Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ውሃና ፋሳሽ አገልግሎች ድርጅት

Dead Line: 2015-02-05

 

Tender Detail:

 

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ውሃና ፋሳሽ አገልግሎች ድርጅት ለከተማው አማራጭ ው ለማቅረብ ቀጥሎ የተጠቀሱት ጠላቂ ፓምፖች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ ቧንቧዎችና የቧንቧ መገጣጠሚያ ዕቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-

  1. የውሃ መሣሪያዎች ግብዓት አቅርቦት በዘርፍ የተመዘገባችሁ የዘመኑን የሥራ ፈቃድ ያደሳችሁ የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁና ቲን ነምበር ያላችሁ

  2. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ

  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሁለት ቅጂ/ኮፒ/ ለየብቻው ከኦርጂናል ኮፒው ለይቶ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል

  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ ለውሃ አገልግሎት ሂሳብ ክፍል በመክፈል የጠረታው ሰነድ እስከ 15ኛ ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል

  5. ጨረታው በ16ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል

  6. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ተከትለው ትዕዛዙን መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ኦርጅናልና ቅጂውን ለይቶ ማሳወቅ ከወልቂጤ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ስም የተዘጋጀው ሲፒኦ ከዋናው ዶክመንት ጋር መያያዝ ይኖርበታል

  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

  8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች እስከ ወልቂጤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ድረስ በማቅረብ ጥራቱን አስፈትሾ ማስረከብ ይኖርበታል

አድራሻ፡- ወልቂጤ ከብሩክ ህንፃ/ ከጉራጌ ዞን አስተዳደር ህንፃ ፊት ለፊት አስፓልት ዳር ያገኙታል፡፡

ስልክ ቁጥር በ0113 300634/ 0113 300113/ በፋክስ ቁጥር 0113 300043 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡