Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ከተማ ልማትና ቤቶች ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-05-08

 

Tender Detail:

 




የሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ከተማ ልማትና ቤቶች ጽ/ቤት በጭሬ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በከተማው ውስጥ ለውስጥ ለማሰራት ላቀደው የጌጠኛ ድንጋይ መንገድ የጎርፍ መውረጃ ቦይ ለማስገንባት ህጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው GC-9 /እና ከዚያ በላይ በኮብልስቶን የተደራጁ ሆነው በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፤
  2. የበጀት ዓመትን ግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፤
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  4. የጥሩ አፈጻጻም ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
  5. የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) የባንክ ጋራንት ማስያዝ የሚችል፤
  6. የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ቢድ ቦንድ ኦርጅናሉና 2 ፎቶ ኮፒዎችን ለየብቻቸው በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፤ በሁሉም ዶክመንቶች ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም መምታት ይኖርበታል፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 13 ቀን በማይመለስ 200 ብር በጭሬ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡ ሰነዱን በ14ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 ሰዓት በጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባዋል፡፡ጨረታው በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፤
  8. የወቅቱ የገቢያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ በፊት የግንባታ ሳይቱን በራሱ ወጪ መጎብኘት ይችላል፤
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ከባንክ /ከአደራጁ መ/ቤት /ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፤
  11. አሰሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆኖ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  12. ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበትን ቀን በስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን ይሆናል፤
  13. ለበለበ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912 68 70 15/ 09 16 38 55 66 /09 36 15 71 /09 16 03 70 38