Tenders

 

Type: Services

 

Organization: የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ

Dead Line: 2016-06-03

 

Tender Detail:

 





የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮፖሬሽን
የተለያዩ እቃዎችን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለማጓጓዝ የጭነት አገልግሎት ግዢን በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በመስኩ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈለቡት መረጃ፣ የቲን ሰርተፍኬት፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት እና የመልካም ስራ አፈጻጸም ማስረጃዎች ያሏቸው ለመሆኑ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድቦንድ ብር 8000.00 (ስምንት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተመሰከለት ቼክ ወይም በባንክ ጋራን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም አስርተው ከፕሮፖዛላቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 60.00 (ስልሳ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጥቀስ ከግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት በኮፖሬሽኑ ህንፃ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  5. ጨታው ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡

  6. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0115521097 ወይም 0115508796 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡

  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ