Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174
Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176
Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216
Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218
የሆድ ድርቀት የምንለው ከታች የሚከተሉት የህመም ምልክቶች መሃከል አንዱ
የሆድ ድርቀት
የሆድ ድርቀት የምንለው ከታች የሚከተሉት የህመም ምልክቶች መሃከል አንዱ ወይንም ከዛ በላይ ሲያጋጥም ነው:: እነዚህም
- የደረቀ ወይንም የጠነከረ ሰገራ
- መጠኑያነሰ ሰገራ
- ሰገራ ለመውጣት ሲያስቸግር
- በሳምንት ውስጥ ከሶስት ወይንም ከዛ ያነሰ ጊዜ ሰገራ መውጣት ሲኖር ናቸው::
- የሆድ ድርቀት መነሻ ሊሆን የሚችለው
- ከአንጀት ችግር
- ከአመጋገብ ልምድ የተነሳ
- የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶች
ድርቀት ስጋት ሊሆን የሚችለው መቼ ነው?
- ከሰገራ ጋር ደም መቀላቀል ወይንም ከተጠቀሙ በኋላ ደም የመፍሰስ
- ትኩሳት ሲኖር
- የክብደት መቀነስ
- የምግብ ፍላጎት ማጣትና ድካም ሲኖር
ድርቀት ሲፈጠር ምን ላድርግ?
- የቃጫነት መጠናቸው የበዙ ምግቦችን ማለትም አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን አብዝቶ መመገብ
- ጠዋት ጠዋት እንደነ ሻይና ቡና ያሉ መጠጦችን መጠጣት
- ውሃ በብዛት መጠጣት
- ሰገራ የመምጣት ስሜት ሲኖር ወዲያውኑ ወደ ሽንት ቤት መሄድ (ለረጅም ጊዜ አፍኖ አለመቆየት)
መቼ ወደ ሐኪም ቤት ልሂድ?
- ቀደም ሲል ከነበረው የሰገራ አወጣጥ ፀባይ መለየት ወይንም አዲስ ድርቀት መከሰት
- ድርቀት እየተመላለሰ ከሶስት ሳምንት በላይ ከቆየ
- ድርቀት እንዳይፈጠር ለመከላከል ምን እናድርግ?
- ቃጫነት የበዛባቸውን ምግቦችን በብዛት መመገብ
- ጠዋት ላይ ሻይ ወይንም ቡና መጠጣት ውሃና ሌሎች ፈሳሾችን በብዛት መጠጣት
- በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት ሽንት ቤት መጠቀም/ሰገራ መውጣት
ምንጭ፡-hakimyamakru