Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

አደሬ በሐረር ከተማ ውስጥ የሚኖር የአንድ የጎሳ ስም ነው።

አደሬ ብሔር

 

 

አደሬ በሐረር ከተማ ውስጥ የሚኖር የአንድ የጎሳ ስም ነው። አደሬዎች ቀደም ባለው ዘመን ከሸዋ ወደ ሐረርጌ የሄዱ ሲሆኑ ስልጤዎች በቅርበት ይዛመዷቸዋል። በግራኝ አህመድ ንቅናቄ ጊዜ ከአረብና ከቱርክ አገሮች በቅጥርና በእርዳታ የመጡ ወታደሮች ጦርነቱ ሲያበቃ ያልተመለሱ በሃይማኖት አንድነት ምክንያት ከአደሬዎች ጋር ተጋብተው ቀርተዋል።

በአፄ ዮሐንስ አራተኛ ዘመነ መንግስትም ግብጾች አስግረው ገብተው ለአስራ አንድ አመት ስለቆዩ በዘመኑ የወለዷቸው ልጆች ከጎሳው ጋር ተቀላቅለዋል። ስለሆነም ከሌላው ኢትዮጵያዊ የአደሬ ጎሳዎች በአማካኝ ቀላ ይላሉ።

 

በኦሮሞ መስፋፋትና በሌሎች ምክንያቶች አደሬዎች በመጨረሻ የተገኙት በሐረር ከተማ ግንብ ውስጥ ብቻ ነበር። በ1940ዎቹ ዓ.ም ውስጥ መንግስት ለመመስረት ሲያድሙና በመስጊዳቸው ውስጥ በድብቅ የጦር መሳሪያ እያካበቱ ነው በሚል ተይዘው አድመኞች ናቸው የተባሉት ሲፈረደባቸው በመላ ኢትዮጵያ ተሠራጭተው ፖለቲካውን በመተው የንግድ ስራቸውን በማስፋፋት ኑሯቸውን ቀጠሉ።

አዲስ አበባ ውስጥ በመርካቶ አካባቢ በብዛት እንደሚኖሩ ይስተዋላል። በዚሁ ምክንያት አዲስ አበባ ውስጥ የአደሬ ሰፈር የሚባል መንደር አለ። በተጨማሪም በመካኒሳ መንገድ ከቫቲካን ኤምባሲ በታች ብዙ አደሬዎች እንደሚኖሩ እና ለነዋሪው ቅርብ የሆነ መስጊድ እንዳለም ይታዎቃል። በተጨማሪም በሰበታ መንገድ ዳለቲ በሚባል መንደር በከብት እርባታ፣ በአነስተኛ ኢንዱስትሪና እርሻ ተሰማርተው የሚገኙ ቁጥራቸው ከፍ ያሉ አደሬዎች እንዳሉ ይነገራል።

 

 

አደሬዎች ቇንቇቸው እንደ ግዕዝ፣ አማርኛ ትግርኛ እና ጉራጊኛ የሴም ቇንቇ ሲሆን በብዛት የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ናቸው። የተለየ የባህል ልብሳቸውም ቀለምና ጌጥ የበዛው ነው። ሴቶች የእጅ ስራ አዋቂ ከመሆናቸውም በላይ በመኖሪያ ቤታቸው ግድግዳዎች ላይ የተጌጡ የምግብ ቤት ቁሳቁሶች በመስቀል ቤታቸውን እንደሚያስውቡ ይነገርላቸዋል።  የአደሬዎች  የህዝብ  ብዛት  በአሁኑ  ወቅት  ወደ  አርባ  ሺህ  ገደማ  እንደሚጠጋ  ይገመታል ።

 

ምንጭ :የ20ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ፣ በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ