Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

’አቦ ሸማኔ’’ የተባለው የነብር ዝርያ በአገራችን በተለምዶ’’አቦ ሸማ??

ቅንጭብጭ እውነታዎች

 

ከእንስሳት ዓለም

አቦ ሸ

‘’አቦ ሸማኔ’’ የተባለው የነብር ዝርያ በአገራችን በተለምዶ’’አቦ ሸማኔ’’ ተብሎ ይጠራል፡፡ ትርጓሜውም የሸማኔ ጭፍራ እንደማለት ነው፡፡ ይህ የዱር እንስሳ በፍጥነቱ ተወዳዳሪ የለውም፡፡ በስልትና በጥንቃቄ ከማደኑ ባሻገር በሰዓት ከዘጠና ስድስት ኪሎ ሜትር በላይ ለመሮጥ ይችላል፡፡

ሲ ሆርስ

ፈረንጆቹ   ‘’ሲ ሆርስ ‘’ ብለው የሚጠሩት የባህር እንስሳ በአንድ ጊዜ በሁለቱም አይኖቹ የተለያዩ ነገሮችን መቃኘት ይችላል፡፡ ሴቷ ሲ ሆርስ እንቁላሏን የምትጥለው ወንዱ ሆድ ላይ በሚገኘው ከረጢት ውስጥ ሲሆን ወንዱ እንቁላሉን አዳብሮ ለተወሰነ ጊዜያት ካቀፈ በኃላ ወቅቱ ሲደርስ ይየፈለፍላል፡፡ ከሁሉም የሚያስገርመው  ግን ወንዱ ሲ ሆርስ አርግዞ መውለድ መቻሉ ነው፡፡

ፖርፖይዝ

ፖርፖይዝ የተባለው የባህር እንስሳ ልክ እንደ በቀቀን ወፍ የሰዎችን ድምፅ ማስመሰል ይችላል፡፡ ይህ እንስሳ ድምፅን አስመስሎ ከመድገም ባሻገር  የሰዎችን ሳቅ ተከትሎ በአግባብ ለመሳቅ ይችላል፡፡

ሎሚንግ

ሎሚንጎች በአርክቲክ አካባቢ ከሚኖሩ   እንስሳት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ አይጥ መሰል እንሰሳት ከብዛታቸው የተነሳ በአንድ አካባቢ ተጨናንቀው ከብዛታቸው የተነሳ በአንድ አካባቢ ተጨናንቀው መኖርን ይመርጣሉ፡፡ ይሁን እንጂ ቁጥራቸው ሲበራከቱና መፈናፈኛ ሲያጡ ብዛታቸውን ለመቀነስ የሚወስዱት አማራጭ ራሳቸውን ባህር ውስጥ በማስመጥ በፈቃዳቸው ህይወታቸውን ማጥፋት ነው፡፡

የዓለማችን ከተሞች

ካናዳ-በካናዳ ከሶስት ሚሊዮን የሚልቁ ሀይቆች ይገኛሉ፡፡ ሃምሳ በመቶ የሚሆኑት ካናዳውያንም የተማሩና ከከፍተኛ ተቋማት የተመረቁ ናቸው፡፡ ካናዳን በተማረ የሰው ኃይል ቁጥር እስራኤልና ጃፓን ይከተሏታል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ-ሳዑዲ አረቢያ ምንም ወንዝ የላትም፡፡ ይህቺ ወንዝ ናፋቂ አገር አብዛኛውን ውሃ የምታገኘው ከከርሰ ምድር ነው፡፡

መንጎልያ፡- በመንጎልያውያን ዘንድ ጉርብትና እንደ ብርቅ ይቆጠራል፡፡ ለምን? ቢሉ እንደ በአንድ  ስኩዌር ማይል ስፋት አራት ሰው ብቻ ስለሚኖር፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በሆንግ ኮንግ ያለው የጉርብትና ቅርበት ግን በአንድ ስኩየር ማይል ስፋት ሶስት መቶ አርባ ሺ ነዋሪ የሚሸፍን ነው፡፡

ገኒ- በጊኒ ብሄራዊ የመግባቢያ ቋንቋ እንግሊዝኛ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአገሪቱ እንግሊዝኛን የሚጠቀመው ህዝብ ብዛት ከሁለት በመቶ አይበልጥም፡፡ አስገራሚው ነገር ደግሞ በጊኒ 820 ቋንቋዎች መነገራቸው ሲሆን ይህን በዓለም ላይ ከሚነገሩት ቋንቋዎች አስራ ሁለት በመቶውን የሚሸፍን ነው፡፡

ምንጭ፡-አድማስ ጋዜጣ