Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 174

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 176

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 216

Notice: Undefined index: title in /home/hawassao/public_html/subpage_articles.php on line 218

ደስታ የስኬት ሚስጥር ነውን?

      ደስታ የስኬት ሚስጥር ነውን?

የhappey ምስል ውጤት

አንዳንዶች ሁልግዜ ደስተኛ መሆን ከአለም እውነታ እራስን ማራቅ ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን በጥናት እንደተረጋገጠው ደስታ አእምሮን በማጎልበት ለትምህርት እና ለስራ ውጤታማነት ያግዛል። “ታዲያ እስካሁን ይህንን እንዴት ሳንገነዘብ ቆየን?” ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ የሚሆነው ተመራማሪዎች ሁሉንም ሰው እንደ ማንኛውም አማካይ (average) ሰው አድርገን ሰለሚቆጥሩ ብቻ ነው ። ሰለ ሰው ልጅ የሚያጠኑ ሳይንቲስቶች በብዛት አማካይ ሰው ላይ ያተኩራሉ ፤ ሰለ አማካይ ነገሮች ስናጠና ደግሞ አማካይ ሆነን እንቀራለን። እስካሁን በደስታ ላይ የተደረጉ ጥናቶችም የሚያተኩሩት አማካይ ሰዎች ላይ ሰለነበር ደስተኛ መሆን የሚሰጠው ጥቅም ሳይታወቅ ቆይቷል። ነገር ግን አሁን አማካይ ሰዎችን ትተን ገንቢ ሃሳብ ያላቸው ፣ አዋቂ እና በጎ አሳቢዎች ላይ ጥናቶችን በማተኮር የተለዩ ውጤቶች እየታዘብን ነው። ደስታን በተመለከተ ስኬታማ እና በጎ አሳቢዎች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ደስተኛ መሆን በስኬታችን ላይ ትልቅ ተጸእኖ እንደሚያሳድር ነው።

በሳይንስ ዓለም ደስታ ምርጫ ነው ፤ አእምሮአችን አለምን ለመረዳት ሲሞክር ምን ላይ እንደሚያተኩር የሚወሰንበት ምርጫ። ቀድመን ስለ መጥፎ ክስተቶች ማሰብ ከጀመርን አእምሮአችን በእጃችን ሰላሉ እና ደስተኛ ልንሆንባቸው ሰለሚገቡ ነገሮች ማሰቢያ አያገኝም ማለት ነው። ነገር ግን ስለ በጎ ነገሮች ማሰብ ከጀመርን ግን ቀጣየነት ያለው ደስታን በማግኘትና አእምሮአችንን በማጎልበት ጥቅሙን እናየው ነበር።

አሁን ይህ የደስታ ሚስጥር በጥናት ሰለተረጋገጠ አለም ጆሮውን እየሰጠው ነው። አስር አመት በፈጀ ምርምር በንግዱ እና በትምህርት አለም ደስተኛ መሆን ውጤታማነትን እንደሚጨምር ተረጋግጦአል። ይህውም ሽያጭን በ37%፣ ምርታማነትን በ 31% እና ትክክለኛ ውጤት ማምጣትን በ 19% ከማሳደጉ በተጨማሪ ጤናን እና የኑሮ ደረጃን እንደሚያሻሽል ታይቶአል።

በአብዛኛው የሰራ ቦታ ያለውን የሰራተኞች ደስተኛ አለመሆን እና ደስታ ከውጤታማነት ጋር ያለውን ግንኙነት በማየት፣ ቀጣዩ ጥያቄ መሆን ያለበት “ድርጅቴ ስኬታማ እንዲሆን እና የደስተኛነትን ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ አለብኝ?” ነው። የድርጅት ባለቤቶች እና አስተዳዳሪዎች ለሰራተኞች ደስተኛነት ሲያስቡ ሌላው ህብረተሰብ ደግሞ “በግል ደስተኛ ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ?” ብሎም መጠየቅ ይኖርበታል።

ጭንቅላታችን በጎ ነገሮችን እንዲያሰብ ማለማመድ ጅምናዝየም ውስጥ ጡንቻችንን ለማዳበር ከሚደረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ጋር ይመሳሰላል። ይህውም አንድ ሰው የጅምናዝየም ውጤትን ለማየት በተደጋጋሚ እንደሚሄደው ሁሉ በጎ ማሰብንም ልማድ ማድረግ አስፈላጊ ነው። አእምሮአችን እንደ ልምድ የተያዙ ሰራዎችን ለመስራት ስለሚቀለው በጎ ማሰብን ልማድ በማድረግ ደስተኛነትን የዕለት ህይወታችን አካል ማድረግ እና ውጤታማነትን ማጎልበት ይቻላል።

እናም አንባቢዎች ከዚሁ ጋር የተያያዘ ለ3 ሳምንት ሙሉ በየቀኑ የሚሰራ ትንሽ ሙከራ ቢሰሩ መልካም ነው። (የሰው ልጅ ላይ የተካሄዱ የሳይኮሎጂ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሰው ልጅ አንድን ነገር በተከታታይ ለሶስት ሳምንት ከሰራው ከዛ በኋላ እንደ ልማድ እንደሚይዘው ነው።) እሱም በየቀኑ

በዛን ቀን ደስተኛ የሚያደርግዎትን ሶስት ነገሮች ይጻፉት (ለምሳሌ. ጤነኛ ሰለሆንኩ ደስተኛ ነኝ፣ ቤተሰቦቼ ጤነኛ ሰለሆኑ ደስተኛ ነኝ …)

በዛን ቀን ያሳለፉትን ደስ የሚል ነገር ለሁለት ደቂቃ ይጻፉት (ለምሳሌ. መክሰስ የበላሁት ኬክ እንዴት ይጣፍጣል፣ …)

10 ደቂቃ እንቅስቃሴ ያድርጉ

ለ2 ደቂቃ እራስዎን ረጋ አርገው ይቀመጡ

ጠዋት ሲነሱ ለሚወዱት ሰው (ቤተሰብ፣ እጮኛ፣ ጓደኛ) ትንሽ መልክት በኢሜይል ይተዉ ወይም በስልክ ያናግሩ

እውን ይህ ይሰራ ይሆን? … አንድ ጥሩ ስራ መስራት በሚገባበት ግዜ ገበያው የቀዘቀዘ መስሪያ ቤት ጋር አብሮ የሰራው የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ ከአራት ወራት በኋላ በሰራ እና ኑሮ ሁኔታ በቢሮው እና በሰራተኞች ላይ 24% እድገት ተመልከቷል። ጊዜያዊ ለውጥ መታየት ብቻ ሳይሆን ደስተኛ መሆን ዘላቂነት ያለው የአስተሳሰብ ለውጥ እንደሚያጎለብት ታይቶአል።

 

ወደ ደስታ አለም ህይወታችንን እንዳንቀይር ወደኋላ የሚጎትት አንድ በዘመናችን ያለው ትልቁ አስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል እና ለውጥ በአብዛኛው ጥሩ እንዳልሆነ ነው። ነገር ግን ወደ ደስተኛ አለም ህይወትን መቀየር ምንም መጥፎ ነገር ሊወጣለት የማይችል እና በትምህርት ፣ በስራ እና በሌሎችም ህይወታችን ስኬታማ መሆን የሚያስችል ነው።

 

ምንጭ፡-Shawn Achor on TED