Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ለውዝ ወይም ኦቾሎኒ ከ1,6ዐዐ ዓመት በፊት በፔሩ የተገኘ እንደሆነ ይነገራ??

የለውዝ /ኦቾሎኒ/19 የጤና በረከቶች

 

Image result for ለውዝ /ኦቾሎኒ

 

ለውዝ ወይም ኦቾሎኒ ከ1,6ዐዐ ዓመት በፊት በፔሩ የተገኘ  እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከዛም በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት  ላይ ተሠራጭቶ በዓለም ታዋቂ ሆኗል፡፡ ለውዝ ከምግብነት

ባሻገር ለጤናም ሰፊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገራል፡፡ እነዚህን ጠቀሜታዎች በዝርዝር አስቀምጠናል እንሆ…

1. በተለምዶ ከሚባለው ጋር በተዛመደ መልኩ በዕርግጥም ለውዝ ለተዋልዶ ስርዓት ጤንነት ተመራጭ ነው፡፡ በተለይም ከእርግዝና በፊትና በዕርግዝና ወቅት ለውዝ መመገብ በውስጡ የሚገኘው ፎሊክ አሲድ በእርግዝና ወቅት በጽንሱ ዕድገት ላይ ሊያጋጥም የሚችለውን ችግር 70 በመቶ ያህል ያስወግዳል፡፡

2. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላል – በለውዝ ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚገኘው ማንጋኒዝ ለስብና ለካርቦሀይድሬት መፈጨት፣ ለካልሲየም በሰውነታችን ህዋሳት መዋሀድና በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን የተስተካከለ እንዲሆን ያስችላል፡፡

3. በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ጥሩው ኮልስትሮል እንዲጨምርና መጥፎው የኮልስትሮል ዓይነት ደግሞ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ በለውዝ ውስጥ የሚገኘው የመዳብ ማዕድን ሰውነታችን በልብ ህመም እንዳይጠቃ ይከላከላል፡፡

4. የሐሞት ጠጠር እንዳይከሰትና የሐሞት ከረጢት ጤናን ያስጠብቃል፡፡

5. ድብርትን ይከላከላል፡፡

6. የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፡፡

7. የልብ ህመም፣ ካንሰርን፣ የነርቭ ህመሞችን እንዲሁም ከቫይረስና ከፈንገስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎችን ይከላከላል፡፡

8. የአእምሮ ብቃትን ከመጨመርም በተጨማሪ እንደ ፓርኪንሰንና አልዛይመር ዓይነት በሽታዎች እንዳይከሰቱ

ይረዳል፡፡

9. በካንሰር መጠቃትን ይቀንሳል፡፡

10. ሐይል ሰጪ ከመሆኑም በላይ ጥቂት በልተው ለረጅም ሰዓታት እንዳይርቦት ስለሚያደርግ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

11. በእርግዝና ወቅት ለውዝ መመገብ የሚወለዱ ህጻናት እንደ አስም በመሳሰሉት በሽታዎች እንዳይጠቁ ያደርጋል፡፡

12. ለታዳጊዎች የአካል ግንባታ ለውዝ እጅጉን ተመራጭ ነው፡፡

13. በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡

14. የጸጉር ስሮችን በማጠንከር ለጸጉር ጤንነት ተመራጭነው፡፡

15. ስትሮክ የሚሰኘውን ወደ አንጎል በሚሄደው የደም ፍሰት መዛባት ሳቢያ የሚከሰተውን የአንጎል ላይ አደጋ ይከላከላል።

16. ፍሪ ራዲካል በተሰኙት ሞሎክዩሎች ሳቢያ በሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ይቀንሳል።

17. እብጠትና ሌሎችን ከቆዳ ጋር የተያያዙ ህመሞችን ይከላከላል። ቆዳን ከውስጥ በማለስለስ የተለያዩ የቆዳ ችግሮችን ይከላከላል።

18. ለውዝ በተለያዩ የቫይታሚን ዓይነቶች የበለጸገ ነው።

19. ለውዝ በፖታሲየም፣ ማንጋኒዝ፣ መዳብ፣ ካልሲየም፣ ማግኒዚየም፣ ብረት፣ ሴሬኒየም እና ዚንክ በመሳሰሉት ማዕድናት የበለጸገ ነው። ቡናን መጠጣት ከጤና አኳያ

ያለው ጠቀሜታ፡-

– የማስታወስ አቅምን ይጨምራል

– ድብርትን ያስወግዳል

– ለራስ ምታት እና አስም ፍቱን ነው

– በኩላሊት ጠጠር እንዳንጠቃ ይከላከላል

– ጉበታችን እንዳይታወክ ይከላከልልናል

– በሰውነታችን ላይ በስራ ብዛት የሚፈጠሩ ህመሞች  እንዳንጠቃ ይረዳል

– ለድንገተኛ ሞት የሚያበቃ የልብ በሽታ እንዳንጠቃ ይጠብቃል

– በስኳር በሽታ ከመያዝ ይከላከላል

– በነቀርሳ በሽታ እንዳንያዝ ይረዳል

ምንጭ- ዘ ሀበሻ