Tenders

 

Type: Accounting / Audit

 

Organization: በደቡብ ብሔር ብሔሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ

Dead Line: 2016-05-27

 

Tender Detail:

 





በደቡብ ብሔር ብሔሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ
ለከተማ ፕላን ኢንሲቲትዩት አገልግሎት የሚውል ቶታል እስቴሽን የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በመስኩ ከተሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከተጫራቾች የሚጠበቀው፡-

  1. ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፤

  4. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 2% በመ/ቤቱ ስም በባንክ በተመሰከረለት /CPO/ ወይም ጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከደቡብ ክልል ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆን ወይንም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የሚከፈትና የማይከፈተውን በመለየት አሟልተው በሁለት ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በግዢ፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

  8. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በሰንበት ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ አሸናፊነታቸው ተለይቶ እስከሚገለጽ ድረስ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ20 ቀናት ይሆናል፡፡

  10. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀ  በአምስት ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የሽያጩን ጠቅላላ ዋና 10% በንግድ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል በመግባትና ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቶታል ስተሽኑን ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ የግዢ፣ ፋይናንስ አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 አምጥቶ ማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡

  11. የጨረታ አሸናፊነታቸው እንዲታወቅ ለጨረታ ማስረከቢያ ያስያዘውን ገንዘብ ወይም /CPO/ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡  
     
  12. የጨረታ አሸናፊው በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት ቀርቦ ውል መግባት ካልቻለ የጨረታ አሸናፊነቱ በገዛ እጁ እንዲሰረዝ ተደርጎ የጨረታ አሸናፊነቱ መሰረት ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

  13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

በስልክ ቁጥር፡- 046 2205936/046 22094893/046 2209484

የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ