Tenders

 

Type: Electronics

 

Organization: የቤንች ማጂ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ

Dead Line: 2016-05-28

 

Tender Detail:

 

 



የቤንች ማጂ  ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ለዞን መምሪያዎች ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ኪቦርድ፣ ድራም እና ጀነሬተር እንዲሁም ከለር ፕሪንተር ግዥ ለመፈጸም በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  3. // ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

  4. ተጫራቾች ከተሰማሩበት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ስለተሰማሩበት የስራ ዘርፍ በሚመለከተው አካል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ /የዘርፍ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት/ ማስጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  5. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መውሰድ የሚችል፡፡

  6. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከዋበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የቤንች ማጂ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ ቢሮ ቁ.10 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

  7. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡

  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተውና ፈርሞበነት በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ማጂ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ ቢሮ ቁ.10 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

  9. ጨረታው በማስታወቂያ በወጣ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን፤ ቀኑ በዓል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 047 835 91 79

የቤንች ማጂ ዞን

ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ ሚዛን ተፈሪ