Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

በአብዛኛው ጊዜያዊ ችግር እንጂ የከፋ የጤና ችግር ምልክት ሊሆን እንደሚች

የአፍ መድረቅ ችግር

 

Image result for የአፍ መድረቅ ችግር

በአብዛኛው ጊዜያዊ ችግር እንጂ የከፋ የጤና ችግር ምልክት ሊሆን እንደሚችል አይገመትም።

ይሁን እንጂ ሰውነታችን ያለ በቂ ምክንያት በአፋችን ውስጥ እርጥበት (ምራቅ) እንዲኖር አያደርግም።

በአሜሪካ የጥርስ ህሙማን ማህበር ቃል አቀባይ ዶክተር ማት መሲና እንደሚሉት፥ ለጥርስ መበስበስ ምክንያት የሚሆኑ ባክቴሪያዎች ደረቅ ሁኔታ ይመቻቸዋል።

የአፍ መድረቅ ታዲያ ለጥርስ እና ሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ዶክተር መሲና ተናግረዋል።

ምራቃችን የአልካላይን ይዘት አለው የሚሉት የጥርስ ባለሙያው፥ የምንመገባቸው የአሲድ ይዘት ያላቸው ምግቦች ጥርሶቻችን እንዳያበላሹት ያደርጋል ብለዋል።

የጉሮሮ ህመም እና የአፍ ማቃጠል ስሜቶች የአፍ ድርቀት ምልክቶች መሆናቸውን የአሜሪካ የጥርስ ህሙማን ማህበር መረጃ ያመለክታል።

የአፍ ድርቀት በወቅቱ ህክምና ካልተደረገለት ለሌሎች ህመሞች እንደሚያጋልጥም ነው የሚነገረው።

 

ከዚህ በታችም የተጠቀሱት ነጥቦች የአፍ ድርቀት መንስኤዎችን ይጠቁማሉ።

1. መድሃኒቶች

ዶክተር መሲና ከ600 በላይ መድሃኒቶች ለአፍ መድረቅ የማጋለጥ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላቸው ተረጋግጧል ብለዋል።

የጨጓራ እና ደም ግፊት ህመምን እንዲሁም የአዕምሮ መቃወስን ለማከም የሚወሰዱ መድሃኒቶች የአፍ ድርቀትን ከሚያስከትሉት መካከል ተጠቅሰዋል።

2. እርጅና

እድሜያችን እየጨመረ ሲሄድ የምራቅ አመንጪ እጢዎች በሙሉ አቅማቸው ምራቅ ማመንጨት አይችሉም ያሉት ዶክተር መሲና፥ የእድሜ መግፋት ለአፍ መድረቅ መንስኤ እንደሚሆን አስረድተዋል።

3. የውሃ ጥም

ሰውነታችን በቂ ውሃ ሳያገኝ ሲቀር ምራቅ የማመንጨት አቅሙ ይወርዳል። በዚህም የውሃ ጥም ለአፍ ድርቀት መንስኤ ይሆናል ማለት ነው።

4. የአተነፋፈስ ችግር

 

ከአፍ ይልቅ በአፍንጫ መተንፈስ በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት ይነገራል።

የመተንፈሻ አካላት ችግር በተለይም የአፍንጫ ቀዳዳዎች መዘጋት ግን በአፍ ብቻ እንድንተነፍስ ያደርጋል።

ለረጅም ስአት በአፍ መተንፈስም የአፍ ድርቀትን ያስከትላል ይላሉ ዶክተር መሲና።

 

5. የካንሰር ህክምናዎች

በጨረርም ሆነ በኬሞቴራፒ የሚደረግ የካንሰር ህክምና ለአፍ መድረቅ መንስኤ እንደሚሆን በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ህክምና ክፍል መምህሩ ፕሮፌሰር ጄፍ ቡርጌስ ይናገራሉ።

 

መፍትሄዎቹ…

ዶክተር መሲና ችግሩ የሚያጋጥማቸው ሰዎች በመጀመሪያ ሊያደርጉት የሚገባው ውሃ በብዛት መጠጣት ነው ይላሉ።

የአልኮል መጠጥ ከጠጡ በኋላ የአፍ መድረቅ ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ውሃ አብዝተው መጠጣት እንዳለባቸው ነው የሚመክሩት።

በተለይም ቀይ ወይን የአፍ ውስጥ እርጥበትን የመቀነስ አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ በቂ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

ዶክተር በርጌስ በበኩላቸው፥ የስኳር ይዘት የሌላቸውን ማስቲካዎች ማኘክ የምራቅ መመረትን ስለሚያሳድግ ይሞክሩት ብለዋል።

ውሃ መጠጣት እና ማስቲካ ማኘክ ችግሩን ካላስወገደው ግን የአፍ ድርቀትን ለመቀነስ የሚያግዙ የጥርስ ሳሙናዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

የምራቅ መመረትን የሚጨምሩ ከረሜላዎችን መጠቀምም ሌላኛው መፍትሄ ነው ተብሏል።

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ሁሉ ግን ቀን ላይ ነው የሚሰሩት።

ይሁን እንጂ ሁሌም ከእንቅልፍ ስንነቃ የጉሮሮ ህመም የሚሰማን ከሆነ እና ሌሎች የአፍ ድርቀት ምልክቶችን ካስተዋልን ወደ ህክምና ተቋማት ማምራት ይኖርብናል።

ከዚህም በተጨማሪ የታዘዘልን መድሃኒት ለአፋችን መድረቅ ምክንያት ሆኗል ብለን ካሰብን ሀኪማችን ማማከር ተገቢ ነው፡፡

 

ምንጭ፡-ዶክተር በርጌስ።