Tenders

 

Type: Stationery

 

Organization: የሙሴ የመጀመሪያ

Dead Line: 2016-01-28

 

Tender Detail:

 

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ በወረዳ 08 የሙሴ የመጀመሪያ ት/ቤት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የደንብ ልብስ የፅዳት ዕቃዎች የተለያዩ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ ጥገናና እና የት/ቤቱ ስማ በዋናው በር ላይ ባለው ላሜራ የተመሟላ ስሙን በቀለም መጻፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሠራት ይፈልጋል፡፡በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ 

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ቲን ነምበርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  2. ተጫራቾች የዘመኑን የግብር ግዴታ ለመወጣቸው ከግብር ሰብሳቢው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  3. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰንድ የማይመለስ ብር 80/ሰማንያ ብር/በመክፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡

  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫተቱበት አጠቃላይ ዋጋ 3000/ሶስት ሺ ብር/በባንክ በተረጋገጠ የዋስትና ደብዳቤ(CPO)ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡

  7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በፈረሙት ውል መሰረት ሙሉ በሙሉ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

  8. የጨረታው ሰነድ ዋናው እና ኮፒውን በሰም በታሸገ በሁለት ኤንቨሎፕ ታሽጎ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ  በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን በ11 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

  10. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበርያ ዋስትና 10/100/አስር መቶ/CPO/ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር ውል ይፈርማል፡፡

ማሳሰቢያ፡-ከላይ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች ያላሟላ ተጫራቾች  ከጨረታው ውድድር ውጪ ይሆናል፡፡ት/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠነቀ ነው፡፡

አስራሻ፡-ከጎተራ ማሳለጫ በሚወስደው መንገድ ከንፋስ ስልክ ቴ/ኮሌጅ ፊት ለፊት ሐኪም ማሞ ቤት በሚወስደው መንገድ ጫፍ ላይ ስልክ ቁጥር 011 442 4694/0114707199