Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ያኒ-የበርካታ አፍቃሪያኑን ቀልብ የገዛዉ የሙዚቃ ባለሙያ

ያኒ-የበርካታ አፍቃሪያኑን ቀልብ የገዛዉ የሙዚቃ ባለሙያ

 

Image result for yanni

 

የሙዚቃ ቅንብሩን ለ  .ሰ .መ . ነፍሳቸዉ በሀሴት የምፈነጥዘ በርካቶች ናቸዉ፡፡ ጆሮአቸዉን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቀልባቸዉን ሰጥተዉ እዉነትም ለሙያዉ ነዉ የተፈጠረዉ ምስክርነትም የሚለግሱትን አድናቂዎች ቁጥር መፈለግ ፈታኝ የቤት ስራ ነዉ፡፡በእርግጥም ወደኋላዉ በሚለቀዉ ረዥምና ጥቁር ደማቅ ጸጉር የሚታወቀዉ ሸንቃጣዉ ያኒ  ክሪሶማሊስ ለረቂቅ ሙዚቃ የተፈጠረ ድንቅ ባለሙያ ነዉ፡፡ እራሱ በራሱ የፒያኖ ሙዚቃ ያስተማረዉ ያኒ የሙዚቃዉ ችሎታዉ የሚያስመሰክርለት ትይንት ማቀረብ የጀመረዉ ለቤተሰብ ነበር ያን ግዜ ቋሚ የሚባል የሙዚቃ ትምህርት ስልጠና ያልወሰደዉ ክሪሶማሊስ በቤተሰቦቹ ዘንድ የሚቀርብለት አድናቆት እና ማበረታቻ ይበልጥ እንዲተጋ ምክንያት ሆነዉ፡፡ ያኒ የሙዚቃ ባለሙያም ብቻም አልነበረም፡፡አሪፍ ዋናተኝነቱን ሀገር መስክሮለታል፡፡በሀገሩ በግሪክ 50 ሜትር እርቀት ነፃ ዋና የሀገር ውስጥ ሪከርድ የነበረዉ ያኒ በ18 አመቱ ሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ ተቀላቀለ፡፡ ያኒ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ቢሆንም ቀልብ የነበረዉ ሙዚቃ ላይ ነበርና የሀገር ወስጥ ሙዚቃ ቡድን  የሆነዉ የ ‘chameleon’ ቡድን አባል ሆነ፡፡ ከድራመር ቻርሊ አዳምስ ጋር የተገናኙት እዚህ የሙዚቃ ቡድን ውስጥ ነዉ፡፡

 ያኒ የተቀላቀለዉ ቡድን የሙዚቀ ቡድን በመካከለኛዉ ምዕራብ (mid-west) የሙዚቃ ኮንሰርት ኩዞ አድርጎ በለስ ቃናዉ፡፡ሚኒሶታ፤እዮብ፤ዊስኮንሲን፤ኢሊኖይስ እና ሳዉዝ ዳኮታ እጆቻዉን ዘርግተዉ ተቀብሏቸዉ፡፡ ይህን ጊዜማ ማን  ይቻለዉ? በፍቀር ለወደቀላት ሙዚቃ በለሆሳስ ቃል ገባ፡፡ ቡካዲሽ ሲል አንሾካሾከ፡፡ ይሄዉ ዛሬም ድረስ እያስጠራትና እሱም እየተጣራበት አለ፡፡ በሳይኮሎጂ (ስነልቦና) የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ድግሪዉን ካገኘ በኋላ ሙሉ በሙሉ ፊቱን ወደሙዚቃ ያዞረዉ ያኒ ኮርሳሚሊስ እቅዱን ግብ ለማድለስ ወደ ካሊፎርኒያ ተጓዘ፡፡ እቅዱ በፊል ማጀቢያ የሆነ ሳዉንድትራካችን መስራት ነበር፡፡ በዚህም ያልረካዉ ያኒ እ.አ.እ በ1987 ዓ.ም. ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ማለትም ጆን ተሸ እና ቻርሊ አዳምስ ጋር በመሆን አነስተኛ የሙዚቃ ባንድ አቋቋመ፡፡ ይህ የሙዚቃ ቡድን የያኒን በሙዚቃ አልበም ለማስተዋወቅ በተለያዩ ስፍራዎች በተንቀሳቀሰ ጊዜ ያገኘዉ ተቀባይነት በዋዛ የሚታይ  አልነበረም፡፡ በአልበሙ ውስጥ የተካተቱት ኬይስ ቱ ኢማጂኔሽን፤ አዉት ኦፍ ሳይለንስ እና  ቻሚሊዮን ዴይስ የያኒንም የባንዱንም ስም ክፍ ክፍ አደረጉለት፡፡ የያኒ የመጀመሪያ የግራሚ እጩ አልበም የተለቀቀዉ እ.እ.አ በ1992 ዓ.ም ሲሆን ’Dare to Dream’ የተሰኘዉን ዘፈን መሰረት ያደረገ ነበር፡፡ ‘In my Time’ ለግራሚ የተጨ ሁለተኛ አልበሙ ነዉ፡፡ ከአመት በኋላ ማለትም በ1993 ዓ.ም ሲወጣ መልካም ተቀባይነትን አግኝቶለታል፡፡ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ዕያገኙ የመጡጥን የያኒ ስራዎች በቴሌቭዥን ጣቢያዎች፤ በተለይም ከስፖርታዊ ክንዎኖ ጋር የተያያዙት ዕየተከታተሉ ማቅረብ ጀመሩ፡፡ ሱፐር ቦዉል፤ ዋይድ ወርልድ ኦፍ ስፖርትስ፤ ዩ.ኤስ.ኦፕን፤ቶዉር ዲ ፍራንስ፤ወርልድ ፊገር ስኬቲንግ ሻምፒየን ሸፕ፤ ዘኦሎምፒክ እና ABC Newes  ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡ለያኒ ከፍተኛ ስኬት ካጎናጸፉት ስራዎች መካከል እ.አ.አ. ሴምቴምበር 23 ቀን 1993 ዓ.ም ሁለት ሺ አመት እድሜን ባስቆጠረዉ የግሪክ አቴንስ ወስጥ በሚገኘዉ ሄሮድ አቲክስ ቲያትር አዳራሽ የቀረበዉ ‘Yanni live at the Acropolis  የተሰኘ አልበም የቪዲዮ ስራ ነዉ፡፡ ይህ ስራ በተጠቀሰዉ ግዜ በፊልም መልክ ቢቀርብም ለህዝብ በይፋ የተለቀቀዉ ግን በ1994 ዓ.ም. ነዉ፡፡ በዚህ ዓይነት የስኬት ጎዳና የተጓዘዉ ያኒ ዛሬም ድረስ በበርካታ የሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ተወዳጅ እንደሆነ አለ፡፡

 

ምንጭ፡-ሮዳስ ቅጽ 2. 2002 ዓ.ም