Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ማንጎ እጅግ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ሲኖሩት፥ በዋናነት ግን የሚከተሉት?

ማንጎ የፍራፍሬዎች ንጉስ

 

Image result for ማንጎ

 

የፍራፍሬዎች ሁሉ ንጉስ እየተባለ የሚሞካሸው ማንጎ እጅግ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ሲኖሩት፥ በዋናነት ግን የሚከተሉትን የጤና በረከቶች ይዟል።

1. ካንሰርን ይከላከላል፣

ጥናቶች እንደሚሳዩት ከሆነ ማንጎን መመገብ ከአንጀት፣ ከጡት፣ከደም እና ከፕሮስቴት ካንሰር ለመጠበቅ ይረዳል።

2. የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል፣

ማንጎ የኮሌስቴሮል መጠንን መቀነስ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ በከፍተኛ ሁኔታ ይዟል።

3. ለቆዳ ጤንነት ተመራጭ ነው፣

ማንጎን በመመገብም ሆነ ፊትን በመቅባት የቆዳዎን ጤንነት ማሻሻል ይችላሉ።

4.የኩላሊት ጠጠርን ይቀንሳል፣

ማንጎን አዘውትሮ መመገብ ጣፋጭ ጣዕምን ከማግኘት ባላፈ በኩላሊታችን ውስጥ ጠጠር እንዳይፈጠር ማድረግ ይቻላል።

5. ለአይን ጤንነት ፍቱን ነው፣

ማንጎ ቫይታሚን ኤ በውስጡ ስለሚይዝ የአይን የማየት ጥራትን ይጨምራል።

6.የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል፣

እንደ ፓፓዬ ሁሉ ማንጎም የምግብ መፈጨትን ስርአት ያፋጥናል።

7.የማስታወስ ችሎታችን ለማሳደግ፣

ማንጎ ግሉታሚን የተሰኘ እና የማስታወስ ችሎታችንን የሚያሳድግ እንዲሁም አንድን ስራ በትኩረት ለመስራት የሚያስችል ንጥረ ነገርን አምቆ ይዟል በውስጡ።

በተለይም ህፃናት እና ታዳጊዎች አዘውትረው ቢመገቡት በፈተና ወቅት ትኩረታቸውን ለመሰብሰብ በእጅጉ ይረዳቸዋል።

 

8.በሽታ የመከላከል አቅማችንን ያጎለብታል፣

ቫይታሚን እና ቫይታሚን በተጨማሪ ሌሎች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች በሽታን የመከላከል አቅማችንን ያዳብራሉ።

9.በሰውነታችን የስኳር መጠንን ለማስተካከል፣

የማንጎ ፍሬው ብቻ ሳይሆን ቅጠሉም ለጤና ጠቃሚ ነው።

የስኳር ህመምተኞች የሆንን ምሽት ላይ ከአምስት እስከ ስድስት የሚሆኑ የማንጎ ቅጠሎችን በመቀቀል እና በመጭመቅ ዘወትር ጠዋት ጠዋት ለተወሰኑ ቀናት ከአንድ ብርጭቆ ያላነሰ ብንጠጣ በሰውነታችን የስኳር መጠንን ለማስተካከል ይረዳናል።

ምንጭ፦ http://healthimpactnews.com