Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

በእርግዝና ወቅት የማይመከሩ ምግቦችና መጠጦች!!

እርግዝና እና አመጋገብ


1. ጥሬ ወይም በከፊል የበሰለ እንቁላል።
እርጉዝ ሴቶች በፍጽም ጥሬ ወይም በከፊል የበሰለ እንቁላል መመገብ የለባቸውም። ጥሬ እንቁላል ለሳልሞኔላ ኢንፌክሽን አይነተኛ መነሻ ሲሆኑ ማስመለስና ተቅማጥ ያስከትላል ይህም የልጅዎን ጤንነት ይጐዳል። እንቁላል የፕሮቲን፣ ቫይታሚንና ሚኔራሎች ጥሩ መገኛ ነው ስለዚህ እንቁላል ሲመገቡ በሚገባ መብሰላቸውን ያረጋግጡ።


2. አልኮል መጠጦች።
እርጉዝ ሴቶች በሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት ምክንያት አልኮል ከመጠጣት መታቀብ አለባቸው። አልኮል መጠጣት የሚከተሉት ነገሮች የመከሰት ዕድላቸው እንዲጨምር ያደርጋል፦ የህፃኑ ዕድገት ችግር፣ ማስጨንገፍ (ማስወረድ)ና ፌታል አልኮሊክ ሲንድረም።


3. ቡና መጠጣት።
በእርግዝና ወቅት የምትጠጭውን የቡና ብዛት መመጠን አለብሽ። ከፍተኛ የካፌይን መጠን ሲወሰድ አነቃቂ ነው ይህም የህፃኑን የልብ ምት መጠን ያስተጓጉላል።
በተጨማሪም ካፌይን ዝቅተኛ ክብደት ያለው ህፃን የመውለድና የማስጨንገፍ ዕድልን ይጨምራል። በብዛት ከተጠቀሙ ደግሞ ድርቀትን ያስከትላል።


4. ከፍተኛ የሜርኩሪ መጠን ያለው አሳ።
አሳ ጤናማ የኦሜጋ - 3 ፋቲ አሲድ መገኛ ነው ነገር ግን በእርግዝና ወቅት የሜርኩሪ ይዘታቸው ከፍ ያሉ አሳዎችን ከመመገብ መቆጠብ አለባቸው። ከፍተኛ የሜርኩሪ መጠን የህፃኑን የአእምሮ ዕድገትና የነርቭ ሥርዓትን ያስተጓጉላል።


5. ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ ስጋ።
በፍጽም ጥሬ ሥጋ አይመገቡ በተለይ ነፍሰ ጡር ከሆኑ። ጥሬ ወይም በሚገባ ያልበሰለ ሥጋ መመገብ በፓራሳይት አማካይነት የሚከሰተው የቶክሶፕላስሞሲስ ኢንፌክሽን የመያዝ አደጋን ይጨምራል ይህም ገና ያልተወለደ ህፃንን ጤና ይጐዳል።


6. ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ ፓፓያ።
እርጉዝ ከሆኑ ወይም ለማርገዝ ሙከራ እያደረጉ ከሆነ ያልበሰለ ፓፓያ በፍጽም አይመገቡ። ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ ፓፓያ በብዛት መመገብ ልክ እንደ ማስጨንገፊያ መድሃኒቶች በመሆን ይሠራል ስለዚህ ያልበሰለ ፓፓያ በብዛት መመገብ ማስጨንገፍ (ማስወረድ) ያስከትላል።


7. ለስላሳ አይብ።
በእርግዝና ወቅት ለስላሳ አይብ መመገብዎን ያቁሙ። በአብዛኛው እነዚህ ለስላሳ አይቦች የሚዘጋጅት ፓስቸራይዝድ ካልሆነ ወተት ይዘጋጃሉ። እነዚህ ለስላሳ አይቦች በውስጣቸው ሊስቴሪያ የተባለ ባክቴሪያ በውስጣቸው ሊይዙ ይችላሉ ይህ ባክቴሪያ ማስጨንገፍ፣ ያለጊዜው (ያለዕድሜ) ወሊድና በወሊድ ጊዜ ከፍተኛ ህመም እንዲኖር ያደርጋል።


መልካም ጤንነት!!!
ምንጭ፡- ኢትዮ ጤና