Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Dead Line: 2016-06-08

 

Tender Detail:

 





የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ 3B+G+M+12 የሆነ የሐዋሳ ዲስትሪክት የግንባታ ስራ ለማከናወን ደረጃቸው አንድ (GC/BC-1) የሆኑ ስራ ተቋራጭ ስራ ላይ የተሰማሩና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ ከመሰረተ ልማት ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የስራ ተቋራጮች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር በሚገኘበት ቫቲካን ኤምባሲ ወረድ ብሎ በቀድሞ ሚድሮክ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ህንፃ ግንባታ ክፍል ግንቦት 01 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒካል ሰነድ ዋናውንና ሁለት ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋናውንና ሁለት ፎቶ ኮፒ (በማሽን ኮፒ) ሰነዶችን ለየብቻ የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 01 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በፊት በማስመዝገብ ማስገባት አለባቸው፡፡

  3. ተጫራቾ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ (BID BOND) ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank guarantee) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

  4. ተጫራቾች ጨረታውን ሲገዙ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የስራ ፍቃድ፣ የታክስ ከፋይነት ማስረጃ (ቲን ሰርተፍኬት)፣ ታክስ ክሊራንስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

  5. ጨረታው ሰኔ 01 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር ህንፃ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

  6. ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113 72 28 65/72/69