Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ደራሲ ሲድኒ_ሼልደን

በ 17 ዓመቱ እራሱን ሊያጠፋ የነበረዉ ደራሲ

 

 

 

የእዉቁ ደራሲ ሲድኒ ሼልደን ስም ሲነሳ በመጻፍ ንባብ ፍቅር ስር የወደቀ ሁሉ የሚስማሙበት የጋራ ነጥብ አለ ሼልደን የፈጠራ ስራዎች አባት መሆኑን፡፡በቃላት ላይ ህይወቱን የመዝራትን ታላቅ  ክህሎት የታደሰዉ ሸልደን ያገኘዉ ክብርና ዝና ለመጎናጸፍ በርካታ የህይወት መሰናክሎች ማለፍ ግዴታዉ ነበር፡፡ሲድኒ ሼልደን 50ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ እስኪገባ ድረስ ረዥም ልብወለዶችን መፃፍ አልጀመረም ነበር፡፡ ከዚያ በፊት በነበሩት ጊዜያት “I Dream of Jeannie” እና “The Patty Duke Show” የመሳሰሉ ተወዳጅ የቴሌቭዥን ድራማዎችን ነበር የሚፅፈው፡፡ ቬልይን “The Bachelor and the Bobby Soxer” በተባለች የፊልም ጽሑፉ ኦስካር አሸንፏል- “ምርጥ ኦሪጅናል የፊልም ጽሑፍ” በሚል ዘርፍ፡፡ማግኘት ይቀል ነበር። ዩሪስ ከነሮበርት ሉድለም፣ ሲድኔ ሼልደን፣ ፍሬድሪክ ፎርሳይዝ፣ ሀሮልድ ሮቢንስና ኧርቪንግ ዋለስ ጋር በእንግሊዝኛ መፃሕፍት አንባቢያን ዘንድ ተፈላጊነት ከነበራቸው ደራሲያን አንዱ ነበር አለማችን ካፈራቻቸውና በስነ-ፅሁፍ ስራቸው አንቱ ከተባሉ ታላላቅ ፀሀፍት መካከል የይሁድ ዝርያ ካላቸው ራሺያዊ ቤተሰቦቹ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር February 11,1917 Chicago , Illinos የተወለደው የአለማችን ቁጥር አንድ የስለላ መፅሀፍት ደራሲ የሆነው #ሲድኒ_ሼልደን አንዱ ነው፡፡

ሼልደን በህይወት በቆየባቸው 89 አመታት ውስጥ ሶስት ሚስቶችን ያገባ ሲሆን ከመጀመሪያ ባለቤቱ (Jane kaufman handing ጋር ከ 1945-1948 በፍቺ የተለያዩ ፣) (ከሁለተኛ ባለቤቱ ከሆነችዉና አንድ ልጅ ለማፍራት ከበቁት Jorja cunright ጋር ከ 1951-1985 በሚስቱ ሞት ምክንያት የተለየ) እንዲሁም በስተመጨረሻ ካገባት እና በሱ ሞት ምክንያት ከተለያት Alexandra Joyce kostoff ጋር ከ 1989-2007 አመተ ምህረት ድረስ) ሶስት ሚስቶችን አግብቶ ኖሯል፡፡

ሼልደን ካበረከታቸው የስነ ፅሁፍ ስራዎች ውስጥ አብዛኞቹ በሀገራችን ቋንቋ ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎች ለትርጉም ሊበቁ ችለዋል፡፡

ሼልደን ካበረከታቸው የስነ ፅሁፍ ስራዎች መካከል ፦

=The stars shine down (1992)

=A stranger in the mirror (1976)

=The best laid plans (1997)

=The naked face (1970)

=Tell me your dreams ሇላም "ህልምሽን ንገሪኝ" በሚል ወደ ሀገራችን ቋንቋ ሊተረጎም የበቃ (1998)

=Memories of midnight (1990)

=Rage of angels (1980)

=Nothing lasts forever (1994)

=Bloodline (1977)

=Master of the game አስኳል ተብሎ በሀገራችን ቋንቋ የተተረጎመ (1982)

=If tomorrow comes (1985)

=The dooms day conspiracy የፍርድ ቀን ዘመቻ በሚል ለትርጉም የበቃ (1991)

የሚሉ እና ሌሎች በዚህ ፅሁፍ ያልተካተቱ በርካታ የስነ ፅሁፍ ድርሰቶች መካከል ለንባብ ያበቃቸው ስራዎቹ ናቸው፡፡

ሼልደን ሁለተኛ ካገባት ሚስቱ አንድ ልጅ ያለው ሲሆን አብዛኞቹ የስነ ፅሁፍ ስራዎቹ የወንጀል ነክ እንደሆኑ ይታመናል፡፡

ሼልደን በተወለደ በ 89 አመቱ Rancho mirage, California ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡

 

ምንጭ፡- ቃልኪዳን መፅሄት 2002 አትም