Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174
Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176
Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216
Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218
አፍሪካ ጎሽ ሊጎዳው የሞከረንና የጎዳውን ሰው ከዓመት በኋላም ቢሆን የማስ
የአፍሪካ ጎሽ
የአፍሪካ ጎሽ ሊጎዳው የሞከረንና የጎዳውን ሰው ከዓመት በኋላም ቢሆን የማስታወስ ችሎታ አለው፡፡ ይቅርታ የማድረግ ባህሪ ስለሌለውም ባገኘው አጋጣሚ የጎዳውን ሰው ካገኘ ብድሩን ይመልሳል፡፡ ከበሬ፣ አራት እጥፍ ጉልበት ያለው የአፍሪካ ጎሽ፣ ጥልቅ በሆነ ውኃ ውስጥ በመዋኘት ችሎታውም ይታወቃል፡፡
ሳር ከሚመገቡ እንስሳት የሚመደበው ጎሽ፣ ረግረጋማና ለም በሆኑ ቦታዎች መኖርን ይመርጣል፡፡ ተራራማና በአረንጓዴ ተክሎች በተከበቡ ሥፍራዎችም ይኖራል፡፡ የመኖር ዕድሜ ጣሪያው እስከ 25 ዓመት ሲሆን፣ ክብደቱም ከ700 ኪሎ ግራም እስከ 1200 ኪሎ ግራም ይደርሳል፡፡
ከላም ዝርያዎች የሚመደቡ ሲሆን፣ ወተትም ይሰጣሉ፡፡ አንድ ጎሽ ባንዴ የምትወልደው አንድ ሲሆን፣ መንታ የመውለድ ዕድሏ አናሳ ነው፡፡ መንታ ሆነው ከተወለዱም የማደግ ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡
ምንጭ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ