Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

አነስተኛና መጠን ያለው ቀላሉ ስልክ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚዎች እ??

አነስተኛና መጠን ያለው ቀላሉ ስልክ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚዎች እጅ ይደርሳል

 

 

በመጠኑ አነስተኛ እና ቀላል ነው የተባለው ሞባይል ስልክ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚዎች ዘንድ እንደሚደርስ ተገለፀ።

“ላይት ፎን” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ስልኩ የክሬዲት ካርድ ወይም የኤ.ቲ.ኤም ካርድ መጠን ያለው ሲሆን፥ ስልክ መደወል እና ስልክ ሲደወልልን ጥሪ መቀበል ብቻ የሚያስችል ነው።

“ላይት ፎን” ለስማርት ስልኮች አጋዥ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ሲሆን፥ ሰዎች ስልካቸውን ስራ ቦታ ወይም ቤት ጥለውም ቢወጡ የሚመጡላቸውን ጥሪዎች ወደዚህኛው አነስተኛ ስልክ እንዲተላለፍ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ከዚህ ውጪም ስልኩ 2G ሲም ካርዶችን የሚቀበል መሆኑም ተገልጿል።

የባትሪ አቅሙ ከፍተኛ ነው የተባለለት ይህ ስልክ፥ አንድ ጊዜ ሀይል ከተሞላ ባትሪው ለ21 ቀናት ያገለግላል ተብሏል።

ካሜራ እና የአድራሻ መመዝገቢያ የሌለው “ላይት ፎን”፤ ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ የሚደውሉለትን የ10 ሰዎች ስልክ ቁጥር መያዝ ግን ያስችላል።

ሞባይል ስልኩን የቻይናው ፋክስኮን ኩባንያ ነው የሚያመርተው።

ስልኩ ለተጠቃሚዎች ይቀርባል ከተባለው ጊዜ በጣም የዘገየ ሲሆን፥ የላይት ፎን ኩባንያ መስራች ጆዪ ሆሊየር ለዚህም ይቅርታ ጠይቀዋል።

“ስልኩ የዘገየበት ምክንያትም የአይ ፎን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ገደቦችን ጥሎብን ስለነበረ ነው፤ አሁን ግን ተስተካክሏል በቀጣይ 15 ቀናት ውስጥ ደንበኞች ዘንድ መቅረብ ይጀምራል” ብለዋል።

ነጭ ቀለም ያላቸው 1 ሺህ 800 የላይት ፎን ሞባይል ስልኮች እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ለተጠቃሚዎች ይቀርባሉ ያሉት ሆሊየር፥ ጥቁር ቀለም ያላቸው ስልኮች ደግሞ በጥር ወር ላይ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።

“የላይት ፎን” ሞባይል ስልክ የመሸጫ ዋጋ 100 የአሜሪካ ዶላር ተደርጎ ነው የተቆረጠው።

 

ምንጭ፦ www.bbc.com