Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

በእርግዝና ወቅት ነብሰጡሮች መውሰድ ስለሚኖርባቸው አመጋገብ አይነቶች እነሆ

Image result for በእርግዝና ወቅት

 

የተመጣጠነ ምግብ በእርግዝና ወቅት ለፅንሱና ለእናት ጤና እጅጉን ጠቃሚ ነው፤ ስለዚህ በዚህ ፅሁፋችን ዛሬ በእርግዝና ወቅት ስለሚወሰናመወሰድ ስለሌባቸው የምግብ ዝርዝሮች እንመለከታለን።

በእርግዝና ወቅት የሚመጣ ህመም ወይም ከእርግዝና በፊት ያለ የህክምና ችግር ብሎም ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ልምድ በእርግዝና ወቅትበሚደረግ የህክምና ክትትል ያስፈልገዋል ። በአጠቃላይ ለአንድ ጤናማ እናት

 

·         በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ ይኖርባታል፣ 

·         አትክልት፣ 

·         ጥራጥሬ፣ 

·         ፍሩት እና አነስ ባለ መልኩ የፕሮቲን ይዘት ያላቸውን ምግቦች ማለትም እንደስጋ፣አሳና እንቁላል አይነት ምግቦችን መመገብ ጤናማ የእርግዝና ሁኔታ እነዲፈጠር ይረዳል። 

·         በእርግዝና ወቅት ሲጋራ፣ አልኮል እና ሌሎች እጾችን መጠቀም የፅንሱን ጤና ማበላሸት ብቻ ሳይሆን የሚወሰዱት ጤናማ ምግቦች  ላይም በሰውነት ውስጥ ሊሰሩት የሚችሉትን ጥቅም በእጅጉ ይቀንሳል።

·         ቫይታሚን ኤ በብዛት መመገብ ማለትም ከ10,000 IU በላይ በቀን አንድ እናት የምትወስድ ከሆነ ፅንሱ ላይ ጉዳቶችን ሊያደርስ ስለሚችል ከእንደዚህ አይነት እንክብል መቆጠብ ይኖርቦታል።

·         የምግብ ሰዐትን ጠብቆ አለመውሰድ ብሎም ፈፅሞ አንድ አይነት ምግብን ብቻ ማዘውተር ለእርግዝናው አስፈላጊ የሚሆኑትን ንጥረነገሮች ስለሚያሳጣ የፅንሱ እድገትን ይጎዳል።

በእርግዝና ወቅት በተበከለ ምግብ አማካኝነት ከሚመጡ ኢንፌክሽኖች መቆጠብ ለፅንሱ ጤንነት እጅግ አስፈላጊነው፤ ስለዚህ፦

·         አንድ ነብሰጡር ሁሌ ከምግብ በፊትና በሃላ እጇን መታጠብ ይኖርባታል።

·         ሁሉም አይነት የስጋው ጤቶች መብሰል ይኖርባቸወል።

·         ወተት ፓስቸራይዝድ መሆን አልያም መፍላት ይኖርበታል።

·         ሁሉም አይነት የአትክልት ውጤት በደምብ መታጠብ ይኖርበታል፤ በቤት ውስጥም ምግብ ለማዘጋጀት የምንጠቀምባቸውን ጨምሮ።

በሃኪም የሚታዘዝ እስከ

· 15mg ያክል የሚሆን አይረን በቀን ተጨማሪ መውሰድ በእርግዝና ወቅት የሚፈጠር የደም ማነስን ይከላከላል።

·  በሃኪም ትዛዝ ከ0.4-0.6 mg ፎሊክ አሲድም እርግዝናው ከመፈጠሩ አንድ ወር በፊትና ከእርግዝናው በሃላ እሰከ 3 ወር ጊዜ ያክል መውሰድ ፅንሱ ላይ ሊፈጠር ከሚችል neural tube defect የአከርካር ችግር ይታደጋል።

ሌሎች የቫይታሚን፣ ሚንራል እና ተጨማሪ መድሃኒት እንክብሎች በሃኪም ሳይታዘዙ ፈፅሞ መውሰድ አይገባም።

 

ምንጭ፡-.ethiohakim