Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌ?

ይሉኝታ

ይሉኝታ ምንድን ነው?

የሰዎችን ደስታና ሃዘን መካፈል፤ ለሰዎች በችግራቸው ጊዜ ያአቅምን ማድረግ አብዛኞቻችን ያስደስተናል፤  እርካታም ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴ ሰዎች በይሉኝታ ሲታሰሩና ከፍላጎታቸው እና ከአቅማቸው በላይ ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውን፤ ሃሳባቸውን ለሌሎች ሰዎች ደስታ ሲያውሉ ይታያል፡፡ ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን  ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት፡፡

 

የይሉኝታ መንስኤዎች

ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት

በራስ መተማመን ማነስ

ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ

የውስጥ መረጋጋት ከሌለን

አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ

ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡-በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ

 

ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች መገለጫ ባህሪያት

ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ ጋር ሁሌም መስማማት እንዳለብን ሲሰማን

ሰዎችን ሊያስደስታቸውና ሊያስከፋቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸው ነገሮች ላይ በብዛት መጨነቅ

ሳናምንበትም እንኳ ቢሆን ስለሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገር ሲወራ አብሮ ማማት

ሰዎች ስለኛ ምን ሊያስቡ እና ምን ሊናገሩ እንደሚችሉ ማሰብና መጨነቅ

የሃሰብ ልዩነቶችንና ግጭቶችን ተጋፍጦ በሃሳብ ከመርታት ይልቅ መሸሽ፤ ሃሳቦች ሳይብላሉ ማቋረጥ

ሰዎች በውይይት መሃል የተለየ ሃሳብ ሲያነሱ ከሃሳቡ ይልቅ ሰዎች ላይ ማተኮር

ሃሳባችን ከማንጸባረቅና ላመንበት ነገር ከመቆም ይልቅ ለቡድን ተጽእኖ እጅ መስጠት

ከደንብና መመሪያ መከበር ይልቅ በሰዎች ለመሞገስና ለመከበር ትኩረት መስጠት

የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍለንም ሌሎችን ላለመሳከፋትና ላለማበሳጨት መጣር

አይሆንም የማለት ድፍረት ማጣት፤ ለሁሉም ነገር እሺን ማስቀደም

 

ይሉኝታ የሚያስከትለው ጉዳት

በራሳችን ህይወት ደስተኞች አንሆነም፤ ስልቹዎች እንሆናለን

ከሰዎች የምንጠብቀውን ማበረታትና ተቀባይነት ሁሌም ላናገኝ እንችላለን

ራስ ወዳድና በሌሎች ሰዎች መጠቀም ለሚፈልጉ ሰዎች ተጋላጭ እንሆናለን

ሁሉም ቦታ ለመገኘት ስንጥር በስራችን ውጤታማ አንሆንም

ይሉኝታን ለመቀነስ የሚረዱ መንገዶች

ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት

ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?

በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ

አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ

በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ

ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር

ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር

ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል

 

ምንጭ :  ZePsychologist