፩. ለመፈጨት ቀላል ነው
እንቁላል ፍርፍር ወይም ቅቅል ከተመገብነው በኋላ ለከርሳችን/ሆዳችን ቀላል ነው ወይም አይከብድም፡፡ ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙ እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

፪. ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሳምንት ቢያንስ 6 እንቁላል መመገብ በጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላችንን በ44% ይቀንሳል፡፡

፫. ለአይን ጤንነት ይጠቅማል
ሁለት ካሮቲኖይድ፣ ሉቲይን እና ዜክሳንቲን የጠራ እይታ እንዲኖረን እና አይናችን ጤናማ እንዲሆን ይረዱናል፡፡ እንቁላል ተመጋቢ ከሆኑ ከካታራክት እና ከፀሃይ ጐጂ ጨረር ከመጋለጥ ይከላከልልዎታል፡፡

፬. የፀጉር እና ጥፍር ጤንነትን ለመጠበቅ
በሰልፈር(ድኝ) የበለፀገ አሚኖ አሲድ በእንቁላል ውስጥ ይገኛል፡፡ የጥፍር ጤንነትና ጥራትን ይጨምራል፡፡ ሌሎች ሚኒራሎች እንደ ብረት፣ ዚንክ እና ሴሊኒየም ለፀጉር ጤንነት የበኩላቸውንድርሻ ይወጣሉ፡፡

፭. የሰውነት ክብደትን ያመጣጥናል
የሰውነት ክብደታቸውን መጨመር የሚፈልጉ ሰዎች እንቁላል ትክክለኛ ምርጫ ሲሆን በፕሮቲን ይዘቱ በጣም የበለፀገ ነው፡፡ እንቁላል የምንጠቀም ከሆነ ከመጠን በላይ እንዳንመገብ አስተዋጽኦ ያደርጋል ስለዚህ በቀላሉ የሰውነት ክብደታችንን አመጣጠንን ማለት ነው፡፡

፮. አጥንታችን ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል
ካልሲየም በሰውነታችን እንዲመጠጥ እና እንዲዋሃድ ቫይታሚን ዲ(Vitamin D) በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እንቁላል ከፍተኛ የቫይታሚን ዲ፣ ፎስፈረስና ካልሲየም መጠን አለው እነዚህ በአንድነት በመሆን የአጥንት ችግርን ይከላከላል፡፡

፯. ለአእምሮ ጤንነት አስፈላጊ ነው
እንቁላል ክሎሪንን ለአእምሮ በመመገብ ጤንነቱን ይጨምራል/ይጠብቃል፡፡ ክሎሪን መልዕክት አስተላላፊ በመሆን ያገለግላል፡፡ በእቁላል አስኳል ውስጥ የሚገኝው ፎሌት የተባለው ንጥረ ነገር የነርቭ ሴሎችን በመጠበቅ አእምሮ ተግባሩን በትክክል እንዲወጣ ያደርገዋል፡፡

መልካም ጤንነት!!
 ምንጭ፦ኢትዮጤና