Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ብዙ ጊዜ ለመተው አስቸጋሪና ለጤና ጠንቅ ከሆኑ መጥፎ ልማዶች አንዱ ሲጋራ

በሲጋራ ጭስ የተጎዳን ሳንባ ለማከም

 

ብዙ ጊዜ ለመተው አስቸጋሪና ለጤና ጠንቅ ከሆኑ መጥፎ ልማዶች አንዱ ሲጋራ ማጨስ ነው።

ሲጋራ ማጨስ ደግሞ ለሳንባ ደህንነት ጠንቅ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ዋናው መሆኑ ይነገራል።

በሲጋራ ጭስ ሳቢያ የመተንፈሻ አካል ችግር ይከሰታል፤ ይህ ጉዳት በተለይም በሳንባ ላይ ከፍ ያለ ችግር እንደሚያስከትል ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት።

የህክምና ባለሙያዎች ይህን ሱስ ማቆምና ጤናን መጠበቅ ተገቢ እንደሆነ ይመክራሉ።

ከዚህ በታች ደግሞ ባለሙያዎች ረጅም ጊዜ ሲጋራን አጭሰው ያቆሙና ሳንባና የመተንፈሻ አካላቸው ላይ ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች ይህንን ቢያደርጉ በማለት ምክረ ሃሳባቸውን ያቀርባሉ።

ፍራፍሬ መመመገብ፦ ፍራፍሬዎችን አብዝቶ መመገብ በሲጋራ ጭስ የቆሰለን ሳንባ ለማከም ያስችላል።

በሳንባ ላይ የሚፈጠርን ቁስለት ማከምና ከጭስ ብዛት ሳንባ ላይ ተለጥፎ የሚቆየውን ጥቁር ነገርም ለማጽዳት እንደሚያስችል ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት።

የዝንጅብል ሻይ፦ ረጅም ጊዜ አጭሰው ሲጋራ ካቆሙ የመተንፈሻ አካልና ሳንባ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ አይቀርም።

እናም የተጎዳውን ለማከም የሚጠቀሙበት ሌላኛው መንገድ ደግሞ በየቀኑ የዝንጅብል ሻይን አፍልቶ መጠጣት ነው።

ዝንጅብል በእነዚህ የሰውነት ክፍሎች ላይ የደረሰውን አብዝቶ የመቅላት፣ የማበጥ እና የመቆጣት ጉዳት የማስወገድ ሃይል አለውና እርሱን ይጠቀሙ።

የተመጣጠነ አመጋገብ ስርዓት፦ ለሰውነት ተስማሚ የሆነና የተጎዳን አካል በሚጠግን መልኩ የተመጣጠነ አመጋገብ ስርዓትን መከተልም ሌላው አማራጭ ነው።

ለዚህም በማዕድን እና ቪታሚን የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር ዋናው አማራጭ ነው ይላሉ።

አትክልትና ፍራፍሬዎችን አብዝቶ መጠቀምን የሚመክሩት ባለሙያዎች ቢያንስ በቀን እስከ አራት አይነት ፍራፍሬና ሶስት የተለያዩ አይነት አትክልቶችን መመገብ እንደሚያስፈልግም ይጠቅሳሉ።

ንፁህ አየር፦ በተቻለ መጠን ንጹህና ያልተበከለ አየር ባለበት አካባቢ መዋልና ጊዜን ማሳለፍም መልካም ነው።

ሌላው ደግሞ ሳንባንና የመተንፈሻ አካልን ሊጎዱ የሚችሉ ልማዶችን ማስወገድ መልካም መሆኑንም ያስረዳሉ።

ለዚህ ደግሞ ኬሚካል ማጽዳት፣ ጀርምና ቆሻሻ ማጽዳት ከመሳሰሉ ስራዎች ፣ ብናኝ ያለባቸው የማተሚያ ቤትና መሰል ስራዎችን ማስወገድ እና በመተንፈሻ አካል ላይ ችግር በሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ላይ አለመሳተፍን ይመክራሉ።

ከዚህ ባለፈም ቤት ውስጥ ሲቀመጡ ቤቱን በኬሚካል ከማጽዳት መቆጠብ እና ብናኝ ነገሮችን ማስወገድ።

በተጨማሪም መስኮትን መክፈትና ንጹህ አየር እንዲገባ በማድረግ የታፈነ እና የታመቀ አየርን ማስወገድም ልማድዎ ያድርጉ።

እነዚህ የባለሙያ ምክረ ሃሳቦች ረጅም ጊዜ በሲጋራ ጭስ የተጎዳን ሳንባና የመተንፈሻ አካል ለማከም የሚያስችሉ ናቸውና በዚህ ህይዎት ካለፉ ይጠቀሙባቸው።

ምንጭ፦ livestrong.com/a