Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ተመራማሪዎች ኤች.አይ.ቪን በዩ.ኤስ.ቢ /ፍላሽ ዲስክ አማካኝነት በቀላሉ መመ

ኤች.አይ.ቪን በዩ.ኤስ.ቢ /ፍላሽ ዲስክ አማካኝነት መመርመር የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተዋወቀ

 

 

ተመራማሪዎች ኤች.አይ.ቪን በዩ.ኤስ.ቢ /ፍላሽ ዲስክ አማካኝነት በቀላሉ መመርመር የሚያችል ቴክኖሎጂ አስተዋውቀዋል።

የእንግሊዝ ለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ ተመራማሪዎች ይፋ ያደረጉት አዲሱ ቴክኖሎጂ በ30 ደቂቃ ውስጥ የምርመራ ውጤቱም የሚያሳውቅ ነው ተብሏል።

የዩ.ኤስ.ቢ የመመርመሪያ ቁስ ከኮምፒውተር ወይም መሰል ዩ.ኤስ.ቢን ከሚያነቡ ኤሌክትሮኖክስ ጋር በማገናኘት ነው የሚሰራው ይላሉ ተመራማሪዎቹ።

ይህም የደም ጠብታ በዩ.ኤስ.ቢው ላይ በማድረግ ሲሆን፥ ደሙም ኤሌክትሪካል ሲግናል በመፍጠር ኮምፒውተሩ እንዲያነበው ያደርጋል።

በዚህም መሰረት ቴክኖሎጂው በደም ውስጥ ያለን የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መጠን የሚለካ ሲሆን፥ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ታማሚዎችም የጤንነታቸውን ሁኔታ ለመከታተል ሊጠቀሙበት ይችላሉ ብለዋል።

ተመራማሪዎቹ አዲሱ ቴክኖሎጂውን ውጤታማነት በሙከራ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል።

በሙከራው ጊዜም ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የ991 ሰዎች የደም ናሙና ላይ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ 95 በመቶ ስኬታማ ምርመራ ማድረግ እንደተቻለም ተነግሯል።

የእያንዳንዱ የደም ናሙና ውጤትም በአማካኝ በ20 ነጥብ 8 ደቂቃዎች ማወቅ እንደተቻለም ነው ተመራማሪዎቹ ያስታወቁት።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለፃ፥ አዲሱ ቴክኖሎጂ በተለይም የኤች.አይ.ቪ መመርመሪያ እጥረት በብዛት በሚያጋጥማቸው ከሰሃራ በታች ላሉ እና ሌሎችም ቫይረሱ በስፋት በተስፋፋባቸው አካባቢዎች አዎንታዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

ዩ.ኤስ.ቢን በመጠቀም እንዴት ሌሎች በሽታዎችን መለየት እንችላለን የሚለው ቀጣይ ስራችን ነው ሲሉም ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

 

ምንጭ፦ www.upi.com/Health