Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ሳያገቡ መኖር ለሰው የሚሰጠው የራሱ የሆኑ መልካም ዕድሎች አሉ፡፡

ከማግባትና ሳያገቡ ከመኖር የትኛው ይሻላል?

 Image result for ከማግባትና ሳያገቡ ከመኖር

 

ሳያገቡ መኖር ለሰው የሚሰጠው የራሱ የሆኑ መልካም ዕድሎች አሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ጋብቻ ሳይመሠርቱ መኖር ነፃነትን ይሰጣል፡፡

 

ሳያገቡ መኖር ለሰው የሚሰጠው የራሱ የሆኑ መልካም ዕድሎች አሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ጋብቻ ሳይመሠርቱ መኖር ነፃነትን ይሰጣል፡፡ ያላገቡ ሰዎች በህይወታቸው መስራት የሚፈልጉትን ነገር ለማከናወን ጊዜ አላቸው፡፡ በግል በመኖር በህይወት ዘመን ማከናወን በሚፈለገው ዓላማ ላይ ሙሉ ትኩረት ለመስጠት ያለማግባት ይመረጣል፡፡ ሙሉ የህይወት ዘመንን መስዋዕትነት የሚጠይቅ ሥራ ወይም ተልዕኮ ካለ በሙሉ ልብ እዚያ ላይ ለመስራት ከትዳር ጉዳይ ነፃ መሆን ይመረጣል፡፡ ለተለየ የህይወት ጥሪ ምላሽ በመስጠት ፍሬያማ ለመሆን ያለማግባት ይሻላል፡፡

 

የግለሰቦች ምርጫ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ማግባት ካለማግባት የበለጠ ጥቅም አለው፡፡ አንድ ሰው ዕድሜው ለትዳር ከደረሰ በኋላ ትዳር መስርቶ ለመኖር ቢወስንና ቢያገባ የሚያገኛቸው ጥቅሞች በርካታ ናቸው፡፡ ከእነዚህም ጥቅሞች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

 

1. ለወሲብ እርካታ

 

የሰዎች የወሲብ ግንኙነት እንደሚያምኑት እሴት የተለያየ ቢሆንም ከፍተኛ የሆነ የወሲብ እርካታ የሚገኘው በጋብቻ በተጣመሩ ጥንዶች መካከል ሲፈጸም ነው፡፡ ሳይጋቡ ከሚፈጸም ወሲብ ይልቅ በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የሚኖር የወሲብ እርካታ የበለጠ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ በዘላቂ የጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የሚፈጸም ወሲብ ከስሜትም አልፎ ሁለንተናዊ ህይወትን የማርካት ኃይል አለው፡፡ ምክንያቱም ወሲብ የግንኙነቱ መገለጫ ተደርጎ ስለሚታሰብና በባልና ሚስት መካከልም የመተማመኑና የመተዋወቁም መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ያገቡ ሰዎች ሁሉ መልካምና አርኪ የወሲብ ግንኙነት ይኖራቸዋል ማለት አይደለም፡፡ መልካም ወሲብ ትምህርት፣ ክህሎት፣ መሰጠት፣ መተማመንና ግልጽነትን ስለሚጠይቅ በማግባት ብቻ የሚገኝ ውጤት አለመሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

 

2. ለሁለንተናዊ ጤና

 

ማግባት ለአካላዊና የስነ-ልቦናዊ ጤንነት አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው፡፡ በመልካም የጋብቻ ግንኙነት ውስጥ በጥንዶች መካከል ሁሉ ነገር መደጋገፍ ስለሚኖር አንዱ ብቻውን ከሚጨነቅ ለሌላው ጭንቀቱን ያጋራል፡፡ የጭንቀት መቀነስ ደግሞ ለስነ-ልቦና ጤንነት እንዲሁም ሰውነት በሽታን መቋቋም የሚያስችል ኃይል እንዲኖረው ያግዛል፡፡ በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ጥንዶች ካላገቡ ሰዎች ይልቅ የሚኖራቸው የህይወት ዘይቤ ለምሳሌ አመጋገብ ስርዓት ያለውና በጥንቃቄ የሚሠራ ይሆናል፡፡ በአብዛኛው እቤት የሚዘጋጅ ምግብ በመሆኑ የምግቡን ዓይነትና አሠራር ለጤንነት በሚያመች መንገድ የማዘጋጀት ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ማግባት ሰዎች ስርዓት ያለው የህይወት ዘይቤ እንዲከተሉ ይረዳል፡፡ ያገቡ ሰዎች ለአልኮል መጠጥና ለሌሎች ሱስ አምጪ ነገሮች የመጋለጣቸው ዕድል ካላገቡት ሰዎች ያነሰ ነው፡፡ ያገቡ ሰዎች ከኃላፊነትና ተጠያቂነት የተነሣ ለአልኮል፣ ለሲጋራና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች በቀላሉ የተጋለጡ አይሆኑም፡፡ ያገቡ ሰዎች ካላገቡ ሰዎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ፡፡ ያላገቡ ሰዎች ህይወታቸውን ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮችን የማድረግ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ስለዚህ ቶሎ ይሞታሉ፡፡

 

3. ልጆች ወልዶ ለማሳደግ

 

ሰዎች ሳያገቡ ልጆችን መውለድ እንደሚችሉ የታወቀ ነው፡፡ ሆኖም ሳያገቡ ልጆችን መውለድ ቢቻልም ነጠላ ሆኖ ልጆችን ማሳደግ አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ በልጆቹ የስነ-ልቦና ህይወት ላይ የሚኖረው ውጤት አሉታዊ ነው፡፡ ልጆች በሁለንተናዊ ህይወታቸው በመልካም ሁኔታ ለማደግ ምቹ የሆነው አውድ አባትና እናት ተጋብተው በአንድ ላይ ሲኖሩ ነው፡፡

 

4. ሃብት ለማፍራት

 

አንዳንድ ሰዎች ሃብት ለማፍራት ሳያገቡ መኖር እንደሚሻል ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ሃብት ለማፍራት ማግባት የተሻለ ዕድል ይሰጣል፡፡ አንድ ሰው ለብቻው ከሚሠራ ይልቅ ባልና ሚስት አንድ ላይ ሆነው ኃይላቸውን፣ ዕውቀታቸውን፣ ልምዳቸውን፣ ክህሎታቸውን አስተባብረው ቢሰሩ የበለጠ ውጤታማ መሆን ይችላሉ፡፡ ከአንድ አእምሮ ሁለት አእምሮ የተሻለ ውጤት ይኖሯል፡፡ በእርግጥ በዓለም ላይ የታወቁ ሃብታም ሰዎችን ስንመለከት ብዙዎቹ ያገቡና ትዳር ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ማግባት ለብልጽግና አስተዋጽኦ አለው፡፡ ከደመወዝም አንፃር ሲታይ ያገቡ ሰዎች ካላገቡ ሰዎች በላይ አማካይ ደመወዝ እንደሚያገኙ በአንዳንድ ስፍራዎች የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

 

5. ማኅበራዊ ከበሬታን ያስገኛል

 

በአብዛኛው ማግባት የተጋቢዎችን ማኅበራዊ ከበሬታ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በኅብረተሰብ ውስጥ ላገቡ ሰዎች የሚሰጥ አክብሮት ላለገቡ ሰዎች ከሚሰጠው ይበልጣል፡፡ ያገቡ ሰዎች ኃላፊነት መሸከም እንደሚችሉም ይታሰባል፡፡ በአንዳንድ ስፍራዎች በኅብረተሰቡ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ኃላፊነቶችን ለመቀበል ጋብቻ እንደ አንድ መስፈርት የሚታይበት ሁኔታ አለ፡፡

 

አጭር ምክር

ስለጋብቻ ጥቅም አንጠራጠር፣ ነገር ግን ለጋብቻ የምንሆን ዓይነት ሰው መሆናችንን እንፈትሽ፡፡

ጋብቻ ተሰርቶ አይጠብቀንም፤ እኛው ራሳችን ሰርተን የምናሳምረው ቤት ነው፡፡ ስለዚህ ኃላፊነታችንን ለመወጣት እንዘጋጅ፡፡ 

ለምን ማግባት እንደምንፈልግ እንወቅ፡፡ ይህ ከጋብቻ ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዳንጠብቅ ይረዳናል፡፡

በጋብቻ ውስጥ የማይገኘውን ነገር ጠብቀን በኋላ እንዳንጸጸት ከወዲሁ የምንጠብቀውን ነገር እናስተካክል፡፡

ዕድሜ ልካችንን ሳናገባ ለመኖር ካልወሰንን በስተቀር በተገቢው ዕድሜ ለማግባት እናቅድ፡፡ ሁሉም በጊዜው ሲሆን ያምራል፡፡

 

ምንጭ :  ZePsychologist face book