Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

በኢንተርኔት ለሚፈጠሩ የፍቅር ግንኙነቶች ስኬታማነት በእጥፍ የሚጨምሩ ??

ከኢንተርኔት ወደ አካላዊ ግንኙነት መቀየር

 

Image result for ትዳር በኢንተርኔት

 

በኢንተርኔት ለሚፈጠሩ የፍቅር ግንኙነቶች ስኬታማነት በእጥፍ የሚጨምሩ እና ሃሰተኛ አካውንቶ ችን መለየት የሚያስችሉ ወሳኝ 4 ነጥቦች!

አንባቢዎቼ በሙሉ የመረጃ መረብ ተጠቃሚ እንደመሆናችሁ መጠን ዛሬ “መላ” ከምትሰኘው እና በቅርቡ ለህትመት ትበቃለች ተብሎ ከምትታሰበው መጽሃፌ ትንሽ ቆንጥሬ ስለ ድህረ-ገጽ ክጀላ (online dating) ላጫውታችሁ አሰብኩኝ። በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ ትልቅ የህይወት አካል እየሆነ የመጣው የመረጃ መረብ (internet) አገልግሎት ነው። ሳይንቲስቶች እንደሚጠቁሙት የሰው ልጅ ከኢንተርኔት ጋር ያለው ቁርኝነት ከቀን ቀን እየጨመረ ነው እናም ከዚሁ ከኢንተርኔት የሰው ልጅ እየተጠመባቸው ካሉ ግልጋሎቶች መሃል ግብይት፤ትምህርት እና የመሳሰሉት ቢጠቀሱም ትልቁን ድርሻ ይዘው የተቀመጡት ግን የማህበራዊ ድህረ ገጾች እና የመተጫጫ(dating) ገጾች ናቸው። ከነዚህም መሃል Twitter.com , eHarmony.com, match.com ……የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ ነገር ግን በእኛ ሃገር Facebook ከማህበራዊ ድህረ ገጽነት ግልጋሎቱ አልፎ የኛን ሃገር ወጣቶች ከማጠባበስ ጀምሮ እስከ ትዳር ደጃፍ በማድረስ ቀዳሚነቱን ይዟል። እናም ዛሬ የማጫውታችሁ እዚሁ Facebook ላይ የተቃራኒ ጾታን ቀልብ መሳብ የሚያስችሉ እና ሃሰተኛ (scam,catfish) አካውንቶችን መለየት የሚያስችሉ አጠር ያሉ 4 ነጥቦችን ነው። እነዚህ ነጥቦች ለሁለቱም ጾታ ጠቃሚ ናቸው

 

  • ግለ ታሪክ (profile) ወሳኝ ነው

መጀመሪያ የምትልከው መልእክት(message) እና ግለ ታሪክ (profile) በኢንተርኔት ለሚፈጠሩ ግንኙነቶች እንደ መሰረት የሚታይዩ እና በተቃራኒ ወንበር ለተቀመጠው ሰው ስለአንተ የመጀመሪያ ምልከታን የሚሰጡ ስለሆነ ጥንቃቄ ይገባቸዋል። ስለዚህ profile ን በተገቢው ሁኔታ ማሰማመርይገባል ለምሳሌprofile picture ስትመርጥ የምትወደው ስፖርተኛ፤ የፊልም አክተር፤ ዘፋኝ ወይም አባባል ሊሆን አይገባም ምክንያቱም እነዚህ ባለህ የራስህ ገጽታ የማትተማመን ሊያስመስሉህ ስለሚችሉ ብዙ ለምትልካቸው መልክቶች(message) ምላሽ ሊያሳጡህ ይችላሉ። ስለዚህ profile picture ስትመርጥ በአሪፍ ኳሊቲ የተነሳ አሪፍ ፎቶ ቢሆን እና አይንህ ቀጥታ ወደ ካሜራው ያላዞርክበት ቢሆን ይመረጣል በተጨማሪም ሁለት ሶስት ከሆኑ የተቃራኒ ጾታዎች ጋር በመዝናኛ ቦታ የተነሳሀውን ፎቶ profile picture ብታደርገው ከሰው ጋር መግባባት የምትችል እና ፈታ ያልክ ሰው መሆንህን አንተ ምንም ሳታወራ ፕሮፋይልህን ለተመለከተው ሰው በቀላሉ ሊያሳይልህ ይችላል በመጨረሻም ”biography” ከሚጻፍበት ቦታ ላይ ራስህን ከአቅም በላይ መኮፈስ እና ብዙ ነገር ማውራት ኦንላይን ሊተዋወቅህ የሚችለውን ሰው ብዛት እንደሚቀንስ ልታውቅ ይገባል ምክንያቱም ይሄ የስራ መወዳደሪያ cv ሳይሆን ኦንላይን ዴቲንግ ነውና ። ስለዚህ ስለራስህ ቀለል ያለ እና ወጣ ያለ አይን ውስጥ የሚገባ አጭር ጽሁፍ ቢሆን ይመረጣል በተጨማሪም የሚያነበውን ሰው ቀሪውን ማንነትህን ለማወቅ እንዲጓጓ የሚያደርግ እንዲሆን ቆንጆ አድርገህ ቀምረህ ጻፈው።

 

  • የመጀመሪያው መልእክት (message) ምን ይሁን?

እዚህ ጋር ብዙዎቻችን የምንሳሳትበት እና የላክነው መልእክት ምላሽ በማጣቱ የምንበሳጭበት ቦታ ነው በእርግጠኝነት ከዚህ በታች ከምነግርህ ስህተቶች መሃል ቢያንስ አንዱን አድርገሀዋል።

 

ስህተት አንድ ቆንጆ ለሆነች ሴት ምን ያክል ቆንጆ እንደሆነች መልእክት መላክ ለምሳሌ “anchi konjo” “hey sexy” “ u r beautiful as……” ምናምን ብለህ ልከህ ምላሽ መጠበቅ የዋህነት ነው ምክንያቱም አንተ የላከው አይነት መልእክት በቀን ከ 50 በላይተመሳሳይ መልእክቶች ይደርሷታል እናም ላንተ ተራ ሙገሳ ባለመመለሷ ልትናደድ አይገባም።

 

 

ሌላ ስህተት ልጨምርልህ፡ ትርጉም አልባ መልእክቶች መላክ ለምሳሌ “hey” “hi’ “what’s up?”…….. ምናምን…… እነዚን የመሳሰሉ መልእክቶ ች ከመላክ ተቆጠብ ምክንያቱም የምታውቅህ ወይም የደበራት ሴት ካላገጠመችህ በስተቀር ምላሽ ሊያሳጡህ ወይም ላንተ ያላትን አመለካከት ትንሽ እንዲሆን ሊያደርጉት ይችላሉ። ሌላ በተደጋጋሚ የምንሰራው ስህተት ልጨምርልህ፡ የህይወት ታሪኳን እንደሚጽፍ ጋዜጠኛ በደረቅ ጥያቄዎች አታፋጣት መልእክቶችህን መመለስ ያለባት ተገዳ ሳይሆን ፈልጋ መሆን አለበት። እናም በተመሳሳይ ሁኔታ ወሲብ ተኮር የሆኑ መልእክቶችን ወይም ፎቶዎችን በጣም ላልተግባባሀው ሰው በፍጹም እንዳትልክ ምክንያቱም ምንያህል ጅላጅል እና ወሲብ ፈላጊ ተራ ቂል መሆንህን ያሳብቁብሃል። እነዚህን ካስተካከልክ በኋላ መላክ ያለብህን አይነት መልእክት ልንገርህ ፡ ምንግዜም መልእክት የምትልክለትን ሰው profile ትንሽ ለማየት ሞክር እናም ከፎቶዎት ወይም ፖስት ከምታደርጋቸው ነገሮች መሃል አንተ እና እሷን አንድ የሚያደርጋችሁን ነገር ለማግኘት ሞክር ለምሳሌ ሁለታችሁም የምትወዱት ዘፋኝ፤ፊልም ወይንም ለጉብኝት ሄዳ ፎቶ የተነሳችቸትን ቦታ አንተም የምታውቀው ከሆነ ወሬህን ከእነዚህ ብትጀምር ስኬታማ የመሆንህ እድልህ ይሰፋል በተጨማሪም ፈገግ የሚያሰኙ መልእክቶችን ወይም ፎቶዎችን በመላክ ወሬህን ብትጀምር የተሻለ ይሆናል፤ አንዳንዴም ወጣ ያሉ መልእክቶችን መላክም ምላሽ ከማያሳጡት መካከል ተመድበዋል ለምሳሌ “stop thinking about me” ወይም “I saw this cute doll and it remind me something of you, u know what?” የመሳሰሉ መልእክቶች አሪፍ ናቸው ምክንያቱም ማንኛውም ሰው ሌላ ሰው ስለ እሱ ምን እንደሚያስብ ማወቅ ይፈልጋል፤ በተጨማሪም አንተ የምትልካቸው መልእክቶች በርዝመት እሷ ከምትልካቸው መልእክቶች ጋር እንዲመጣጠኑ አድርግ። በመጨረሻም ማወቅ ያለብህ ነገር ይሄ የፌስቡክ ጠበሳም የቁጥር ጨዋታ መሆኑን ነው ስለዚህ ብዙ ጓደኞች ባሉህ ቁጥር ውጤታማነትህም አብሮ ይጨምራል።

 

  • ከኢንተርኔት ወደ አካላዊ ግንኙነት መቀየር

እዚህ ጋር ሁለት መንገዶች አሉ፡ የመጀመሪያው ረጋ ያለና ትእግስትን የሚጠይቅ እና ሁለተኛው ደግሞ ፈጣን ነገርግን አደጋ ያለው ነው።

 

መንገድ አንድ ረጋ ያለው መንገድ ቀስ እያሉ ግንኙነትን ማጥበቅ እና እምነትን መገንባት ነው። ይሄም ሳይበዛ ፖስት በምታደርጋቸው ነገሮች ላይ ጥሩ ነገሮችን comment በማድረግ እና ለነገሮች የሚሰማትን ስሜት ቻት ስታደርጉ በመጠየው ለአንተ ያላትን ስሜት በጊዜ ሂደት በመቀየር ግንኙነታችሁን በማሳገግ ከ facebook ወደ viber ወይም whatsapp እንድትጠቀሙ ይስልክ ቁጥር በመቀያየር ከዚያም ወደ መደዋወል እና መገናኘት በደረጃ መሄድ ነው።

 

መንገድ ሁለት ፈጣን ቢሆንም ግን አደጋም አለው እንዴት መሰለህ ትንሽ መልእክቶችን (20-30) ያክል ከተለዋወጥክ በኋላ “ደስ ብለሽኛል ብዙም የ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ስላልሆንኩ ተገናኝተን ብንጫወት ደስ ይለኛል” ብለህ በመላክ መልሷን መጠበቅ ነው። እዚህ ላይ ማወቅ ያለብህ ነገር ጥሩ profile ካለህ እሺ የማለት እድሏ እንደሚጨምር ነው ስለዚህ ጥሩ ጥሩ ፎቶዎችን ከፕሮፋይልህ መጨመርን አትዘንጋ።

 

  • ሃሰተኛ አካውንቶ ችን እንዴት መለየት ይቻላል?

ሃሰተኛ አካውንቶችን ልታውቅበት/ልታውቂበት የሚቻልባቸው ቀለል ያሉ መንገዶች አሉ እነዚህም አ ብዛኛዎቹ አካውንቶች ከዚህ በታች ያሉትን ምልክቶች ያሳያሉ እናም እንደዚህ አይነት አካውንትካጋጠመ UNFRIEND ወይም BLOCK ማድረግ እንዳይዘነጉ።

 የሃሰተኛ አካውንቶች ምልክቶች

ብዙዎቹ በጣት የሚቆጠሩ 1 ወይም 2 ብቻ የሆኑ በጣም ቆንጆ ፎቶዎች አላቸው

ወሲባዊ የሆነ መልእክቶችንም ሆነ post የሚደረጉ ነገሮችን ከማስተላለፍ ወደ ኋላ አይሉም

ፎቷቸው ላይ የሚገባውን ያህል like አይኖርም በተጨማሪም ፎቶዎቹ ላይ የሚሰጡት commentች ብልግና ነክ ነገሮች እንጂ ከጓደኛ ወይም በአካል

ከሚያውቃቸው ወዳጅ እንዳልሆነ ያስታውቃሉ

መልእክቶችን በመለዋወጥ ላይ እያላችሁ የራሳቸውን ምንም አይነት ፎቶ ለመላክ ፍቃደኛ አይሆኑም

ምንጭ፡-studentethiopia