Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

የታችኛው መንጋጋ ትንንሽ ጥርሶች እንደተለመደው መጀመሪያ ይወጣሉ።

ለጥሩ የጥርስ ጤንነት ምክር

 

Image result for የጥርስ ጤንነት

 

ጥርስን መጠበቅ

የታችኛው መንጋጋ ትንንሽ ጥርሶች እንደተለመደው መጀመሪያ ይወጣሉ። ይሄም የሚከሰተው  ከስድስት እስከ ስምንት ወራት እስኪሆነን ነው። ነገር ግን ቀድመውም ሆነ ዘግይተው ሊወጡ ይችላሉ። ከዚያ ቀጥለው የሚወጡት የላይኛው መንጋጋ የፊት ጥርሶች ሲሆኑ በመከተልም የፊት ጥርሶች፣ ክራንቻ እና በመጨረሻም የኋላኞቹ የመንጋጋ ጥርሶች ይወጣሉ። በአብዛኛው ልጆች እድሜያቸው ከሁለት ተኩል እስከ ሶስት አመት ሲሆናቸው ሁሉንም የወተት ጥርሶች ማለትም አስር ከላይ አስር ከታች ያበቅላሉ።

 

የጥርስ መቦርቦር

ስኳር ለጥርስ መቦርቦር ምክኒያቱ ነው። ልጆች ስኳር አዘል የሆነ ምግብ ስንበላ ወይም ስንጠጣ በአፍ ውስጥ ያለው ባክቴሪ አሲድ በማመንጨት ጥርስ እንዲበሮቦር ያደርጋል።  ስለዚህም ከመመገቢያ ሰአት ውጪ ስኳር የያዘ ነገር ያለመብላት ወይም ያለመጠጣት ጥሩ ነው።

 

ጥርሳችንን ማፅዳት

ከጫወታ ወደ ቁም ነገር ፤ የመጀመሪያ ጥርስ በትንሽ እና ለስላሳ የጥርስ ብሩሽ ማፅዳት ይችላል። ጥርስ መቦረሹን እንደ ጨዋታ መጀመር ይቻላል። ጥርሳችንን በቀን ሁለት ጊዜ በጥርስ ሳሙና መፋቅ አለብን፡

 

ጣፋጭ ምግብ መቀነስ

ጥሩ ምግብ እና የአመጋገብ ባህሪይ ለጥርስ ብቻ ሳይሆን ለመላው አካል አስፈላጊ ነው።  ጣፋጭ ነገሮች ቅዳሜ እና የተለየ ዝግጅት ለምሳሌ ልደት ሲኖር ብቻ ብንመገብ መልካም ነው። እንደ አፕል፣

ካሮት የመሳሰለ መስጠት ለጥርስም ለሰውነትም ጥሩ ነው።

 

አደጋ ከደረሰ

ልጆች በአጋጣሚ ከወደቅን ወይም አፋችን ሲመታ አንዱ  ወይም ብዙ ጥርሶች ሊጎዱ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ በአከባቢያችን ወደሚገኝ  የጥርስ ክሊኒክ ወይም የህክምና ተቋም መሄድ አለብን።

 

 Source; akukulunews