Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ጉራጌ ምንም አይነት የሚያነጋግርም ሆነ የሚያከራክር ጉዳይ ሲገጥመው አስ?

 ጉዳ/ጉርዳ/

 

ጉራጌ ምንም አይነት የሚያነጋግርም ሆነ የሚያከራክር ጉዳይ ሲገጥመው አስቀድሞ ጉዳ/ጉርዳ/ ይያያዛል፡፡ የፍትአብሔርንም

ሆነ የወንጀል ጉዳይ በትክክለኛና ቀጥተኛ መንገድ ለመፍታት በወገኑ በሀብቱ ወይም በሌላ ሶስተኛ አካል ከመታመን ይልቅ

በጉዳ ላይ ይታመናል፡፡ ሁለት ባለጉዳዮች ጉዳ ሲያያዙ ጉዳ አያያዥ የጉዳ/ጉርዳ/ ዳነ/ዳኛ/ ቢኖርም በዋናነት የሚፈራው ግን

ጉዳ ራሱ ነው፡፡ ለምን ቢባል ማንም ጉዳ ሲያያዝ በመሀከላችን ምድርና ሰማይ ምስክር ይሁኑብን ስለሚሉ ነው፡፡ ነገሩ

መሬት የእግዚአብሔር መረገጫ ሰማይ ዙፋኑ ስለሆነች ከእግዚአብሔር ዓይን ማን ይሰወራልና ነው፡፡ ጉዳ ተጥሶ የእምነት

ክደት ቢፈፀም ባልተጠበቀ ሰዓት ክፉ ነገር ይሆንብኛል የሚል እምነት በሁሉም ሰው የልብ መዝገብ ተፅፎአልና፡፡ ስለዚህ

በማንኛውም ወቅት ጉዳ/የማይታየው ረቂቅ ሀይል/ በወንጀለኛው ወይም ጉዳን በተላለፈ አካል/ቡድን/ ላይ የበቀል ርምጃ

ይወስዳል ብሎ ስለሚያምን ይፈራዋል ያከብረዋልም፡፡ በየትኛውም የኧጆካ ጉባኤ ስሙ "ኢትፊ" ጉዳ በማለት ይጠራል

እንጂ ጉዳ ተብሎ በደረቁ አይጠራም ይህም ጉራጌ ለጉዳ ያለውን ከበሬታና ቃሉን አላግባብ ለመጥራት እንኳ ፍርሀቱን

የሚያሳየን ይሆናል፡፡

ሰዎች የጉዳ ስም ሲጠራ ፈጥነው የትኸበድ ጉዳ በአማርኛው ክብር ይሁንለት ጉዳ ይላሉ፡፡ ምክንያቱም በማወቅም

ባለማወቅም ከእውነት በወጣንበት በተላለፍንበት ፍትህ ባዛባንበት ጉዳይ ጉዳ ይቅር በለን ማለታቸው ነው፡፡ የጉዳ መያያዝ

አብዛኛውን ጊዜ የሚከናወነው በግለሰቦች መሀል ሳይሆን በጎሳዎችና በቤተ-ጉራጌዎች መሀል ነው፡፡ ይህም የሆነው በታላላቅ

ማህበረሰቦች መሀል የተከሰቱ የደም ጉዳዮች፣ጦርነቶች፣የድንበር ግጭቶች፣በጋራ ገበያ ለመውጣትና ለመነገድ የሚከለክሉ

20

ጉዳዮች፣ሴት ልጅን ለትዳር ለመውሰድ የሚከለክሉ የአንዱ ከብቶች ከአካባቢው ከብቶች እንዳይቀላቀሉ/በጋራ

እንዳይታገዱ/ የሚከለክሉ እሳት እንዳይጭሩና በማንኛውም ማህበራዊ ህይወት እንዳይሳተፉ የሚከለክሉ ጉዳዮች

የሚፈቱትና መፍትሔ የሚያገኙት ጉዳ በመያያዝ/በሰማይና በምድር ፊት/ ቃል ኪዳን በመጋባት ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳ ምንም

እንኳ በጽሑፍ የሰፈረ ህግ ባይሆንም የጉራጌ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ህይወት ያስተሳሰረ ሲሆን የጆካ ሸንጎ ፍትህ

ማስፈኛ ማስፈፀሚያ ዓይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡ ለመሆኑ ጉዳ መቼ እና እንዴት ተጀመረ? ምላሹን እንደሚከተለው

አቅርበነዋል፡፡

ጉዳ/ቃልኪዳን/ በጉራጌ ብሔረሰብ ህይወት ውስጥ ሰፊ የሆነ ማህበራዊ ፋይዳ ኖሮት ለአያሌ አመታት ሲተገበር መቆየቱን

ቀደም ባሉት ገጾች ስር አስነብበናል፡፡ ጉራጌ የክርስትናውንም ሆነ የእስልምናውን ሀይማኖት ከመቀበሉ በፊት ጠንከር ያለ

ፈሪሀ እግዚአብሔር እንደነበረውና በሀይማኖት አባቶች ቃለ እግዚአብሔር ባይነበብለትም በህገ-ልቦናው ጥሩውን ጥሩ፣

መጥፎውን መጥፎ፣ደጉን ደግ ከማለት የቦዘነበት ዘመን ስላልነበረ በእኛና በእናንተ ወይም በእኔና በአንተ(በአንቺ) መሀል

ሰማይና ምድር ምስክር ናቸው ብሎ ጉዳ መያያዝ በጉራጌ ህይወት ረዥም ዘመን ወደ ኋላ እንዳስቆጠረ የብሔሩ አባቶች

ይናገራሉ፡፡ የጉራጌ አባቶች ጉዳ ሲያያዙ "አፈር ኧቶንኸ እግዘር ዳኘንኸ" በአማርኛው "መሬት ምስክር ነህ እግዚአብሔር ዳኛ

ነህ" በማለት እንደሆነ በአባቶች አንደበት ይነገራል፡፡

ጉዳ እንዴትና መቼ እንደተጀመረ የብሔሩ ተወላጆች ሲናገሩ እንዲህ ይሉናል ከአያሌ አመታት በፊት አንችምና ውርትም

ወይም አንጀልና ቡልትም የሚባሉ ሁለት ጓደኛሞች ላይከዳዱ ቃል ይግባባሉ፡፡ ሁለቱም "እኔ ብከዳህ እንዲህና እንዲያ

ይሁንብኝ አንተ ብትከዳኝ እንዲህና እንዲያ ይሁንብህ" ብለው ከተማማሉ በኋላ "የለም ይህ በቂ አይሆንም አንተ ብትከዳኝ

አንጀትህ እኔ ብከዳህ አንጀቴ ይጎተት" ተባብለው ቃል ይግባቡና ጉዳ ተያይዘው ሲያበቁ ውርትም የሁለቱንም ሀብት ተሸክሞ

መንገዳቸውን ይቀጥላሉ፡፡ የተወሰነ መንገድ ከተጓዙ በኋላ ውርትም ጓደኛውን ሊከዳውና የተሸከመውን ንብረት የግሉ ብቻ

ሊያደርግ ይፈልጋል፡፡ እናም "አንተ እየሄድክ ጠብቀኝ እኔ ልፀዳዳ" ይለውና ወደ ጫካ ይገባል፡፡ አንችም የተነገረውን አምኖ

ጉዞውን ወደፊት ይቀጥላል፡፡ ርቆ ከሄደ በኋላ መለስ ብሎ ቢያይ ውርትምን ስላጣው "ምን አግኝቶት ይሆን?" የሚል ሀሳብ

ይገባውና ከርሱ ተነጥሎ ለመጸዳዳት የቀረውን ጓደኛውን ፍለጋ ወደኋላ ይመለሳል፡፡ በዚሁ ፍለጋ ላይ እያለ ውርትም

እንደሚፀዳዳ ሰው ሆኖ ለማስመሰል በተቀመጠበት ቦታ አንጀቱ ወጥቶ ያገኘዋል፡፡ ባየው ድንገተኛ ክስተት ይደናገጣል፡፡

"ጓደኛዬ አንችም ልከዳህ ወስኜ በፈጸምኩት ስህተት የተነሳ እነሆ የተማማልነው መሀላ ደረሰብኝ" ብሎ ውርትም ቀደም ሲል

ከጓደኛው አንችም ጋር ላለመከዳዳት የተግባቡትን ቃል-ኪዳን በማፈረሱ የደረሰበትን መከራ በፀፀት እንዳስታወሰውና

ከዚህም የአንችምና የውርትም መሃላ በኋላ ለጉዳ ምክንያት ሆኖ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ አንዳንድ አባቶች ላይከዳዱ ቃል

የተግባቡት የሁለቱ ሰዎች ስም ዘኘራጐና ኤበሮ ናቸው ይላሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ግን በመጀመሪያዎቹ ስሞች ይስማማሉ፡፡ ምንም

እንኳ ጉዳ አጀማመሩ በዚህ ዓይነት መልኩ ቢሆንም ጉዳ ማፍረስ የሚያስከፍለው ዋጋ እጅግ አደገኛና አስፈሪም እንደሆነ

አንጋፋዎቹ የብሔሩ ተወላጆች ይናገራሉ፡፡ ምክንያቱም ጉዳ የማፍረስ መዘዝ የሚያስከትለው ጦሱ ለልጅ ልጅ በአጠቃላይ

ለዘር ማንዘር ስለሚተርፍ በጉራጌ ብሔር ዘንድ ጉዳ ይፈራል፡፡ ይከበራልም፡፡

 

ምንጭ፡-አዲስ አድማስ ጋዜጣ