Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የወላይታ ብሄረሰብ ግፋታ በዓል

ግፋታ

 

Image result for ግፋታ ወላይታ

 

ኢትዮጵያ ከ84 በላይ ብሄር በሄረሰቦች በመፈቃቀድ ተባብረዉና ተከባብረዉ የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን እነዚህ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች  ደግሞ ራሳቸዉን ባህል፤ትዉፊትና ሀይማኖት አላቸዉ፡፡ እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ ታዲያ የራሱን ባህልና ትዉፊት ወደ ቀጣዩ ትዉልድ የሚያስተላልፍበት የየራሱ የዘመን ቀመርና በአል አከባበር ስርአት አለዉ፡፡

ከነዚህ የህብረተስ ባህላዊ ዕሴቶች አንዱ የሆነዉ የወላይታ ብሄረሰብ ግፋታ በዓልን እንዲህ ቃኝተናል፡፡

በብሄረሰብ ቋንቋ ግፋት ማለት ትርጉሙ በኩር ወይም ታላቅ ማለት ሲሆን ብሄረሰብ አዲስ አመትን አንድ ብሎ የሚጀመርበት የአዲስ አመት መግቢያ ብቻም ሳይሆን የብርሀን ግዜ ማብሰሪያ ነዉ፡፡

የግፋት በአል መከበር የጀመረበት ጊዜና አመት ምህረቱ በዉል የማይታወቅ ቢሆንም የወላይታ ብሄረሰብ አሃዱ ብሎ ማህበራዊ ተቋም መስርቶ በኦሞኖና በብላቴ ተፋሰሰ አካባቢዎች በአንድ ጥላ ስራ መኖር ከጀመረበት ከክርስቶስ ልደት በፊት መሆኑን የብሀረሰቡ ባህልና ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

በአሉ ለመከበሩ መነሻ በቀደሙት ዘመናት የወላይታ ብሄረሰብ የሚኖሩበት አካባቢ በደን የተሸፈነ ስለነበር ከሀምሌ ወር መጀመሪያ አስከ ነሀሴ ጨረሻ ድረስ ሀይለኛ ክረምት ነዉ፡፡

በመሆኑም የክረምት ጎርፍ ለሰዉና ለእንሰሳቱም አስፈሪ በመሆኑ ከቤት መዉጣት የማይችሉበት ወራቶች ናቸዉ፡፡ የብሄረሰቡ አባላት በቤተሰቦቻችን ከብቶቻችን  ሳይጎዱን በጎርፍ ሳይወሰዱ እነዚህን የጨለማ ጊዜያት አለፈን ብርሀን አየን በማለት ለፈጣሪያችን ምስጋና የምስጋና የሚያቀርቡበት ነዉ፡፡

በአሉ የሚከበረዉ መስከረም ከገባ ከ14 እስከ 20 ባለዉ ቀናት ውስጥ አንዱ በሆነዉ ዕሁድ ዕለት ሲሆን በዚሁ ቀን የወላይታ አዲስ  አመት አንድ ተብሎ ይጀመራል፡፡

በአሉ መከበር ሲጀምር በአካባቢዉ የእስልምናም ሆና የክርስትና ሃይማኖቶች ያልነበሩ ሲሆን ለየትኛዉም ለሚያመልኩት አምላክ በሰላም ስላደረስከን በማለት ምስጋና የሚያቀርቡበት በመሆኑ ምንም ሃይማኖታዊ መሰረት የለዉም፡፡

ለግፋት በዓል ከአመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ሰፊ ዝግጅት የሚደረግ ሲሆን አባዎራዎቹ ደግሞ ለቅቤ መግዣ  ገንዘብ ያጠራቅማሉ፡፡ ከሰኔ 27 ጀምሮ  አስከ በአሉ ያሉት ቀናት ወጣቶች  ወደ ጫካ በመሄድ ለሌላ ስራ አገልግሎት የማይሰጡ እንጨቶች በመሰብሰብ በየአከባቢያችን አንድ ቦታ ላይ የሚመከሩበት ጊዜ በመሆኑ በብሄረሰቡ አጠራር ጉሊያ ይባላለ፡፡

ጊሊያ የአማሪኛ ትርጉሙ ደመራ ማለት ነዉ፡፡

ጉሊያ/ደመራ/ መሰብሰብ ከተጀመሩት ጊዜ አንስቶ ሰዉ ሁሉ ስለ በዓሉ ማሰብ ይጀምራል፡፡ አባቶች ስለ አቅጣጫ ሰንጋ እናቶች ደግሞ ስለተለያዩ ምግቦች ዝግጅት የሚያሳቡበት የሚጨነቁበት እንዲሁም ለከብቶቻቸዉ  ምግብ  የሚያሰባስብ ቡበትና ሳር የሚያዘጋጅበት ጊዜ ነዉ፡፡

ለበዓሉ አብዛኛዉ ምግብ  የሚዘጋጀዉ ከእንሰት ዉጤቶች በመሆኑ አባወራዎች በማሳ ውስጥ ካሉት የተሸለዉን መርጠዉ ቅጠሉን በመቁረጥ ለእማዎራዎች ሲያስረክቡ እማወራዎች ደግሞ ለየምግብ አይነቱ ያመቻቻሉ፡፡

ምንጭ፡- ማህደረ ደቡብ ከሀምሌ-መስከረም 2008ዓ.ም