Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ተመራማሪዎች በስማርት ስልክ አማካኝነት የካንሰር ህመምን የሚለይ መሳሪ??

ተመራማሪዎች በስማርት ስልክ አማካኝነት የካንሰር ህመምን የሚለይ መሳሪያ ሰርተዋል…

 

ተመራማሪዎች በስማርት ስልክ አማካኝነት የካንሰር ህመምን የሚለይ መሳሪያ ሰርተዋል…

 

የዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ካንሰርን በስማርት ስልክ ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ መስረራታቸውን አስታውቀዋል።

ቴክኖሎጂው በስማርት ስልኮች ላይ የሚገጠም ስፔክቶሜትሩ የሚባል ሲሆን፥ ሰዎች በካንሰር መያዛቸውን በቶሎ በመለየት ህክምናውን ቶሎ እንዲያገኙ ለማድረግ ያስችል ነው የተባለው።

በአንሰተኛ ወጪ እንደተሰራ የተነገረው የስማርት ስልክ መመርመሪያው፥ በቀላሉ ይዞ ለመንቀሳቀስ እና ጥራት ያለው የቤተ ሙከራ ውጤቶችን በፍጥነት ያቀርባል ተብሏል።

መሳሪያውን የሰሩት ተመራማሪዎች እንደሚናገሩት፥ አዲሱ ቴክኖሎጂ የሰዎችን የኢንተርሌኩይን 6 መጠንን ይለካል ያሉ ሲሆን፥ ይህም ለጡት፣ ለፕሮስቴት፣ ለጉበት እና ሌሎች የካንሰር አይነቶች መንስኤ የሆኑትን ለመለየት ያስችላል።

ስማርት ስልኩ ላይ የሚገጠመው ስፔክቶሜትር በሰዎች ውስጥ ያለውን የኬሚካል አይነት እና መጠን ለመለካት የሚያስችል መሆኑንም የፈጠራው ባለቤቶች ይናገራሉ።

አዲሱ መሳሪያ በሁሉም ስፍራ አስፈላጊውን ህክምና በቀላሉ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑንም የጥናት ቡድኑ አስረድቷል።

አሁን የሰሩት የስማርት ስልክ ስፔክቶሜትር በአይፎን 5 ላይ የሚሰራ ሲሆን፥ 99 በመቶ ውጤታማ መሆኑንም ይናገራሉ።

በአሁኑ ጊዜ ስማርት ስልኮቹን በመጠቀም ምርመራ እያደረጉ መሆኑን የሚናገሩት ተመራማሪዎቹ፥ ቴክኖሎጂው በሁሉም አይነት ስልኮች ላይ እንዲሰራ የማሻሻያ ስራ መጀመራቸውንም አስታውቀዋል።

 

ምንጭ፦ www.upi.com/Health