Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ድብርት ሰውነታችንን፤ ስሜታችንን እና ሀሳቦቻችንን የሚነካ በሽታ ነው፡??

ድብርት

ድብርት ምንድን ነው?

 

ድብርት ሰውነታችንን፤ ስሜታችንን እና ሀሳቦቻችንን የሚነካ በሽታ ነው፡፡ አመጋገቦትንና አስተኛኘትዎን፤ ስለራስዎ የሚሰማዎትን ስሜት፤ ስለ ነገሮች ያሎትን አመለካከት በሙሉ ይነካል፡፡ እንደሌሎች የሀዘን ወይም መጥፎ ስሜት በቀላሉ ሊያስወግዱት የሚችሉት አይደለም፡፡ የዚህን በሽታ መነሻ ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ አንዳንዴ በዘር የሚተላለፍ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በቤተሰባቸው ውስጥ ይህ በሽታ የሌለባቸው ሰዎች ሲጠቁ ይታያል፡፡ በሕይወት ላይ የሚመጡ ለውጦች ለዚህ በሽታ መንስኤ ሲሆኑ ይታያል፡፡ እነዚህም የጋብቻ ፍቺን፣ የኑሮ ቦታ መለወጥን፣ ከሥራ መባረርን፣ የቅርብ ወዳጅ ወይም ዘመድ ሞት፣ ከባድ በሽታ የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

    • ሁልጊዜ ማዘንና የባዶነት ስሜት መሰማት
    • ለሚወዱት ሥራ ፍላጎት ማጣት
    • የመረበሽ ስሜት
    • ብዙ ጊዜ ማልቀስ
    • የጥፋተኝነት ስሜት፤ ጥቅም የለሽ ዓይነት ስሜት/ተስፋ የመቁረጥ ስሜት
    • ብዙ መተኛት ወይንም ከነጭራሹ አለመተኛት
    • ብዙ መመገብ ወይንም ከነጭራሹ የምግብ ፍላጎት አለመኖር
    • ሀሳብን ለመሰብሰብ ወይም ውሳኔዎችን ለመወሰን መቸገር
    • አልኮል በብዛት መጠጣትና አደንዛዥ ዕፆችን መውሰድ
    • የመሞት ወይም ራስን የማጥፋት ሀሳቦች

እንዴት መከላከል ይቻላል?

ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች ከ2 ሳምንት በላይ የተሰማዎት ከሆነ በፍጥነት ወደ አእምሮ ሀኪም ዘንድ ይሂዱ፡፡ ድብርት በተለያዩ በሽታዎች አማካኝነት ሊመጣ ይችላል፡፡ በተለይ የስኳር በሽታ፣ የልብ በሽታ፣ የመርሳት በሽታ፣ካንሰር እና ስትሮክ ለዚህ በሽታ ተጠቂ እንዲሆኑ ሊያደርጎት ይችላሉ፡፡ አንዳንድ መድሃኒቶችም ድብርትን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ የአልኮል ወይም የአደንዛዥ ዕፅ ሱሶች ይህን በሽታ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

ሕክምናው ምንድን ነው?

አእምሮአችን ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች ካልተመጣጠኑ ድብርትን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ድብርትን ለማከም/ለማሻል ለአንዳንድ ሰዎች መድኃኒት መውሰድ ፍቱን ነው፡፡ ለሌሎች ደግሞ ከአእምሮ ሐኪም ጋር መማከር የተሻለ ይሠራል፡፡ ለእርስዎ መድኃኒት ወይም የምክር አገልግሎት ካልሠራልዎት ሐኪምን ማማከር የሚሠራ መፍትሄ እስኪያገኙ ይሞክሩ፡፡ ለእርስዎ የሚስማማዎትን ሕክምና ካገኙ በኋላ በትጋት ይከታተሉት፡፡ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለውጥ ማየት ይጀምራሉ፡፡

ምንጭ፡-ሰዋሰዉ