Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ከብርሀን ፍጥነት በላይ ለምን መጓዝ አይቻልም ?

 

ከብርሀን ፍጥነት በላይ ለምን መጓዝ አይቻልም ?

(Why Can't Anything go Faster than Speed of Light?)

 

Image result for ፍጥነት

 

አልበርት አንስታይን በአንድ ወቅት የብርሃን ፍጥነት የጠፈር (Universe) የፍጥነት ወሰን እንደሆነ ተናግሯል፡፡ እሱ እንዳለው ከሆነ ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ የማይታሰብና የፊዚክስ ሕግን እና ሌሎች መሠረታዊ ሕጎችን የሚጥስ ነው፡፡ ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ ማለት ሽጉጥ ሳንተኩስ ጥይቱ ኢላማውን እንደመታ ማለት ነው፡፡

የብርሃን ፍጥነት በኦና (Vacuum) ውስጥ 186,282 ማይል በሴኮንድ (299791 ኪሎ ሜትር በሴኮንድ) ነው፡፡ ብርሃን በዚህ ፍጥነት ሊጓዝ የቻለው ክብደት ስለሌው ነው፡፡

ማንኛውም በጠፈር ውስጥ የሚገኝ ቁስ አካል ብርሃንን ጨምሮ <<Higgs field>> በተሰኘ ይዘት ውስጥ ይንቀሳቀሳል፡፡ የተለያዩ ቁስ አካላት ከ<<Higgs field>> ጋር በሚያደርጉት ጥምረት የተነሳ ክብደታቸውን ያገኛሉ፡፡ በተለያየ ጥንካሬ የሚፈጥሩት ጥምረትም የተለያየ ክብደት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ ብርሃን ግን በ<<Higgs field>> ውስጥ ይንቀሳቀስ እንጂ ጥምረት ስለማይፈጥር ክብደት አይኖረውም፡፡ ይህም ማለት ብርሃን በ<<Higgs field>> እገዳ ስለማይካሄድበት እንደፈለገና በተቻለው የፍጥነት መጠን መጓዝ ይችላል ማለት ነው፡፡

 

የጠፈር የፍጥነት ወሰን (Universal Speed Limit)

 

ክብደት ያላቸው ቁስ አካላት በሙሉ ፍጥነት ለመጨመር የሆነ ሀይል (Energy) ያስፈልጋቸዋል፡፡ የአንድን አካል ፍጥነት ወደ ብርሃን ፍጥነት እንዲቀርብ ለማድረግ የበለጠ ሀይል መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ፍጥነት በጨመረ ቁጥር ክብደትም ስለሚጨምር ነው፡፡ በአጭሩ በፍጥነት ከተጓዝን ክብደታችንም አብሮ ይጨምራል፡፡

በዚህ እውነታ የተነሳ አንድ ነጠላ ኤሌክትሮን በብርሃን ፍጥነት እናስኬድ ብንል ያልተወሰነ ሀይል ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም ክብደቱ ያልተወሰነ አና በጣም ትልቅ ስለሚሆን ነው፡፡ በዚህ ጠፈር ላይ በምንም ተዓምር አንድን ኤሌክትሮን ወደ ብርሃን ፍጥነት የሚያፈጥን ሀይል የለም፡፡ ስለዚህ አንድን ኤሌክትሮን እንኳን በዚህ ፍጥነት ማንቀሳቀስ የሚችል ሀይል በሌለበት ጠፈር ውስጥ ሌላ ነገር በዚህ ፍጥነት መጓዙ ፈፅሞ ሊታሰብ አይገባም፡፡

 

አንፃራዊ እይታ (Theory of Relativity)

 

አንስታይን Theory of Relativityን በመሰረተበት ወቅት የተጠቀመው ዘዴ ቢኖር ጠፈርን ከብርሃን አንፃር መመልከት ነበር፡፡ እርስዎ ብርሃን ቢሆኑ ኖሮ ጊዜ ለእርስዎ ምንም ትርጉም አይኖረውም፡፡ ሁሉም ነገር ወዲያውኑ ይከሰታል፡፡ ለምሳሌ ያክል እርስዎ ከአንድ ሩቅ ኮከብ የተገኙ ብርሃን ቢሆኑ እና ወደ እኔ አይን ለመድረስ ከእኔ አንፃር 4 ቢሊዮን አመታት የሚፈጅብዎት ነው እንበል፡፡ ከእርስዎ አንፃር ብንመለከት ግን ከአንድ ኮከብ ወደ እኔ አይን ለመድረስ ምንም ጊዜ አይፈጅቦትም፡፡ ስለዚህ ጊዜ ለእርስዎ ትርጉም የለውም ማለት ነው፡፡ የእርስዎ ውልደትም ሞትም አንድ ላይ ነው፡፡

 

ይህ ሊሆን የቻለው ወደ ብርሃን ፍጥነት እየተቃረብን በመጣን ቁጥር፣ ጊዜ እያጠረና እያጠረ እስከመቆም ድረስ ይደርሳል፡፡ ይህ ራሱ ለምን ከብርሃን ፍጥነት በላይ መጓዝ እንደማይቻል አንድ ምክንያት ነው፡፡ የቆመ መኪናን ለማቆም መሞከር እንደማለት ነው፡፡

 

አንድ ሰው የብርሃን ፍጥነትን ልክ እንደ አልተወሰነ ፍጥነት (Infinite Speed) ሊመለከተው ይገባል፡፡ ብዙ ጊዜ የሚፈጠረው ግራ መጋባት፣ የብርሃን ፍጥነትን ልክ እንደ ውስን ፍጥነት (Finite Speed) መመልከት ነው፡፡ ከውጪ ላለ ሰው ውስን ፍጥነት ሆኖ ሊታይ ይችላል፤ ነገር ግን እንደ ብርሃን ሆነው ካዩት ያልተወሰነ ፍጥነት ሆኖ ያታይዎታል፡፡ በብርሃን ፍጥነት ቢጓዙ ኖሮ የፈለጉበት ቦታ በዜሮ ሴኮንድ ይደርሱ ነበር፡፡

 ምንጭ፡-speedoflight