Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ሁላችንም ከሌላው ሰው ጋር ለየት የሚያደርገን በህሪያትና ችሎታዎች የታደ?

የአለማችን አስገራሚ ሰዎች

ሁላችንም ከሌላው ሰው ጋር ለየት የሚያደርገን በህሪያትና ችሎታዎች የታደልን ነን፡፡ ይሁንና የአንዳንድ ሰዎች የተሰጣችው ልዩ ችሎታ በጣም የሚገርምና ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ ከዚህ በመቀጠል በአለማችን በጣም አስገራሚ የሆኑ  ሰዎችን ተፈጥሮ ካደለቻቸው ልዩ ብቃታቸው ጋር እናያለን፣

 

    1. ወገበ-ቀጭ እመቤት

 

wegebe kechinua

የ26 አመቷ ጀርመናዊት ሚሸል ኮብከ በአለማችን ወገበ-ቀጭኗ እመቤት ስትሆን፤ የወገቧ መጠነ-ዙሪያ 40.64 ሳንቲ ማትር ወይም 16 ኢንች ነው፡፡ ሚሸል የወገቧን መጠነ-ዙሪያ ከዚህም በታች ወደ 35.56 ሳንቲ ማትር ወይም 14 ኢንች  የማሳነስ ዕቅድ እንዳላት ትናገራለች፡፡ “ችቦ አይሞላም ወገቧ ማር እሸት ነው ቀለቧ” የተባለው ለዚች አይነቷ ቆንጆ ሳይሆን አይቀርም፡፡

 

    1. ብረት-በሉ ሰው

 

biret belu.PNG

ይህ ግለሰብ ሚቸል ሎቲቶ ይባላል የፈረንሳይ ዜግነት ያለው ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሠኔ 15 ቀን 1950 ነበር የተወለደው፡፡ ሚቸል ሎቲቶ  አንድን አውሮፕላን በሁለት አመታት ውስጥ አጣጥሞ እንደበላ ይነገርለታል፡፡ በ40 አመት ጊዜ ውስጥ ሚቸል ሎቲቶ ከዘጠኝ ቶን በላይ ክብደት የሚመዝን ብረት ተመግቧል፡፡ መቸም ሰው በጤናው ብረትን አይመገብምና “ይህ ሚቸል የተባለ ግለሰብ ግን ጤነኛ ነው?” ብለው ሳይጠይቁ አይቀሩም:: ሚሸል ፒካ የተባለ የአእምሮ ህመም ተጠቂ ሲሆን፣ የህመሙ ዋነኛ ባህሪይ ሰዎች በተለምዶ የማይመገቧቸውን ነገሮች (ብረትና ፕላስቲክ የመሳሰሉትን) እንድንመገብ የሚያደርግ ነው፡፡

 

    1. ፂመ-ረጅሙ ሰው

 

Tsimamu

ራም ሲንግ ቹዋሃን ይባላል ህንዳዊ ነው በአለማችን ፂመ-ረጅሙ ሰው ለመባል በቅቷል፡፡ የራም ፂም 4.29 ሜትር የሚረዝም ሲሆን በቀን ውስጥ አንድ ሰዓት የሚሆነውን ጊዜ ፂሙን በማጽዳትና በማበጠር ያሳልፋል፡፡ አሪፍ ጊዜ ማሳለፊያ ያገኘ ይመስላል፡፡

 

    1. እድሜ-ጠገቡ ፓይለት

 

shimagelewe pailet

አቶ ፒተር ዌበር ጁኒየር የተባሉት አሜሪካዊ በአለማችን እድሜ ጠገቡ አውሮፕላን አብራሪ መሆናውን አለምአቀፋዊው የክበረ ወሰን መዝገብ ያስረዳል፡፡ አቶ ፒተር የ96 አመት ወጣት ሲሆኑ ላለፉት 72 አመታት አውሮፕላን ሲያበሩ ቆይተዋቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በወር ቢያንስ ለሁለት ጊዜ የሰማይ ላይ ጉዟቸውን እንደሚያከናውኑ አቶ ፒተር ይናገራሉ፡፡

 

    1. እድሜ-ጠገቧ የዮጋ መምህርት

 

 

yogaአሁን ደግሞ ከእድሜ ጠገቡ አውሮፕላን አብራሪ ወደ እድሜ-ጠገቧ የዮጋ መምህርት እንሸጋገር፡፡ ወይዘሮ ታኦ ፖርቸን-ሊንች የ96 አመት እድሜ ባለጸጋ ናቸው፡፡ ለ70 አመታት የዮጋ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ዘወትር ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ወይዘሮዋ ተማሪዎቻቸውን ሰብስበው እንዴት ሰውነታቸውን ማጠፍና መዘርጋት እንደሚችሉና ሌሎችን የዮጋ ዘዴዎች ያስተምራሉ፡፡

 

    1. አፈ-ሰፊው ሰው

 

afe sefi

ፍራንሲስኮ ዶሚነጎ ጃኩይም ይባላል በአለማችን ትልቅ የሆነውን አፍ በመያዝ ክብረ ወሰኑን ሰብሮ ይገኛል:: የጃኩይም አፍ ከዳር እስከዳር 17ሳንቲ ማትር ወይም 6.69 ኢንች ያህል ይሰፋል፡፡

 

    1. ብረ ንግስት

 

asha rani

አሻ ራኒ የሁለት የአለም ክበረ-ወሰኖች ባለቤት ነች፤ ከባድ ነገሮችን በጸጉሯና በጆሮዋ በመጎተት ብቃቷ፡፡ የ23 አመቷ አሻ በዚህ ለዩ ችሎታዋ ብረቷ ንግስት የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷታል፡፡

 

    1. ቀንዳሟ ወይዘሮ

 

Kendamua

ይህ ደግሞ ከወደ ቻይና የተገኘ አስገራሚ ዜና ነው፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2010 ዣንግ ሩይፋንግ የተባሉ ወይዘሮ ግንባራቸው ላይ ቀንድ በማብቀል አለምን አስደምመዋል፡፡ ወይ ጉድ!!

 

    1. የብርቱ ሳንባ ባለቤት

 

bale sanba

እርስዎ ምን ያህል መጠን ያለውን ፊኛ መንፋት ይችላሉ? ማንጂት ሲንግ የተባለው ግለሰብ ግን 2.5 ሜትር መጠነ-ዙሪያ ያለውን ፊኛ በ42 ድቂቃ ውስጥ በመንፋት በአለማችን የጠንካራ ሳነባ ባለቤት መሆኑን አስመስክሯል፡፡

 

    1. እጁን እንዳነሳ የቀረው ሰው

 

Amagnu

ይህ ሰው የሂንዱ እምነት ተከታይ ነው፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1973 ሳደሁ አማር ባራቲ የተባለ ግለሰብ የሂንዱ አምላክ ክብር ሲል ቀኝ እጁን አነሳ፤ ከዛን ቀን ጀምሮ ለአምላኩ ክብር ያነሳውን እጁን አላወረደም፡፡

 ምንጭ፡-proudlyhabesha.