Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: ችልድረንስ ሆፕቸስት

Dead Line: 2016-04-02

 

Tender Detail:

 




ችልድረንስ ሆፕቸስት የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ በኢፌዴሪ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በተሰጠው እውቅና መሰረት ከተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ጋር በቅንጅት በልጆችና በማህበረሰብ ልማት ላይ በተለያዩ ክልሎች እየሰራ ይገኛል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ድርጅቱ በወንዶገነት አሮማ ትምህርት ቤት አንድ የመማሪያ ብሎክ /አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሉት/ ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸው የዘመኑን ግብ /የ2008 ዓ.ም/ የተከፈለበትና ህጋዊ ፈቃድ በኮንስትራክሽን የንግድ ዘርፍ (GC/BC6ና ከዚያ በላይ) ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣

  2. ተጫራቾቹ የጨረታውን መስፈርት የሚያሟሉበትን ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ቁጥር፣ ቫት፣ ታክስ ክሊራንስ እና ተጨማሪ ማስረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው፣

  3. ለጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኢ (CPO) ወይም ባንክ ጋራንቲ (Bank Guarantee) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣

  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ሀዋሳ ከተማ፣ ገበያ ዳር እናት መካነ ኢየሱስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው ችልድረንስ ሆፕ ቸስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፤

  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ6ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር /4/ በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፣

  7. ተጫራቾች በተገለጸው ስፔስፊኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ /በፋክስ/ ከተገለጸላቸው ከ5ኛው ቀን በኋላ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ውል መፈረም አለባቸው፣

  8. የጨረታ አሸናፊው የጨረታ ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ከተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 251 118 61 47 12