Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ትኩስ ነገር በሞቃት ቀን መጠጣት ሰውነትን ያቀዘቅዛል ?

ትኩስ ነገር በሞቃት ቀን መጠጣት ሰውነትን ያቀዘቅዛል ?

(Does Drinking Something Hot on a Hot Day Cool you Down?)

 

Image result for hot drinks

ብዙ ጊዜ እንደ አፈ-ታሪክ ሲነገር እንሰማለን፡፡ አንዳንዶች ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነን ሲሉ ሌሎች ደግሞ ‹‹ይህ እንዴት ይሆናል፣ በሞቃት ቀን ትኩስ ነገር ስንጠጣ የባሰ ይሞቀናል እንጂ እንዴት ብሎ ይቀዘቅዘናል›› ይላሉ፡፡ እርስዎ በሞቃት ቀን ቀዝቀዝ ያለ መጠጥ የሚመርጡ ከሆነ ልብ ይበሉ፤ እውነትም በሞቃት ቀን ትኩስ ነገር መጠጣት ሰውነታችን እንዲቀዘቅዝ ይረዳል፡፡ ይህም አፈ-ታሪክ ሳይሆን በሳይንስ የተረጋገጠ ነው፡፡

 

እንዴት ያቀዘቅዘናል?

 

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ በሞቃት ቀን ከቀዝቃዛ መጠጥ ይልቅ ትኩስ መጠጥ ሰውነትን ይበልጥ ያቀዘቅዛል፡፡ ከቆዳ ውስጥ የሚወጣው ላብ የሰውነታችንን ሙቀት ለመቀነስ ተመራጭ መንገድ ነው፡፡ ትኩስ ነገር እንደ ሻይ ወይም ሙቅ ውሃ ያሉትን ስንጠቀም ውስጣዊ የሰውነታችን ሙቀት ይበልጥ ይጨምራል፡፡ ይህ ሲሆን የበለጠ እንዲያልበን ያደርጋል፡፡ በአፋችን እና በምግብ ትቦ ውስጥ ያሉ ነርቮች ለዚህ ሙቀት መጨመር መልስ በመስጠት ለአዕምሮአችን የበለጠ ላብ እንዲመረት መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ ባላበን ቁጥር ደግሞ ሙቀት እየተነነ ሰውነታችን ይቀዘቅዛል፡፡

ውሃ ልዩ የሆነ ባህሪ አለው፡፡ ይህም ባህሪ ለመትነን ብዙ ሙቀት ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ውሃ በላብ መልክ ከሰውነታችን በተነነ ቁጥር  ብዙ ሙቀት ተሸክሞ ይወጣል ማለት ነው፡፡ ሰውነታችንም ቀዘቀዘ ማለት ነው፡፡

አንድ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ቢኖር ማላብ የሚጀምረው ወይም የሚጨምረው ሰውነታችን በመጀመሪያ ሞቃት ሲሆን ነው፡፡ ትኩስ ነገር በምንጠጣበት ወቅት ሊሞቀን ይችላል፤ ግን ላብ በሚወጣበት ጊዜ ግን ቅዝቃዜ እየተሰማን ይመጣል፡፡

ማላብ ለሰውነታችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በሞቃታማ አገር እየኖርን የማያልበን ከሆነ ማዕከላዊ የሰውነት ሙቀታችን ጨምሮ ለሞት ሊዳርገን ይችላል፡፡ ለሞት እና ለአዕምሮ መበላሸት ለመዳረግ የሁለት ዲግሪ ሙቀት መጨመር ብቻ በቂ ነው፡፡

 

የሚያቃጥሉ ምግቦችን ስለመመገብ

 

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ትኩስ ነገር መጠጣት ብቻ ሳይሆን የሚያቃጥሉ ምግቦችን በሞቃት ጊዜ መመገብም ሰውነትን ያቀዘቅዛል፡፡ ለምሳሌ ያክል እንደ ቃሪያ ያሉት ካፕሴያሲን (Capsaicin) የተባለውን ኬሚካል የያዙ ምግቦች ልክ እንደ ትኩስ መጠጥ በአፍና በምግብ ቱቦ ላይ ባሉ ነርቮች ላይ ስራቸው ስለሚሰሩ ላብ የበለጠ እንዲመረት ያደርጋሉ፡፡ ይህ በርግጥ ያቀዘቅዛል፡፡ ለዚህም ነው በመካከለኛው ምስራቅ፣ በእስያ እና በደቡብ አሜሪካ ባሉት ሞቃታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች የሚያቃጥል ወይም ቅመማ ቅመሞች የበዛበት ምግብ የሚያዘወትሩት፡፡ ይህ አጋጣሚ ሳይሆን ሳይንሳዊ ትንታኔ ያለው ነው፡፡

 

ቀዝቃዛ ነገር ስለመጠጣት ወይም ስለመመገብ

 

አብዛኞቻችን የምናደርገው በሞቃት ወቅት ቀዝቃዛ ነገር መጠጣት ነው፡፡ ነገር ግን ቀዝቃዛ መጠጦች ለጊዜው ብቻ ነው ቅዝቃዜ የሚፈጥሩልን፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የመጠጡ ቅዝቃዜ ከሰውነታችን ሙቀት ጋር ሲነፃፀር እዚህ ግባ የማይባል ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ የማቀዝቀዝ ችሎታው ወዲያውኑ ይጠፋል፡፡ ብዙ የቀዝቃዛ መጠጥ ከጠጣን ደግሞ የደም ስሮቻችን ስለሚጠቡ ላብ መውጣት ያቅተዋል፡፡ ስለዚህ የበለጠ እንዲሞቀን እንጂ እንድንቀዘቅዝ አያደርገንም፡፡

ስለዚህም ይህ አፈ-ታሪክ እንዳልሆነ ማስታወስ ይገባል፡፡ በሞቃት ቀን ትኩስ ነገር መጠጣት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ እውነትም ያቀዘቅዘናል፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች፡

የአየሩ ሙቀት ሞቃታማ መሆን አለበት፡፡

አየሩ ደረቅ እንጂ እርጥበታማ (Humid) መሆን የለበትም፡፡

ላባችን ሳይታገድ መትነን መቻል አለበት፡፡ ይህም ማለት ቆዳችን በወፍራም ልብሶች መሸፈን የለበትም ማለት ነው፡፡

 

ምንጭ፡-wanawtenanew