Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ኮንቺ ከካንሰር በሽታ ጋር ለሰባት ዓመታት ስትታገል የቆየች በመካከለኛ

 በተጫዋችነት ባህርይ  ሕመምን መቋቋም

 

Image result for happy

 

ኮንቺ ከካንሰር በሽታ ጋር ለሰባት ዓመታት  ስትታገል የቆየች  በመካከለኛው ዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ፍልቅልቅ ሴት ናት፡፡ ተመርምራ የጡት ካንሰር እንዳለባት ካወቀችበት ጊዜ አንስቶ በሽታው እንዳይሰራጭ ለማገድ ሰባት ጊዜ የቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረግ   አስፈልጓታል፡፡ ታዲያ፣ ይህን ሁሉ ልትቋቋመው የቻለችው እንዴት ነው?

ኮንቺ እንዲህ በማለት ተናግራለች፡- ‘’ዶክተሮቹ የቀዶ ጥገና ሕክምና እንደሚያስፈልገኝ   ባረዱኝ  ቁጥር አልቅሽ አልቅሽ ካለኝ ሐዘኔ እስኪወጣልኝ ድረስ ስቅስቅ ብዬ አለቅሳለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ወትሮው እንቅስቃሴዬ    በመመለስ የሚያስደስቱኝን ነገሮች ለማድረግ እጥራለሁ፡፡  ከነዚህ ውስጥ ቻይንኛ መማር፣  መስብሰባዎች ላይ መገኘት፣  እንዲሁም ከቤተሰቦቼና ከጓደኞቼ ጋር ለሽርሽር  ወጣ ማለት ይገኙበታል፡፡’’ 

አክላም፣ ‘’ሁልጊዜ ተጫዋች ለመሆን እጥራለው  ለዶክተሮች ጋር እንቀላለዳለን፣ አስቂኝ ፊልሞችን  እመለከታለሁ፣  ከዚህም በላይ ከወዳጅ ዘመዶቼ ጋር ዘወትር እገናኛለሁ፡፡  አብረዋችሁ የሚስቁ ወዳጆችን ማግኘት ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡ አንድ ቀን ወደ ጥገና ሕክምና ክፍል ከመግባቴ በፊት  አንዳንድ ጓደኞቼና ዘመዶቼ በዋዜማው ምሽት ያጋጠማቸውን  አንድ አስቂኝ ሁኔታ አወጉኝ፡፡  በጣም ከመሳቄ የተነሳ ዘና ያለ ስሜት ኖሮኝ ወደ ቀዶ ጥገና ሕክምና ክፍል ገባሁ’’ ስትል ተናግራለች፡፡

የተጫዋችነት ባህርይና አዎንታዊ አመለካከት ማዳበር የጤና   ችግሮችን  ለመቋቋም እገዛ ሊያበረክት እንደሚችል ለመገንዘብ ኮንቺ  የመጀመሪያዋ አይደለችም፡፡ ዘመናዊው ሕክምና ተጫዋች መሆን ሕመምንና በሽታን ለመቋቋም ለምናደርገው ትግል ጠቃሚ ድርሻ እንደሚያበረክት ከተገነዘበ ሰንበትበት ብሏል፡፡

ለሰውነትና ለአእምሮ ጤንነት ይጠቅማል

 በ17ኛው ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረው ስፔናዊው ደራሲ ሎፕ ደቬጋ፣ ‘’ጨዋነት የተላበሰ ቀልዶችን  ብንናገር ጤናሞች ሆነን መኖር የምንችል ይመስለኛል’’  ሲል ጽፏል፡፡  ሆኖም፣ አሁን ባለው ውጥረት በተሞላ   ዓለም ውስጥ ሰዎች  ጠቻዋችና ቀልድና ከመሆን ይልቅ ዝም ማለት   የመረጡ ይመስላል፡፡ የምንኖረው ቴክኖሎጂው እጅግ በመጠቀበት ዘመን ውስጥ ሲሆን፣  የተጫዋችነት መንፈስም  እየጠፋ መጥቷል፡፡ ኤል አርቲ ደ ላሪስ (የሳቅ ጥበብ) የተባለ አንድ የጽሑፍ ስራ በዘመናዊ ኅብረተሰብ ውስጥ ‘’ሆሞ ሳፒያንስ (ዘመናዊ ሰው) በሆሞ ዲጀታሊስት (በኮምፒውተራዊ  የሰው ምስሎች) የተተካ’’ ይመስላል በማለት ይገልጻል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተር ሳቅምና ፈገግታን የመሳሰሉ ባህርያትን የተካ ይመስላል፡፡

የታመሙ ሰዎች ተጫዋችን ቀልደኛ መሆናቸው ይበልጥ አዎንታዊ የሆነ አስተሳሰብ፣ ስሜትና ባሕርይ እንዲኖራቸው  ይረዳቸዋል፡፡ የካንሰርና የሕመም ማስታገሻ መድሐኒቶች  ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተሩ ሂማ ሳንስ-ኦርትስ በቅርብ ባወጡት  አንድ ጽሑፍ ላይ እንደገለጹት፣ ተጫዋች መሆን  ‘’የመግባባት ችሎታን ይጨምራል፣ የሰውነትን በሽታን የመከላከል አቅም ያጎለብታል፣ ሕመምን ያስታግሳል፣ ጭንቀትን ያስወግዳል፣ የአእምሮንና የጡንቻን ውጥርት ይቀንሳል፣ እንዲሁም የፈጠራ ችሎታን ለማዳበርና ብሩህ ተስፋ ለመያዝ ያስችላል፡፡’’

ተጫዋች መሆን ያለው ትልቅ ጠቀሜታ

ቀልደኛ ወይም ተጫዋች መሆን  የመፈወስ ኃይል አለው የሚባለው ለምንድን ነው በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በምንሆንበት ጊዜም  እንኳን ነገሮችን አዎንታዊ በሆነ መንገድ  እንድንመለከት  ስለሚረዳን ነው፡፡ ሳንስ-ኦርቲስ ፣  ‘’በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ተጫዋችና ሳቂታ በመሆን መሆን ሃይላችንን ማደስ፣ ደካማችንን ማቃለልና ትካዜያችንን ማስወገድ  እንችላለን’’ በማለት ተናግረዋል፡፡

ፈገግ እንድንል ወይም እንድንስቅ  የሚያደርጉን ነገሮች እንደየሰውና እንደየባህሉ እንደሚለያይ ግልጽ ነው፡፡ ሳንስ-ኦርትስ ሁኔታውን ‘’ውበት እንደ ተመልካች እንደሆነ  ሁሉ፣  ቀልድም እንዲሁ ነው’’ በማለት ይገልጻሉ፡፡  አስተዳደጋችን ወይም የትምህርት ደረጃችን  ምንም ይሁን ምን ተጫዋች ተጫዋች መሆናችን ከሌሎች ጋር ለመግባባት እንዲሁም፣ የሚሰማንን ከፍተኛ መረበሽ፣ የውጥረት ወይም የስጋት ስሜት ለማስወገድ ያስችለናል፡፡ ታዲያ፣ ይህን ያህል የሚጠቅመን ከሆነ የተጫዋችነትን ባሕርይ የምናዳብረው  እንዴት ነው?

ልንወስደው የምንችለው የመጀመሪያው እርምጃ በችግራችን ወይም በሕመማችን ላይ ብቻ  ማተኮራችንን አቁመን እያንዳንዱን አጋጣሚ ባለው አዎንታዊ ጎን  ለመደሰት መሞከር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ ችግሮችን አጋነን እንድንመለከት የሚያደርጉ የተዛቡ ወይም ሚዛናዊነት የጎደላቸው አመለካከቶችን አስወግደን  ምክኒያታዊ አስተሳሰብ  ለማዳበር ብርቱ ጥረት   ማድረግ ይኖርብናል፡፡ አንድን ሁኔታ በተለየ መንገድ  ለመመልከት በመጣርም የተጫዋችነትን ባህርይ ማዳበር እንችላለን፡፡   ሁልጊዜ ሳቂታዎች ወይም

ፈገግታ የማይለየን  ላንሆን እንችላለን፣ ሆኖም፣ የአንድን ሆኔታ  አስቂኝ ጎን ማየታችን ችግሮችን ለመቋቋም ይረዳናል፡፡ ሳንስ-ኦርትስ፣ ‘’ቀልድ ወይም ጫወታ  የሚያሳስበንን ችግር ለጊዜው ቸል ብለን ሁኔታውን ከተለየ አቅጣጫ እንድንመለከትና….. አዳዲስ የመፍትሄ  ሐሳቦችን በማፍለቅ በተሳካ ሁኔታ ችግሩን እንድንወጣ ያስችለናል’’ በማለት አብራርተዋል፡፡

ቀልደኛ የመሆን ወይም የተጫዋችነት ባህርይ በህይወተችን ውስጥ ለሚያጋጥሙን ችግሮች ሁሉ መፍትሄ ነው ማለት አይደለም፡፡ ያም ሆነ ግን፣ ችግሮችን ይበልጥ አዎንታዊ አመለካከት ይዘን ምክኒያታዊ በሆነ መንገድ እንድንጋፈጠው ይረዳናል፡፡ ኮንቺ፣ ባችሁ፡፡  ሕይወቴ በተለያዩ  አትክልቶች የተሞላ አንድ የአትክልት አፀድ እንደሆነ አድርጌ እመለከተዋለሁ፣ የሚያሳዝነው ከነዚህ ዘትክልቶች መከሰከል አንዱ ነሽታዬ ነው፡፡ ሆኖም ይህ አትክልት፣ ማለትም ያለብኝ የካንሰር ሕመም፣ ሌሎችን እንዳይበክል ጥንቃቄ አደርጋለሁ፡፡ እርግጥ ነው፣ የካንሰር በሽታ ሙሉ ለሙሉ አሸንፌዋለሁ ማለት ባልችልም፣ አሁንም ቢሆን በሕይወቴ ደስተኛ ነኝ፣ በጣም አስፈላጊው ነገር ደግሞ፣ ይህ ነው’’  ስትል ተናግራለች፡፡

ምንጭ፡- እቴጌ ቁ፡17 2002 ዓ.ም