Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

በውስን ሁኔታዎች የንዴት ስሜት መሰማት ተገቢ ነው፡፡

ንዴትን የመቆጣጠር ክህሎት

 

Image result for angry

 

ልጅዎ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ቁጣ ወይም ከሌሎች ጋር ዘወትር የመጋጨትና የመጨቃጨቅ ልማድ አለባቸውን? ንዴት በመሰረቱ የተለመደ፣ ጤናማ ስሜት ቢሆኑም ቅሉ ስር የሰደደ፣ድንፋታና ከቁጥጥር ውጪ የወጣ ንዴት ግን አደገኛ ውጤት ይኖረዋል፡፡ የንዴት ስሜት መጥፎ አይደለም፡፡ በውስን ሁኔታዎች የንዴት ስሜት መሰማት ተገቢ ነው፡፡ ልዩነቱ ልጅዎ ለንዴት ስሜታቸው የሚሰጡት ምላሽ ነው፡፡ብዙ ጊዜ ንዴት የሌሎች ስሜቶች ሽፋን ነው፡፡ ይህም በዋናነት ልጅዎን ወይም ልጅዎችዎን

ለሚያስጨንቃቸው ነገር ምላሽ ነው፡፡ ልጅዎን ለመርዳት መማር ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም፤

 

 ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ንዴት የልጅዎን አካላዊ ጤና ይጎዳል፡፡ ንዴት የከፍተኛ ደረጃ

ውጥረትና ጭንቀት መንስኤ ነው፡፡ በተከታታይ ከፍተኛ ደረጃ ውጥረት ላይ መስራት

ለርስዎ ጤንነት መጥፎ ነው፡፡ ስር የሰደደ ንዴት ልጅዎን ለልብ በሽታ፣ ለስኳር በሽታ፣

ለከፍተኛ ስብ መጠን፣ የመነመነ በሽታን የመቋቋም ስርአት፣የዕንቅልፍ ማጣትና

ለከፍተኛ የደም ግፊት በተፋጠነ ሁኔታ ያጋልጣል፡፡

 

 ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ንዴት የልጅዎን የአዕምሮ ጤና በጊዜ ሂደት ይጎዳል፡፡ ስር

የሰደደ ንዴት የአዕምሮን ከፍተኛ መጠን ሀይል ይወስዳል፤ እናም በልጅዎ አስተሳሰብ

ላይ ያጠለሽበታል፣ ተረጋግቶ ትኩረት ማድረግ፣ ትልቁን ዕድልና ህይወትን ማስደሰት

ይሳናቸዋል፡፡ ለውጥረት፣ለድብርትና ለሌላ አዕምሮ ጤና ችግሮች ሊዳርጋቸው

ይችላል፡፡

 

 ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ንዴት የልጅዎን የቀለም ትምህርት ስኬት ይፈታተናል፡፡

መምህራንና የክፍል ጓደኞች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ብቻ እንኳን ልጅዎችዎን ግለኛና

ከሌሎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይሸረሽራል፡፡

 

 ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ንዴት ልጅዎችዎ ከሌሎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያውካል፡፡

እጅግ በጣም ከሚወዱት ሰውና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸው የጓደኝነት መስመር ላይ

የመጨረሻ ጠባሳ ያሳርፋል፡፡ ስር የሰደደ፣ ብርቱ ንዴት በሌሎች ለመታመን፣ እነሱን

በቅንነት ለማናገር ያውካል ፣ ወይም ምቾት አይሰጥም ምክንያቱም ሌሎች ሰዎች እነሱ

ምን እንደሚያደርጉ ወይም ምን እያደረጉ እንደሆነ ፈጽሞ ለማወቅ ስለማይችሉ፡፡

 

ንዴትን የመቆጣጠር ክህሎት

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወላጆች ልጆቻቸው ንዴትን በተሻለ መንገድ እንዴት መቆጣጠር

እንደሚችሉ አጋዥ ፍንጮች ናቸው፡፡

ንዴትን ለመቆጣጠር አጋዥ ፍንጮች

1. ንዴት ጤናማ ነው፡፡ በተወሰኑ ሁኔታዎች ንዴት ጤናማ እንደሆነ ለህፃን ልጅዎችዎ

ያሳውቁዋቸው፡፡ የብቀላ ስሜት እንኳን ተግባራዊ እስካልተደረገ ድረስ ጤናማ

ነው፡፡በንዴት ማድረግ፣ በንዴት ሌሎችን መጉዳት፣ እና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ቁጣ

ተቀባይነት የለውም፡፡

2. sለጥቂት ደቂቃዎች የእረፍት መንፈስ ወይም አዝናኝ ተግባር እንዲያስቡ ማስተማር፡፡

3. የሁከት አጫሪ ተደራሽነታቸውን መወሰን፡፡ ልጅዎን ከቴሌቪዥን ወይም በቪዲዩ

ከሚተላለፉ ሁከት አጫሪ ጨዋታዎች ያላቸውን ግንኙነት መቆጣጠር፡፡ የሁከት

ምስሎች የልጅዎን አዋኪ የመሆን ወይም የቁጡነት ዝንባሊያቸውን ይጨምራል፡፡

4. መረዳትና ማበረታታት ፡፡ ልጅዎችዎ ስለ ፍርሀታቸውና ስለ አሉታዊ ስሜቶቻቸው

እንዲያወሩ ማበረታታትና ለመረዳት መሞከር፡፡

5. ስጋትዎን ማሳየት፡፡ ስለ ልጅዎ ስሜቶች ያለዎትን ስጋትና እንደሚከባከቡዋቸውም

ማስተማር፡፡

6. ድጋፍ መሻት፡፡ እነዚህ ምልክቶች በጊዜ ሂደት ከቀጥሉ የአዕምሮ ጤና ባለሙያ

ማናገር፡፡

7. ረጋ ይበሉ፡፡ በተናደደ ልጅ ላይ መጮህ ወይም ማንባረቅ ልጆች አደጋ ውስጥ

እንደሆኑ የሚሰማቸውን ስሜት ያጠናክርላቸዋል፡፡

8. ልጆች ስሜታዊ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ መርዳት፡፡ በስሜታቸው ደስተኞች የሆኑ

ህጻናት ቁጣቸውን በአግባቡ ይቆጣጠሩታል፡፡

 

ምንጭ፡-www.acps