Tenders

 

Type: Agricultural Products

 

Organization: የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን

Dead Line: 2016-05-20

 

Tender Detail:

 




የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
በ2008 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ የጥበቃና የስፖርት አገልግሎት የሚውሉ የፖሊስ ውሾች መኖ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን

ሎት

የጨረታው ዓይነት

ናሙና የሚቀርብ መለያ

የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን

001

የእንስሳ መኖዎች

 

10000.00

አጥንት የሌለው ስጋ

ናሙና የማይቀርብበት

 

ስለዚህ፡-

ተጫራቾች ከዚሀ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል በፅሁፍ ማቅብ አለባቸው፡፡
  2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  5. የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. በጨረታ ለመሳተፍ የሚስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፡፡
  8. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረቅ አይቻልም፡፡
  9. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
    • ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል/ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡
    • ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን የእንስሳት መኖ በማለት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን፣ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
    • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስዙት ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
    • በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም የእንስሳት መኖዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ በሚገኙት እንስሳት ጥበቃ ማሰልጠኛ ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫ በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፣
    • በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት የሚቀርበው ስጋ አጥንት የሌለው መሆን አለበት፣
    • ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢና ፋይናንስ ቢሮ ቀረበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
    • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ8ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
    • በ8ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል፣
    • የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፡፡
    • ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
    • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 0111 11 04 48 / 0111 26 43 61 የውስጥ ስልክ /1209/1332

የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር

ፖሊስ ኮሚሽን