Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ

Dead Line: 2016-04-05

 

Tender Detail:

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ በ2008 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ተ.ቁ

የጨረታው ዓይነት

የመዝጊያና የመክፈቻ ቀን

1

የተለያዩ ቋሚና አላቂ የጋራዥ መስሪያ ዕቃዎች ግዥ

አርብ መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም የጨረታ ሳጥኑ ከሰአት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰአት በኃላ 8፡30 ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

2

የወጥ ማሞቂያ ዲሽ

ሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

3

ፕላስቲክ ቦቲ ጫማ

ሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም የጨረታ ሣጥኑ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

 

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብ የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ወረቀት ከመጫረቃ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  2. ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ስነ-ስርዓት እና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት የግዥ አዋጅ መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፡፡

  3. ፈላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉት ሎጀ/ዋ/ መምሪያ ሲሆን የጨረታ ሰነዶች የሚመረመሩበት ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7/ሀ/በተገለፀው አድራሻ ነው፡፡

  4. ከላይ በመግለጫ ለተጠቀሱት የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዶችን ከዚህ በታች በቁጥር 7/ሀ/በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚላክው በአካል ቢሮው ድረስ በመምጣት ሲሆን ለሚዘገይ የጨረታ ሰነድ ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንግልፃለን፡፡

  5. የተጫራቾች በሀርድ ኮፒ በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ያልተካተቱ የተለያዩ የጨረታ መመሪያዎች ስላሉ ማንኛውም ተጫራች በሶፍት ኮፒ ለመውሰድ ባዶ ሲዲ ብቻ ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡

  6. የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  7. ለማብራሪያ እና የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የሚያገለግል አድራሻ

ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ (ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት)

ስልክ ቁጥር 011 371 19 48

ስልክ ቁጥር 011 371 28 85

ፋክስ ቁጥር 011 371 77 92

ቢሮ ቁጥር 08

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ግዥ ቡድን