Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ከመልክና ቁመናሽ ጋር በተያያዘ ለመለወጥ በጣም የምትፈልጊው የትኛውን

ስለ መልኬ ከልክ በላይ እየተጨነቅሁ ነው?

 

 

 ጥያቄዎች፦ ከልክ በላይ እየተጨነቅሁ ነው?

 መልኬን የማልወደው ለምንድን ነው?

 መልኬን ለማሻሻል ብሞክር ይሻል ይሆን?

 ከሁሉ የላቀው ማሻሻያ!

ጥያቄዎች፦ ከልክ በላይ እየተጨነቅሁ ነው?

ስሜትሽን ጥሩ አድርጎ የሚገልጸው የትኛው ዓረፍተ ነገር ነው? *

^ አን.9 በዚህ ርዕስ ውስጥ የቀረቡት ነጥቦች ለሁለቱም ፆታዎች ይሠራሉ።

 

መልኬን ጨርሶ አልወደውም።

መልኬን አንዳንድ ጊዜ እወደዋለሁ።

በመልኬ ሁልጊዜም ደስተኛ ነኝ።

ከመልክና ቁመናሽ ጋር በተያያዘ ለመለወጥ በጣም የምትፈልጊው የትኛውን ነው?

ቁመት

ክብደት

የሰውነት ቅርጽ

ፀጉር

የቆዳ ቀለም

ጡንቻ

ሌላ

የሚከተለውን ዓረፍተ ነገር አሟዪ።

በቁመናዬ የማልደሰተው . . .

ክብደቴን ስመዘን ነው።

በመስታወት ራሴን ስመለከት ነው።

ራሴን ከሌሎች (ከጓደኞቼ፣ ከሞዴሎች፣ ከፊልም ተዋንያን) ጋር ሳወዳድር ነው።

የሚከተለውን ዓረፍተ ነገር አሟዪ።

ክብደቴን የምመዘነው . . .

በየቀኑ ነው።

በየሳምንቱ ነው።

አልፎ አልፎ ነው።

ስሜትሽን ጥሩ አድርጎ የሚገልጸው የትኛው ሐሳብ ነው?

መልክና ቁመናዬን አልወደውም። (ምሳሌ፦ “በመስተዋት ራሴን በተመለከትሁ ቁጥር በጣም ወፍራም እና አስቀያሚ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ክብደት ለመቀነስ ስል ራሴን በረሃብ የቀጣሁባቸው ጊዜያት አሉ።”—ሰሪና)

ሚዛናዊ አመለካከት አለኝ። (ምሳሌ፦ “ከመልክና ቁመናችን ጋር በተያያዘ የማንወደው ነገር መኖሩ አይቀርም፤ ይሁንና አንዳንድ ነገሮችን ልንቀበላቸው ይገባል። ልንለውጠው ስለማንችለው ነገር መጨነቅ ምንም ጥቅም የለውም።”—ናታንያ)

 

 ‘ከሚገባው በላይ ስለ ራሳችን ማሰብ’ እንደሌለብን ያሳስበናል።ከዚህ አንጻር በተወሰነ መጠን ስለ ራስ ማሰብ ተገቢ እንዲያውም አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ጥርስሽን መቦረሽሽ ወይም ንጽሕናሽን መጠበቅሽ ተገቢ ነው።

 

 ይሁንና ስለ መልክሽ ባሰብሽ ቁጥር መጥፎ የሚሰማሽ አልፎ ተርፎም ነገሩ ከመጠን በላይ የሚያስጨንቅሽ ቢሆንስ? ይህ ከሆነ እንደሚከተለው ያለ ጥያቄ ሊፈጠርብሽ ይችላል፦

 

‘መልኬን የማልወደው ለምንድን ነው?’

የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

 

የመገናኛ ብዙኃን ተጽዕኖ። “ወጣቶች ነጋ ጠባ የሚያዩት ነገር፣ ሁልጊዜም በጣም ቀጭንና ውብ መሆን እንዳለባቸው እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ልክ እንደሚባለው በጣም ቆንጆ ካልሆንን ስለ ራሳችን መጥፎ ይሰማናል።”—ኬሊ

የወላጆች ተጽዕኖ። “አንዲት እናት የመልኳ ጉዳይ ከመጠን በላይ የሚያሳስባት ከሆነ ብዙውን ጊዜ ልጇም ተመሳሳይ አመለካከት እንደሚኖራት አስተውያለሁ። ከአባቶችና ከወንዶች ልጆች ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።”—ሪታ

ራስን ዝቅ አድርጎ መመልከት። “የመልካቸው ጉዳይ ከመጠን በላይ የሚያስጨንቃቸው ሰዎች፣ ሌሎች ሁልጊዜ መልካቸውን እንዲያደንቁላቸው ይፈልጋሉ። ከእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር መሆን ይሰለቻል።”—ዣን

 መልክሽን እንዳትወጂው ያደረገሽ ምክንያት የትኛውም ቢሆን፣ እንደሚከተለው ብለሽ ታስቢ ይሆናል፦

 

‘መልኬን ለማሻሻል ብሞክር ይሻል ይሆን?’

እስቲ አንዳንድ እኩዮችሽ ምን እንደሚሉ ተመልከቺ።

 

 

“ከመልካችን ጋር በተያያዘ የማንወዳቸውን ነገሮች መለወጥ የምንችለው ሁልጊዜ አይደለም፤ ስለዚህ አንዳንድ ጉድለቶቻችንን ተቀብሎ መኖሩ የተሻለ ነው። እኛ እንዲህ ካደረግን ሌሎች ሰዎች ያን ያህል ላያስተውሉት ይችላሉ።”—ሮሪ

 

“ጤነኛ ለመሆን የተቻላችሁን ጥረት አድርጉ። ጤናማ መሆን በራሱ ጥሩ መልክ እንዲኖራችሁ ያደርጋል። ደግሞም አንድ ሰው መልካችሁን እንጂ ማንነታችሁን ማድነቅ ካልቻለ ያ ግለሰብ ጥሩ ጓደኛ አይደለም።”—ኦሊቪያ

ዋናው ነጥብ፦ ጥሩ አቋም እንዲኖርሽ ማድረግ የምትችዪውን አድርጊ። ስለቀረው ነገር አትጨነቂ። ስለ መልክ ከሚገባው በላይ መጨነቅ አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

 

 በሌላ በኩል ግን ኤሪን የተባለች ወጣት እንደተናገረችው ስለ መልክ ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት መያዝ ለራስሽ ያልተዛባ አመለካከት እንዲኖርሽ ይረዳሻል። ኤሪን እንዲህ ብላለች፦ “ስለ መልኬ የማልወዳቸው ነገሮች እንዳሉ የታወቀ ነው፤ ያም ቢሆን ስለ ራሴ መጥፎ የሚሰማኝ በእነዚህ ነገሮች ላይ ትኩረት ሳደርግ ብቻ እንደሆነ አስተውያለሁ። አዘውትሬ ስፖርት እሠራለሁ፤ እንዲሁም ጥሩ የአመጋገብ ልማድ እንዲኖረኝ እጥራለሁ። ይህን ሳደርግ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ይስተካከላሉ።”

 

ከሁሉ የላቀው ማሻሻያ!

ስለ መልክሽ ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት ስታዳብሪ ስለ ራስሽ ጥሩ ስሜት ይኖርሻል፤ ይህ ደግሞ ከውጭ የሚታይ ይሆናል።  በዚህ ረገድ ሊረዳሽ ይችላል። የሚከተሉትን ነገሮች ለማድረግ እንድትሞክሪ ያበረታታሻል፦

 

ባለሽ መርካት። “ትርፍ ነገር ለማግኘት ከመቅበዝበዝ ይልቅ፥ ባለህ ነገር መደሰት የተሻለ ነው።

ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ስፖርት መሥራት። “የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጥቂቱ ይጠቅማል።

ውስጣዊ ውበት ማዳበር። “ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል።

 

“ስለ ራሳችን ያለን አመለካከት በፊታችን ላይ ይነበባል። አንድ ሰው ባለው የሚረካ ከሆነ ሌሎች ይህን ማስተዋል የሚችሉ ከመሆኑም ሌላ ወደ እሱ ለመቅረብ ይነሳሳሉ።”—ዛራ

 

“ውበት፣ ቶሎ ዓይን ውስጥ እንድንገባ ሊያደርገን ይችላል። ከሰዎች አእምሮ የማይጠፋው ግን ማንነታችን እና መልካም ባሕርያችን ነው።”—ፊሊስያ

ምንጭ፡- የወጣቶች ጥያቄ