Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ብዙዎቻችን በጣም የምንወዳቸው እና አዘውትረን የምንጫማቸው ጫማዎች

አሮጌ ጫማዎትን ንጹህ ፤ ጽዱ እና አዲስ የሚያደርጉበት ዘዴ እነሆ

 

Image result for አሮጌ ጫማዎትን ንጹህ ፤ ጽዱ

 

ብዙዎቻችን በጣም የምንወዳቸው እና አዘውትረን የምንጫማቸው ጫማዎች እንደሚኖሩን ግልጽ ነው። እነዚህ አዘውትረን, የምንጫማቸው ጫማዎች ከአገልግሎት  ብዛት መቆሸሽ እና በመጎሳቆል ሳያልቁ ይወገዳሉ።ታዲያ እነዚህን  ከአገልግሎት  ብዛት የሚቆሽሹ እና የሚጎሳቆሉ ጫማዎች እንዴት በቀላሉ ማጽዳት እና እንደቀድሞው ንጹህና አዲስ ማድረግ የምንችልበትን ዘዴ ይዘንላችሁ ቀርበናል። ይህን ለማድረግ የሚያስፈልጉን ነገሮች :

 

የዳቦ ዱቄት ማቡኪያ (ሶዲየም ባይ ካርቦኔት)

የጥርስ ብሩሽ

ሆምጣጤ

ውሃ በጎድጓዳ ሰሃን

እና የቆሸሸው ጫማ

shoe-1

እዚህ ጋር መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር ምንም እንኳ ጫማዎች የቱንም ያህል ንጹህ ቢሆኑም የጫማ ማሰሪያዎች ንጹህ ካልሆኑ  የጫማውን ውበት ከመደበቅም በላይ የጫማውን ያረጀ ያስመስሉታል። ስለዚህ የጫማ ውበት ሲታሰብ የማሰሪያ ንጽህና በፍጹም መዘንጋት የለበትም።  ስለዚህ ጽዳቱን የምንጀምረው ማሰሪያውን ፈትቶ በማፅዳት ይሆናል።

 

shoe-2

ወደ ጫማው ማጽዳት ስንመለስ በመጀመሪያ ሁሉንም የጫማውን ክፍል በውሃ ማራስ እና ማርጠብ  ያስፈልጋል፡፡ ይህም ጫማው ላይ ያሉት እና በቀላሉ የሚገወዱ ቆሻሻዎች ለማስለቀቅ ይረዳል። በመቀጠል ሆምጣጤ እና የዳቦ ዱቄት ማቡኪያ  (baking powder) በበጎድጓዳ ሰሃን ላይ በተመጣጠነ ሁኔታ ማዋሃድ። በዚህ ወቅት ፈጣን እና አደገኛ የሆነ ውህደት እንዳይፈጠር ጥንቃቄ መደረግ አለበት። (ሆምጣጤ እና ሶዲየም ባይ ካርቦኔት ሲዋሃዱ ካርበን ዳይኦክሳይድ በመፍጠር ና በመገንፈል ከሰሃኑ ላይ ሊፈሱ  ይችላሉ።)

shoe-3

በመቀጠል በብሩሽ እየቆነጠሩ መላ የጫማውን ክፍል እየቀቡ ማዳረስ። በዚህ ግዜ የመነቸኩ ቦታዎች እስኪለቁ መፈተግ አይጠበቅቦትም። መጠኑ ከቀቡ ይበቃል። አልያም ከቀቡ በኋላ ከማለቅለቅ በፊት ትንሽ ማቆየት ይቻላል።

 

shoe-4-1shoe-4-2

በመጨረሻም ጥቂት ከጠበቁ በኋላ በቀዝቃዛ ውሃ በማለቅለቅ እና በማድረቅ ንጹህ እና አዲስ ጫማ ማግኘት ይቻላል።

 

ምንጭ፡-studentethiopia