Catagory Lists
Tenders
Type: Construction
Organization: የወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የዞን ጤና መምሪያ
Dead Line: 2016-06-03
Tender Detail:
የወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የዞን ጤና መምሪያ ሊያስገነባ ላቀደው የቲቢ ምርመራ ሕንፃ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የስራ ተቋራጮች
- በዞን ኮንስትራክሽን መምሪያ ተመዘግበው ግብር በመክፈል የ2008 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ተ.እ.ታ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ቲን (TIN) መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ደረጃቸው 9 እና ከዚያ በላይ የሆኑና የመልካም የስራ አፈፃፀም ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ ሦስት ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የስራ ልምዱን ዋናውን (Original) ጊዜያዊ ርክክብ ቨርቫልና መጨረሻ ዙር ክፍያ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ከገቢዎች የሚሰጥ የስድስት ወር ታክስ ክሊራንስ (TAX CLEARNCE) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለዚህ ጨረታ የተጻፈ የገበያ ዕድል ድጋፍ ደብዳቤ ከዋናው ማዘጋጃ ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል የወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል መምሪያ ቢሮ ቁጥር 18 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን እና የቴክኒክ ዶክመንት ሰነድ ኦሪጅናሉንና 2 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከ21ኛው ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰዓት በወላይታ ዞን ፋ/ኢል መምሪያ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ሰርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በዞኑ ውስጥ ሲሰሩ ምንም አይነት የስራ ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸውና መልካም ስም ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-በስ.ቁ 0465512116 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
ወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ