Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የስልጤ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር

የስልጤ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር

 

 Image result for የስልጤ ባህላዊ አስተዳደር

 

silte በስልጤ ብሔረሰብ ውስጥ በርካታ ማህበራዊ ቡድኖች / ጐሣዎች/ ያሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስልጤ፣ መልጋ፣ ችሮ ፣ ዲላባ/ጳ/፣ ኑግሶ /ኦግሶ/፣ አሊቶ፣ አባሮ፣ ኡራጎ፣ ጉምቢ፣ ጊዳዋሁሴንና አለቂሮ ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ እያንዳንዳቸው በንዑሣን ጐሣዎች የተከፋፈሉ ናቸው፡፡

ከላይ የተገለኒትንም ሆነ ሌሎችንም ጐሣዎች በአንድ ላይ የሚያስተሳስርና የሚያስተዳድር “ጐጐት” የሚባል ባህላዊ አስተዳደር ሥርዓት ያላቸው ሲሆን የሥርዐቱ አፈፃፀም “ሴራ” ወይንም”ዳምቡስ” በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሥርዓት የሚመራው በጐሣ መሪዎች ሲሆን እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ የሥልጣን ተዋረድ እና ህጋዊ መተዳደሪያ ደንብ አላቸው፡፡

የብሐረሰቡ ባህላዊ አስተዳደር የተለያዩ የስልጣን ሀላፊነትና የሥራ ድርሻ ያላቸውን አካላት ያቀፈ ሲሆን በዚህ የስልጣን ተዋረድ መሰረት “ገራድ” ዋና ዳኛ ሲሆን ከዚህ በታች ሙሉ ገራድ፣ ወላብግራድ፣ ሣረ ገራድ በመባልየሚታወቁ ረዳቶች አሉት፡፡ ከነዚህ ባህላዊ አስተዳደር አካላት በተጨማሪ የበታች አስተዳደር የሚባሉ “ሞሮ” የጐሣ ተጠሪ፣ ሙራ” የአካባቢ ተጠሪና ተላላኪ፣ እና በቤተሰብ ደረጃ የቤተሰብ ሸንጐ የሚባሉ አሉ፡፡ እያንዳንዱ ጐሣ “ሜልቾ” የሚባል ጉባኤ አለው፡፡ ከዚህምባሻገር በብሔረሰቡ ዘንድ አራት ደረጃ ያሉት ባህላዊ የፍትህ ሥርዓት ያለ ሲሆን እነዚህም እንደየቅደም ተከተላቸው እና የሥራ ተግባራቸው “ማገ” ፣ “ራጋ” /ህግ ተርጓሚ/፣ ፈርዛገኝ /ይግባኝ ሰጪ ክፍል/ እና”ወገጋገኜ” በመባል ይጠራሉ፡፡

ይህ ሥርዓት በብሔረሰቡ ውስጥ የሚከሠቱ ግጭቶችንና ወንጀሎችን እንደየክብደታቸው እና ጥፋታቸው መጠን በመመዘን ተገቢውን ቅጣት በመስጠት በባህላዊ መንገድ ግጭት የሚፈታበት አካሄድ አለው፡፡አንድ የማህበረሰቡ አባል የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ቢፈጸም ወንጀሉን አውቆና አስቦበት አሊያም በድንገት የፈፀመ መሆን እለመሆኑን በማጣራትና በመመርመር በባህላዊ መንገድ ፍርድ ይሠጣል፡፡ ይህም በብሔረሰቡ አጋርሳ፣ ተተጋ፣ ሰበባ፣ ተልካና ተልማ በማለት እንደወንጀሎቹ ዓይነት ቅጣት ይቀጣሉ፡፡

በሥርዓቱ”ሙሊ” በሚባል የመሐላ እና የወንጀል ምርመራ ጥበብ ድብቅወንጀሎች ይወጣጣሉ፡፡ የተጠርጣሪው ወንጀለኛ የወንድናየሴት አያት ወገኖች አብረው መሀላ እንደፈጽሙ ይደረጋል፡፡ ይህን ለመፈፀም ፈቃደኛ ካልሆነ ተጠርጣሪው በወንጀለኛነት ይፈረጃል፡፡

በተለይ የነፍስማጥፋት ወንጀል የፈፀመ መሆኑ ከተረጋገጠ የወንጀለኛው ወገኖች ካሣ ይከፍላሉ፡፡ሴቶች በባህላዊ ሥርዓቱ የመሰብሰብ መብት የላቸውም፡፡ በቤተሰብ እና ከአካባቢው ሕዝብ ጋር አለመስማማት ወይም አለመግባባት ሲፈጠር ግን ሴቶች ለሸንጎው “አቤት” ይላሉ፡፡ አቤቱታቸው ተሰሚነት ስላለው ፈጣን ምላሽ ያገኛሉ፡፡ በብሔረሰቡ ዘንድ የጎሣ መሪው ሚስት “ኢቲኮ”የሚል የማዕረግ ስም ይሠጣታል፡፡ እሱ ሥልጣኑን ሲረከብ ቤተሰቧቿ ከ50-60 ከብቶች በማምጣት ድግስ ደግሠው እሷንም ለማዕረጓ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ ሴቶች በኢኮኖሚው እና በሌሎችም ሥራዎች የጎላ ሚና አላቸው፡፡ አብዛኛው ስራ በብሔረሰቡ በሴቶች ጉልበት ይከናወናል፡፡

ምንጭ፦.wordpress.com