Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ስማርት ስልኮችን ከቫይረስ የሚከላከለው “ዩ.ኤስ.ቢ ኮንዶም”

ስማርት ስልኮችን ከቫይረስ የሚከላከለው “ዩ.ኤስ.ቢ ኮንዶም”

 

 

ስማርት ስልካችን ባትሪ በሚጨርስበት ጊዜ ስልካችንን በዩ.ኤስ.ቢ ኬብል አማካኝነት ኮምፒውተር ላይ ወይም ሌላ ዩ.ኤስ.ቢ በሚወስዱ ቁሶች ላይ ሰክተን ሀይል መሙላት በብዛት የተለመደ ነው።

ታዲያ በዚህ ጊዜ የምንሰካበት ኮምፒውተርም ይሁን ሌላ የኤሌክትሮኒክስ ቁስ ብዙ ሰው የሚጠቀምበት ከሆነ በቀላሉ የተለያዩ አይነት ቫይረሶች በዩ.ኤስ.ቢ ኬብሉ አማካኝነት ወደ ስልካችን ሊገቡ ይችላሉ።

ምክንያቱም ዩ.ኤስ.ቢ ዳታ እንደሚያስተላልፈው ሁሉ ቫይረስም ወደ ስልካቸን ሊያስተላልፍ ስለሚችል።

ይህንን ለመከላከል አምራቾች “ዩ.ኤስ.ቢ ኮንዶምስ” የተባለ እና ስልካችንን ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ከሀይል ውጪ ሌላ ዳታ ወደ ስልካችን እንዳይገባ የሚከላከል ቴክኖሎጂ አስተዋውቀዋል።

አዲሱ “ዩ.ኤስ.ቢ ኮንዶም” ሰዎች ስልካቸውን ከኮምፒውተር እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ጋር በሚያገናኙበት ጊዜ ስልኩ ከሀይል ውጪ ዳታ እንዳይቀበል የሚያደርግ ነው።

ኮንዶሙን በዩ.ኤስ.ቢ ኬብሉ እና በኮምፒውተሩ መካከል የሚሰካ ሲሆን፥ መሃል ላይ ሆኖ ቨይረሶችን እንደሚከላከለም ተነግሯል።

በአሁኑ ጊዜ በርካቶች ምርቱን መጠቀም መጀመራቸው ነው የተነገረው።

“ዩ.ኤስ.ቢ ኮንዶም” የመሸጫ ዋጋም 10 የአሜሪካ ዶላር መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk