Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: ቡና ኢንሹራንሽ አ.ማ

Dead Line: 2016-03-20

 

Tender Detail:

 

 

ኩባንያችን የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሸከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ አካላተ እና ሌሎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተሸከርካሪዎቹንና የተሸከርካሪ አካላትን መግዛት ለሚፈልጉ አራት ኪሎ ደብር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያችን ዋና መ/ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 30.00 በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የሚገዙበት ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መጋቢት 09 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይቻላል፡፡

 

  • ተጫራቾች ንብረቶችን እና ተሸከርካሪዎችን ቃሊት ቆርኪ ፋብሪካ ወደ ቁስቋም ማሪያም በሚወስደው መንገድ የአስፋልቱ መጨረሻ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ የካቲት 24 ቀን 2008 አስከ መጋቢት 09 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡
  • ጨረታው ቅዳሜ መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 4 ሰዓት በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪልቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  • ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  • ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ወይም Bunna Insurance S.C ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የጨረታ ማስረከበሪያው ከብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ማነስ የለበትም፡፡
  • ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሸከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሸከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው ይሸፍናል፡፡ በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኃላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላል፡፡
  • አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለው 10 የስራ ቀን ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡
  • ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

 

ቡና ኢንሹራንስ አማ

አራት ኪሎ ዳብር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 0111262861