Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የልብ እና የደም ቧንቧ (

የልብ እና የደም ቧንቧ (ስር) በሽታዎች -CARDIOVASCULAR DISEASES

የልብ እና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎች በአጠቃላይ “Cardiovascular Diseases” በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ በሽታዎች እንደሚከተለው መዘርዘር ይቻላል፦

የአንጎል እና የኩላሊት የደም ቧንቧ በሽታዎች፤
የራሱ የልብ በሽታዎች፦ የልብ የደም ቧንቧ በሽታዎች (coronary Artery Disease)፤ የልብ “Valve” በሽታዎች፤ ከልብ አመታት ጋር የተያያዙ በሽታዎች (Arrhythmias)፤ ልብ የሚያሰራጨው የደም መጠን የማነስ በሽታ (Congestive Heart Failure)
የሌሎች ሰወነት ክፍሎች ደም ቧንቧ በሽታዎች (Peripheral arterial diseases)

የልብ እና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎች መንስኤ ብዙ ነው፤ ግን ዋና ዋናዎቹ የደም ግፊት በሽታ እና የደመ ቧንቧዎች መጥበብ (መደንደን) ናቸው።

በአለማችን በአጠቃላይ ሲታይ ሰው በብዛት የሚሞተው በእነዚህ በልብ እና ከልብ ጋር ተያያዥነት ባላቸው በሽታዎች ነው። በታዳጊ አገሮች እና ወደ ኋላ በቀሩ አገሮች ለየብቻ ሲታይ በብዛት ሰው የሚሞትባቸው ምክንያቶች ይለያያሉ። በኢኮኖሚ በበለጸጉ አገሮች ግን በማያሻማ አገላለጽ ሰው በብዛት የሚሞተው በልብ እና ከልብ ጋር ተያያዥነት ባላቸው በሽታዎች ነው።

አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን፤ ብዙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች እና በኢኮኖሚ ወደ ኋላ በቀሩ አገሮች የልብ እና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎች በከፍተኛ ፈጥነት እያደገ እንደሆነ እና በበለጸጉ አገሮች በተቃራኒው እየቀነሰ መሆኑን ያሳያሉ።

ስለዚህ የልብ እና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎች በየተኛውም የአለም ክፍል ለሚኖሩ ህዝቦች ቀንደኛ የጤና ችግር በመሆናቸው ሁሉም ሰው ስለበሽታዎቹ አስፈላጊ የሆኑ አጥቃላይ እውቀት ኖሮት በሽታዎቹ እንዳይከሰቱ ወይንም ከተከሰቱም እንዳይባባሱ የሚያደርጉ ጥንቃቄዎች ማደረግ ይኖርበታል።

ዋና ዋና መንስኤዎች

የደም ቧንቧ መጥበብ (መደንደን) – atherosclerosis

የዚህ በሽታ አጀማመር እንደሚከተለው መግለጽ ይቻላል። ደምን ወደ ተለያየ የሰውነት ክፍሎች በሚወስዱ ዋና ዋና የደም ቧንቧዎች (arteries) ግድግዳ ላይ ጠጣር ነገር መከሰት ይጀምርና ከጊዜ በኋላ በስፋት እና በውፍረት እያደገ በመሄድ ደንድኖ የደም ቧንቧውን እያጠበበ በመሄድ የተፈጥሮ ተለጣጭነቱንም ያሳጣዋል። ይህ ሂደት በእንግሊዝኛ “plaque formation” በመባል ይታወቃል። እዝህ ላይ በደንብ መታወቅ ያለበት “plaque formation” የረጅም ጊዜ ውጤት ነው። እነዚህ “plaque” እንዲፈጠር መንስኤ የሚሆኑ ነገሮች ቀስ በቀስ አንዱ ባንዱ ላይ እየተደረበ በመከማቸት የደም ቧንቧውን ያቆስሉታል፤ ዙሪያ ግድግዳው ላይ በመከማቸት እና እንደ ጭቃ በመመረግ ያወፍሩታል፤ ያጠነክሩታል፤ በመጨረሻም በቀላሉ የሚሰበር ያደርጉታል።

ለ “plaque” መፈጠር መንኤ የሚሆኑ ነገሮች ምንድናቸው?

የደም ቧንቧዎች የውስጥ ግድግዳ የተገነባው “endothelium” ከተባሉ ሴሎች ሆኖ በጣም ስስ እና ለስላሳ በመሆኑ በቀላሉ ሊቆስል ይችላል። ይህ ለ “PLAQUE” መፈጠር መነሻ (ምክንያት) ሊሆን የሚችለው ቈስለት በምን ምክንያት ሊፈጠር እንደሚችል ግምት እንጂ ምክንያቱ በትክክል አይታወቅም። ግን በመስኩ ያሉ ተመራማሪዎች የሚከተሉት ሶስት ነገሮች መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው ያምናሉ፦

በደም ውስጥ የኮሌስትሮል እና / ወይንም የ “ Ttriglycerides” (ቅባቶች) መብዛት
የደም ግፊት በሽታ
ሲጋራ ማጬስ

“Plaque formation” በአብዛኛው የሚከሰተው እና አደገኛም የሚሆነው ደም ከልብ ተቀብለው ወደ ኩላሊት፤ ወደ ጭንቅላት፤ ወደ እግሮች፤ እና ወደ ራሱ ወደ ልብ በሚወስዱ ሰፋፊ የደም ቧንቧዎች (arteries) ላይ ሲከሰት ነው።

የደም ቧንቧ (ARTERY) ግድግዳ ከላይ በተጠቀሱት ወይንም በሌላ ምክንያት ቁስለት በሚደርስበት ጊዜ እዚያ የቆሰለው ቦታ ላይ ቅባት ነክ የሆኑ ነገሮች፤ ከደም ውስጥ ሊወገዱ የተዘጋጁ የሞቱ ሴሎች/ የሴል ክፍሎች፤ በደም ውስጥ በብዛት ከሚዘዋወረው የካልሲየም ንጥረ ጋር በመሆን መከማቸት ይጀምራሉ። ይህ ቁስለቱ የደረሰበት እና ያልነበረ ነገር የተከሰተበት ቦታ ሰውነታችን በጀርም እንዳይወረር የሚጠብቁ ሴሎች (immune cells) ለማጽዳት ይሞክራሉ፤ ግን የተከሰተው ጠጣር ነገር በነዚህ ሴሎች አቅም የሚጸዳ ሆኖ አይገኝም። እንዲያውም “immune” ሴሎቹ እዚያው እየሞቱ ከክምችቱ ይቀላቀላሉ። በዚህ መልክ የተጀመረው መደራረብ ለአመታት እየጭመረ በመሄድ እና በጅማት (CONNECTIVE TISSUE) በመያያዝ የደም ቧንቧውን ለስላሳ ግድግዳ እያጥበበውና እያደነደነው ይሄዳል። በዚህ አይነት እየደነደነና እየጠበበ የመጣ የደም ስር የተፈጥሮ ተለጣነቱን በማጣት መቋቋም የሚገባውን ያህል የደም ግፊት የማይቋቋም ሆኖ የገኛል። በመሆኑ በበሽታም ይሁን በጊዜያዊ መንስኤዎች የደም ግፊት ከፍ ሲል እነዚህ የደነደኑ እና የጠበቡ ዋና ዋና የደም ቧንቧዎች በቀላሉ በመፈንዳት የልብ መቆም (HEART ATTACK) ወይን ስትሮክ በማድረስ ሞት ወይንም መሰረታዊ የአካል መጉደል ሊያስከትሉ ይችላል።

ምንጭ፡-TENAYE HEALTH INFORMATION CENTER

 
No automatic alt text available.