Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ይህ የሰውነት ጠረን ጤናማ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ግን

መጥፎ የሰውነት ጠረንን ለመከላከል

የሰው ልጅ የራሱ የሆነ የተለየ የሰውነት ጠረን አለው።

ይህ የሰውነት ጠረን ጤናማ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ግን ከመጠን ያለፈ ይሆንና ከራስ አልፎ ሌሎችንም ሊረብሽ ይችላል።

ሰውነታችን ኤክሶክራይን (exocrine) እና አፖክራይን (apocrine) የተሰኙ ሁለት አይነት ላብ አመንጪ እጢዎች አሉት።

ኤክሶክራይን የተባሉት እጢዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍል የሚገኙ ሲሆን፥ የአፖክራይን እጢዎች ደግሞ ጉርምስና እና ኩርድናን በሚያመላክቱና ፀጉር በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው።

የአፖክራይን እጢዎች ፕሮቲንና ስባማ ንጥረ ነገሮችን ያመነጫሉ፤ ይህም ነው ለሰውነት ጠረን መፈጠር ምክንያት የሚሆነው።

የመጥፎ የሰውነት ጠረን መንስኤዎች

ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል እና ማጣፈጫዎችን አዘውትሮ መመገብ

 

ከላብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ባክቴሪያዎች

መፍትሄዎች

- ንፅህናን መጠበቅ፤ በየቀኑ ሻወር መውሰድ በተለይም ካላበን በኋላ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ

- ሻወር መውሰድ ባንችል እንኳን ሰውነታችንን ማደራረቅ

- ሙቀት በበዛባቸው ስፍራዎች የአየር ማቀዝቀዣዎችን መጠቀም

- እንደ አየር ሁኔታው ሳሳ ያሉ ልብሶችን መልበስ፤ ሙቀት አፍነው የሚይዙ ኮተን ልብሶችን አለማዘውተር

- ልብሶቻችን በተለይም የውስጥ ልብሶቻችን በአጭር ጊዜ ልዩነት መቀየር

- ቅመም የበዛባቸውን ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

- ፀረ ባክቴሪያ የሆኑ ሳሙናዎችንና ጄል መጠቀም

- ዲዮድራንት ወይም የላብ ማጥፊያ ከመጠቀማችን በፊት ብብታችን ደረቅ መሆኑን ማረጋገጥ

ከላይ የጠቀስናቸውን ሁሉ ተግባራዊ አድርገው የሰውነትዎ ጠረን የማይቀየር ከሆነ ግን ባለሙያዎችን ማማከር ተገቢ ነው።

ከሁሉም በላይ ግን ዘወትር ንፅህናችንን መጠበቅ ካልተፈለገ የሰውነት ጠረን ያድናል።

 

Source፦ www.wellnessbin.com/