Tenders

 

Type: Stationery

 

Organization: በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር

Dead Line: 2008-03-07

 

Tender Detail:

 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መ/ቁ 022/2008

በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በ2008 በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበ በጀት ለቋሚ እቃዎች መለያ ቁጥር ህትመት አሳትሞ ለመግዛት የሕመት አገልግሎት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 

በመሆኑም፡-

  1. በዘርፉ የንግድ ስራ የሰማሩና ህጋዊ ፈቃድና በመግስት የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያለቸው መሆን ይኖርባቸዋል፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
  4. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  5. የሚቀርበው የቋሚ እቃ መለያ ቁጥር መስጫ ስቲከር ናሙና በታሸገ ፖስታ ውስጥ መቅረብ አለበት
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ ከወገጣበት ዕለት ከየካቲት 9 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 27 ቀን 2008 ዓም ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 201 ቀርበው በመውሰድ አስፈላጊውን ዋጋ በግልጽቫትን ያካተተ መሆነ አለመሆኑን በመግለጽ ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይችላሉ፣
  7. የጨረታ ሳጥኑ የካቲት 27 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በስራ ሂደቱ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፣
  8. ተጫራቾች ብር 5000 ሺ ለህትመት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተራገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማበራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡-

ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት

የስልክ ቁጥር 0251-11-78-79

ፋክስ ቁጥር፡- 0251-11-77-29

ድሬዳዋ