Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

"ዳጉ" በተሰኘው ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓታቸው - አፋሮች።

"ዳጉ" እና አፋሮች

 

 Image result for ዳጉ እና አፋሮች

 

መንደር…ሰፈሩ…ቀዬው አማን ውሎ አማን አድሯል? ግመል…ፍየሉ…ከብት…ሐብት… ንብረቱስ እንዴት ከራርሟል? ይጠያየቃሉ፤ መረጃ ሰጥተው መረጃ ይቀባበላሉ። መልዕክት ይለዋወጣሉ - "ዳጉ" በተሰኘው ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓታቸው - አፋሮች። በአፋር ጥግ ካለ አንድ የገጠር ቀበሌ የተከወነ አዲስ ነገር ከወዲያ ማዶ ካለ ጆሮ ሊደርስ አፍታም አይፈጅበት፤ መልዕክቱ ክንፍ ያበቀለ ያህል ፍጥነቱ አይጣል ነው።

 

ሰዎች ባሉበት ሁሉ መረጃ አለ። እንደዛሬው ቴክኖሎጂ ባልተስፋፋበት ዘመን ያኔ ድሮ በልማዳዊው ሁኔታ መልዕክት የመቀባበል ዘዴን አፋሮችን ያህል የተጠቀመበት መኖሩ ያጠራጥራል - በ"ዳጉ" የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት። ዛሬስ! አፋሮች እና ዘመናዊው የመረጃና ኮሙዩኒኬሽን የአሠራር ግንኙነታቸው ምን ይመስላል? ኋላ ላይ እናየዋለን።

በኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት ሰሞኑን በሎጊያ ሰመራ በተካሄደ የምክክር መድረክ የመሳተፉ እድል ገጥሞኝ ነበረና ስለቆይታዬ ጥቂት ላወጋችሁ ፈቀድሁ።

 

የመወያያ ርዕሰ ጉዳዩ "የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶችን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ሚና ወሣኝ ነው" የሚል ነው። በልምድ መለዋወጫ መድረኩ ላይ ከአፋር 32ቱ ወረዳዎች የተውጣጡ የኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

 

በኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያው ዘርፍ የሌሎች ክልሎች ተሞክሮ ምን ይመስላል? ቅድሚያ አጀንዳውን የወሰደው ይህ ጉዳይ ነበር። ለመድረኩ በመልካም ተሞክሮ የቀረበውም የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ነው።

 

በኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የግንኙነትና ገጽታ ግንባታ  ጄኔራል ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ አብዱራህማን ናስር የልምድ ልውውጥ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ዙሪያ የተከናወኑ የኮሙዩኒኬሽንና የሚዲያ ሥራዎችን የሚያሳይ ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው ብለዋል።

በዚሁ መሠረት በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች የልማት ተጠቃሚነት ዙሪያ የተከናወኑ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ተግባራት መልካም ተሞክሮ ይቀርብበታል። ልዩ ድጋፍ የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚዲያ ተደራሽነት ዙሪያ እና የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶችን ጉዳይ በእቅድና ሪፖርት አካቶ የመሥራት /ሜንስትሪሚንግ/፣ በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ርዕሰ ጉዳዮች ይቀርቡበታል።

 

በተጨማሪም በአፋር ክልል በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች የልማት ተጠቃሚነት ዙሪያ የተሰሩ የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ሥራዎች ይጎበኛሉ፤ ተሞክሮም ይወሰድበታል። በቀጣይም የሚቀሰመውን ልምድ ወደየአካባቢው በመውሰድና ከነባራዊው ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ የሚደረግበትና የተሻለ ውጤት የሚመዘገብበት ይሆናል። በየደረጃው ያለው አመራርም ከተወሰደው ልምድ በመነሳት የተሻለ ሥራ ለማከናወን ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታ ይፈጥርለታል ሲሉ ተጠባባቂ ጄኔራል ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

 

ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣት ኢንፎርሜሽን በትክክልና በወቅቱ ከመስጠት ውጪ ሊሳካ አይችልም። ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣት አገራችን ያላት ዋነኛ መተማመኛ ሐብትም የሰው ኃይል ነው፡፡ የሚፈለገው ዓይነት ልማት በተፋጠነ ጊዜ የሚመጣው ኅብረተሰቡን ለዚህ ዓላማ በማነሳሳት ማሰለፍ ሲቻል ብቻ ነው፡፡

 

ይህ ደግሞ ውጤታማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ሥራ ከመከወን ውጪ ሊመጣ አይችልም። በመሆኑም በክልሉ በመመዝገብ ላይ ላለው ፈጣንና ቀጣይነት ልማት በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግሥት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሴክተር የማይተካ ሚና ተጫውቷል።

 

በዚህም ሂደት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሴክተር ከክልሉ አጠቃላይ ህዝብ ከግማሽ በላይ የሆኑት ሴቶች እንዲሁም ህፃናትና የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ለማክበር፣ የመብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ የእነዚህ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፎች የጎላ ድርሻ እንዲይዝ ለሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።

 

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግሥት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሴክተር የንጋት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ዳዊት ሺፈራው በአፈጻፀም ሂደቱ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ በዝርዝር አቅርበዋል።

 

የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ተሣትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከተከናወኑ ዐቢይ ተግባራት መካከል ኢንፎርሜሽን በህትመት ውጤቶች በወቅቱ ለተገልጋዮች በማሰራጨት የሴቶችን፣ ህፃናትና ወጣቶችን አመለካከት ለመቅረጽ፣ ግንዛቤ ለማዳበርና ለልማት ለማንቀሳቀስ በሴክተሩ ሰፊ ተግባራት ተከናውነዋል።

በዚህም መሠረት ጋዜጣ (በቋሚነት በሴቶች ዓምድ በየ15 ቀኑ በ10 ሺህ ኮፒ)፣ መጽሔት፣ የዜና መጽሔት፣ በራሪ ጽሁፍ፣ ቡክሌት፣ ዓመታዊ መጽሐፍ፣ ካሌንደር፣ ቢልቦርድ እና ፖስት ካርድ ብሎም አጀንዳዎች እየታተሙ በየጊዜው ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች፣ ለዞኖች፣ ለሀዋሣ ከተማ አስተዳደር፣ ለልዩ ወረዳዎች፣ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ለትምህርት ቤቶች እንዲሰራጩ ተደርጓል፡፡

 

በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ደግሞ መሠረታዊና በወቅታዊ፣ ክልላዊና አገራዊ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዙሪያ ለክልሉ ኅብረተሰብ የተሟላ ኢንፎርሜሽን ለመስጠትና የተገኘውን ኢንፎርሜሽን ተጠቅሞ በአካባቢው፣ በክልሉና በአገሩ ጉዳይ ላይ ያለውን ተሣትፎ ለማጎልበት ጥረት እየተደረገ ነው።

 

በዚህም የራዲዮና ቴሌቪዥን ዜናዎች፣ ፕሮግራሞች፣ የመንግሥት አቋም መግለጫዎች እና አጫጭር መልዕክቶች በየጊዜው እየተዘጋጁ በደቡብ ኤፍ.ኤም 1ዐዐ ነጥብ 9 ራዲዮ፣ በደቡብ ቴሌቪዥን፣ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በቪዲዮ ዶክመንታሪ እንዲሁም በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን፣ በፋና እና በአካባቢ ራዲዮኖች እንዲሰራጩ ተደርጓል፡፡

 

በተጨማሪም የተመረጡ ዜናዎች፣ ኘሮግራሞች እና ዜና ትንታኔዎች ወደተጠቃሚው ብሔር ብሔረሰብ ቋንቋ ተተርጉመው በአካባቢያዊ ራዲዮኖች እንዲሰራጩ መደረጉን አቶ ዳዊት አስታውቀዋል። ይህም በአማርኛ ቋንቋ በሚሰራጨው የመንግሥት ኢንፎርሜሽን ተደራሽ ያልሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በራሳቸው ቋንቋ ተደራሽ ለማድረግ ተችሏል፡፡

በደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በራዲዮ በቋሚነት “የሴቶች ራዕይ” በሚል ፕሮግራም በየሣምንቱ የሃያ ደቂቃ ሽፋን እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም በራዲዮ “ስለ እኛ” (ከሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ጋር በትብብር የሚሰራ) በሣምንት ለሃያ ደቂቃ። በቴሌቪዥን ደግሞ “ሴቶች” በሚል ፕሮግራም በቢጋር የታቀፈ በሣምንት ለሰላሳ ደቂቃ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳዮች ሽፋን ያገኛሉ።

 

የንጋት ጋዜጣ ዋና አዘጋጁ እንዳሉት የሴቶች፣ የህፃናትና የወጣቶችን ማህበራዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚነት ከማሳደግ አኳያ ስለ ሴቶች የትምህርት ተሣትፎ በኅብረተሰቡ ዘንድ አዎንታዊ ግንዛቤ እንዲፈጠር፣ የሴቶች ጤና በተለይ በቤተሰብ ደረጃ የጤና ኤክስቴሽን እንዲሻሻል፣ የእርግዝናና የወሊድ አገልግሎት እንዲጠናከር፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻል ሰፊ ሥራዎች ተከናውነዋል። 

በተጨማሪም በአጎበር አጠቃቀም፣ የህፃናት ሞት መጠንን በመቀነስ፣ እናቶች በወሊድ ምክንያት እንዳይሞቱ በማስተማር፣ የመጠጥ ውኃ በማሻሻል ሴቶች ውኃ ፍለጋ  የሚያጠፉትን ጊዜ ለምርት ተግባር እንዲያውሉ፣ ህገ ወጥ የህፃናት ዝውውርና ጉልበት ብዝበዛን በመከላከል፣ በህፃናት አያያዝ፣ ድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት እንዲጠናከር፣ የሴቶች የልማትና የለውጥ ፓኬጅ ባስገኘው ፋይዳ የተጠኑ ጥናቶችን በማስተዋወቅ፣ ለሴቶችና ወጣቶች የተሣትፎና ንቅናቄ ኮንፈረንስ በቂ የሚዲያ ሽፋን በመስጠት በህፃናት መብትና ደህንነት ዙሪያ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ የሚያጎለብቱ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገብ ተችሏል።

 

የጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ተጽዕኖን ለመቀነስ ለተፈጠሩ የህዝብ ንቅናቄዎች በቂ የሚዲያ ሽፋን በመስጠት ወንጀልን በመከላከል፣ በሴት ልጅ ግርዛት፣ ጠለፋ፣ ያለዕድሜ ጋብቻ፣ የሚፈፀሙ የኃይል ጥቃቶች እንዲቀንሱ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ እንዲሁ መልካም ተግባራት ተከናውነዋል። የሴቶችን ማህበራዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንጻር በተሰራው ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ በመላው ኅብረተሰብ ዘንድ አዎንታዊ ግንዛቤ በመፈጠሩ በአርብቶ አደር አካባቢዎችም ጭምር የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ በእጅጉ መጨመሩን አቶ ዳዊት ጠቁመዋል።

 

በአጠቃላይ የመንግሥት ኢንፎርሜሽን በህትመት ውጤቶች፣ አገራዊ፣ ክልላዊና አካባቢያዊ ሽፋን ባላቸው ራዲዮኖች፣ በደቡብ ቴሌቪዥን ኘሮግራም፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲሁም በገጽ ለገጽ መድረኮች በስፋት ስለሚሰራጭ የመንግሥት ኢንፎርሜሽን ተደራሽነት እያደገ መጥቷል፡፡ የተገልጋዮች የመንግሥት ኢንፎርሜሽን ተጠቃሚነትም 82 በመቶ ደርሷል።

 

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶችን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግሥት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሴክተር ስለተከናወኑ ተግባራት መልካም ተሞክሮ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

 

ይሁንና የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶችን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብሎም በሁሉም ዘርፍ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ የኮሚዩኒኬሽንና የሚዲያው ዘርፍ የጎላ ሚና ቢኖረውም በአፋር ክልል በበቂ ደረጃ የማኅበረሰብ ራዲዮ እንኳን በሌለበት ሁኔታ ይህን ተልዕኮ እንዴት መፈፀም ይቻል ይሆን? ሲሉ ጠይቀዋል - ተሳታፊዎቹ።

 

በክልሉ የማተሚያ ቤቶች በበቂ አለመኖር በሚፈለገው ደረጃ የህትመት ውጤቶችን ለማሳተምና ለማሰራጨት አለማስቻሉን፣ በክልሉ ሥር ያሉ የወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤቶች ትኩረት ማጣት፣ በበጀት፣ በሰው ኃይልና በቁሳቁስ አለመጠናከር፣ እቅድ በጋራ ተነድፎ አፈጻፀሙ አለመገምገሙ "ችግሮች" ብለው ያነሷቸው ነጥቦች ነበሩ። በተለይ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መፍትሄ ለማፈላለግ የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ (ለነገሩ ኋላ ላይ ኃላፊው ለሌላ ሥራ ጉዳይ ወደ ወረዳ መሄዳቸው ተነግሯል) በምክክር መድረኩ ላይ መሳተፍ ነበረባቸው ሲሉም ቅሬታቸውን ጠቁመዋል።

 

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግሥት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሴክተር ያለውን ተሞክሮ አሁን በቀጥታ ቀድቶ በአፋር ክልል ተግባራዊ እናድርግ ብሎ ማለም የሚታሰብ አይደለም። ሆኖም ዛሬ ላይ በትላልቆቹ ሚዲያዎች አማካይነት የሚከናወኑ ሥራዎች ወደፊት የሚደረስባቸው ሆኖ ሳለ ከዚያ በመለስ ባሉ አማራጭ ሚዲያዎች መገልገሉ ደግሞ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።

 

በኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የሚዲያ አብዝኃነት ጀኔራል ዳይሬክቶሬት የሚዲያ ልማት ባለሙያ አቶ ወንድወሰን ግርማ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ። የሚዲያ ልማት ባለሙያው እንደሚሉት ከፍተኛ ወጪና የሰለጠነ ባለሙያ በብዛት ሳያስፈልግ በአፋር ክልል የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ተሣትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጡን ሥራ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ሊከናወኑ ከሚገባቸው ተግባራት መካከል በንባብና በራዲዮ አድማጭ ቡድኖች፣ በሚኒ እና አካባቢያዊ ሚዲያዎችን ማስፋፋት ይቻላል።   በተለይም የማኅበረሰብ የመረጃ ማዕከላት እንዲጠናከሩና በቂ መረጃዎች እንዲሰራጩ ማድረግ ይቻላልም ብለዋል። ይህ ሀሳብ በሁሉም ተሳታፊዎች ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷል።

 

ያኔ ድሮ አፋሮች በ"ዳጉ" የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ቀደምት እንዳልነበሩ ሁሉ ዛሬ በዘመናዊው የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ ከወደኋላ መሆናቸው ቁጭትን ፈጥሮ የቀድሞ ሥፍራቸውን ሊይዙ ቃል የገቡበት ነው። ልማዳዊውን የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት በዘመናዊው የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ተግባር ለማጎልበት የመድረኩ ተሳታፊዎች በእልህ የተነሳሱ ይመስላል። ይስመርላቸው።

 

ምንጭ፡- አዲስ ዘመን ጋዜጣ