Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

አቮካዶ ንጥረ-ሀብታም ምግቦች (Super-food) ከሚባሉት መካከል አንዱ ሲሆን በው??

ንጥረ-ሀብታሙ አቮካዶ (Avocado the Super-food)

 

Image result for (Avocado

 

በህክምናው ዘርፍ ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለው አባባል ከፍተኛ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ስለሆነም ሀኪሞች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የትኞቹን የምግቦ አይነቶች ብንመገብ ለየትኞቹ የጤና ችግሮቻችን ፍቱን መፍተሄ ሊሆኑ እንደሚችሉ ምከር ሲሰጡ ይሰተዋላል፡፡ የዛሬው   ፅሁፌ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ባተረፈው አቮካዶ ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ አቮካዶ ንጥረ-ሀብታም ምግቦች (Super-food) ከሚባሉት መካከል አንዱ ሲሆን በውስጡ ብዙ ንጥረ-ነገሮችን ይዟል፡፡ አቮካዶ ባለው ከፍተኛ የሆነ የቫይታሚንና የሚንራል ይዞታ፣ በውስጡ በያዘው ፋይበርና እጅግ አንስተኛ የስብ መጠን የዓለማችን ተመራጭ የፍራፍሬ ዓይነት እንዲሆን አድርጎታል። የእኔም የዕለት ተዕለት ምግቤ ከሆመ ሰነባብቷል፡፡

 

1. የኮሌስትሮል መጠንን ዝቅ ለማድረግ ፣

አቮካዶ በውስጡ የያዘው ከፍተኛ የፋቲ አሲድ መጠን በሰውነታቸን ያለውን የኮሌስትቶል መጠን ዝቅ እንዲል ያስችላል። በአንፃሩ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆነው የኮሌስትሮል መጠን ከፍ እንዲል ያደርጋል ፤

 

2. ለልብ ህመም/ስትሮክ የመጋለጥ ዕድልን ለመቀነስ  

አቮካዶ በውስጡ ያዘለው ቫይታሚን ኢ ለልብ ህመም/ስትሮክ የመጋለጥ ዕድላችንንም በእጅጉ ይቀንሳል፣

 

3. እርጅናን ለመከላከል እና የቆዳ ውበት ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ ፣

በአቮካዶ ውስጥ በብዙ መጠን የሚገኘው አንቲ ኦክሲዳንት ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና የሞቱ የቆዳ ሴሎች እራሳቸውን እንዲተኩ ሲያግዝ፥ ካሮቲኖይድስ የተባለው ንጥረ

ነገርም በቆዳ ላይ የሚታዩና የቆዳን ውበት የሚቀንሱ ምልክቶች እንዳይከሰቱ ያደርጋል።

 

4.ክብደት ለመቀነስ ፣

አቮካዶ ሙቀት ሰጪ ምግብ ከምንላቸው የምግብ አይነቶች እንደመመደቡ፥ በየማዕዳችን በቂ የጊዜ ልዩነት እንድናደርግ ዕድል ይሰጠናል፤ በዚህም ቶሎ ቶሎ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማን በማድረግ የምግብ ፍጆታንና ክብደታችንን እንድንቀንስ ያስችላል።

 

5. ለስኳር ህመምተኞች ፣

በአቮካዶ ውስጥ በጥሩ መጠን የሚገኘው ፖታሺየም በደማችን ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን በማመጣጠን በሰውነት ውስጥ የልብ ስራንና የስኳር መጠንን የተረጋጋ እንዲሆን ያስችላል።

 

6. ለፅንስ ጤንነት ፣

አቮካዶ ጥሩ የቫይታሚን ኤ ፣ ቢ ኮምፕሌክስ፣ ሲ፣ ኢ፣ ኤች፣ ኬ እና ፎሊክ አሲድ መገኛ ነው። በተጨማሪም በውስጡ የሚገኙት እንደ ማግኒዢየም፣ ኮፐር፣ አይረን ፣ ካልሲየም እና ፖታሲየም የመሳሰሉትን ንጥረ ነገሮች ለፅንሱ ዕድገት እጅግ ወሳኝ ናቸው። አቮካዶን አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች ከማያዘወትሩት የተሻለ ለስላሳ ቆዳ እና ፀጉር፣የሰውነት ጠረን፣ የአዕምሮ ዕድገት እንደሚጎናፀፉም ጥናቶች ያመላክታሉ

 

 ምንጭ፡-proudlyhabesha.